Get Mystery Box with random crypto!

የታዋቂው ቢሊየነር ዋረን ቡፌት ምክሮች ጓደኝነትህን ከፍ ያለ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር አ | የስብዕና ልህቀት

የታዋቂው ቢሊየነር ዋረን ቡፌት ምክሮች

ጓደኝነትህን ከፍ ያለ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር አድርግ፡፡ ካንተ የተሻሉ ሰዎችጋ የምትውል ከሆነ እንደ እነሱ መሆን ትጀምራለህ፡፡ ተራ የሆነ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር ስትሆን ተቃራኒውን ትሆናለህ፡፡

እድገትህ ያለው ከፊትህ እንጂ ከኋላህ (ካለፈው) አይደለም፣ የፊትህ ላይ አተኩር፡፡

ከምንም በላይ ራስህን አሳድግ፡፡ በፅሁፍም ሆነ በንግግር ሃሳብህን በሚገባ ለመግለፅ ተማር፣ ስልጠና ውሰድ፡፡ ይሄ ብቻ ተፈላጊነትህን በ50% ይጨምራል፡፡

በተቻለ መጠን ውስጥህ መሆን የሚፈልገውን ሁን፤ የሚያስደስትህን ስራ፡፡ 
ትሁት ሁን፡፡ ትሁት ሰው እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ አይልም፡፡ ከሌሎች ይማራል፤ ያለማቀረጥ ያነባል፣ ሎሎችን ይሰማል፣ ይማራል፡፡

አካልህን እና አእምሮህን በሚገባ ተንከባከብ፡፡ በምድር ላይ ስትኖር የሚኖርህ አንድ አካል እና አንድ አእምሮ ስለሆነ በትጋት ጠብቀው ተንከባከበው፡፡