Get Mystery Box with random crypto!

ክቡር ሰው - ካንት ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ ፀሀፊ ፦ ፍሉይ አለም ከጓ | የስብዕና ልህቀት

ክቡር ሰው - ካንት

ምንጭ ፦ ፍልስፍና ከዘርዓያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ፀሀፊ ፦ ፍሉይ አለም

ከጓደኞችህ ጋር እራት እየበላህ፣ አንዱ ተስተናጋጅ ከመጠን በላይ እያጨበጨበ አስተናባሪውን ይጣራል “እዚህ ጋር አንድ ምግብ፡፡” አንዳንድ ሰውም በሰላም ላደረሰው ሾፌር “እንዴት ነህ፣ ቻው ወይም አመሰግናለሁ” ሳይል ከታክሲ ወርዶ ወደ ጉዳዩ ያቀናል፡፡ ወንጀለኞች ህጻናትን ሰርቀው እንደ እቃ ይሸጣሉ፡፡ መንግስትም አገሩን ከዳ ብሎ ያስበውን ግለሰብ ያስገድላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች በጋራ የያዙት ነገር ምን አለ?

ኢማኑኤል ካንት አስተናጋጁን የሚያመናጭቀው ጓደኛህም፣ ለሾፌሩ ግድ የሌለው ተሳፋሪም፣ ልጆች የሚጠልፉ ወንጀለኞችም፣ አስገዳዩ መንግስትም... ሁሉም የሰውን ልጅ አግባብ ባልሆነ ሁኔታ አስተናግደዋል ይለናል።

ካንት በምክንያታዊነት ላይ ባለው የጸና አቋም በእጅጉ ይታወቃል። ለእርሱ ምክንያታዊነት ከሁሉ የላቀ ንብረታችን እንደሆነ ነው የሚነግረን። ከዚህም በላይ ምክንያታዊነት ምን ልክ ምን ስህተት ምን ኃጢአት ምን ጽድቅ እንደሆነ ይለይልናል፡፡

ካንት የሞራል ህግጋት አይለወጤ እና የጸኑ ናቸው ብሎ ያስባል። የሚደረስባቸውም በምክንያት እና ምክንያታዊነት ብቻ ነው። ይህንንም ምክንያታዊ ግብረገብነትንም ለማስረዳት ካንት ባለ ብዙ ገፅ መጽሐፎችን አሳትሟል።

ካንት ሁሉም ሰው ሊነካ የማይገባው
ክብር አለው ይለናል። እናም የሁላችንም ድርጊቶች ይህን ክብር የጠበቁ ሊሆኑ ይገባል። በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ብንሆንም የሰውን ክብር መንካት የለብንም፡፡ ሰዎች የምንገለገልባቸው ቁሳዊ መሳሪያዎች አይደሉም፡፡ ሁሉም የራሳቸው ዋጋ አላቸው። ለሁሉም ሰው ግድ ሊኖረን ይገባል።

ሁላችንም እንደ ግለሰብ ዋጋ እንዳለን እናስባለን፡፡ ዓለም የግለሰቦች ጥርቅም ናትና ለራሳችን የምንሰጠውን ዋጋ ለሁሉም ሰው መስጠት የተገባ ነው፡፡ እኛ ምንም አይነት ጥያቄ እና ምክንያት ሳንደረድር፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለራሳችን ከፍ ያለ ዋጋን ከሰጠን፣ እንደ ማህበርም ለሌሎች ሰዎች ዋጋ ሊኖረን ይገባል።

አዎ በማህበረሰብ ውስጥ አንደኛው ተገልጋይ፣ ሌላኛው አገልጋይ ሊሆን የተገባ ነው፤ ሆኖም በዚህ ሂደት ውስጥ ሰዎችን እንደ ሰውነታቸው ልናከብራቸው የተገባ ነው፡፡ አስተናጋጁም፣ የታክሲ ሹፌሩም ሆነ ሀገር ከዳተኛው ሰው ናቸው። ሁሉም ለራሳቸው ዋጋን ይሰጣሉ፡፡ ካንት ከእርሱ በኑሮ ደረጃ ዝቅ ያሉትን አገልጋዮቹን በታላቅ ክብር ይመለከታቸው ነበር፡፡

በቀጣይም ሰውን እንዴት ማዋራት እንዳለብህ ስታስብ ይህን “እንደ ሰው እያከበርኳቸው ነው ወይንስ እንደ መሳሪያ እየተጠቀምኩባቸው?” ይህም ቀላል እና ሊተገበር የሚገባው ግብረገባዊ ህግ ነው፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy