Get Mystery Box with random crypto!

የስብዕና ልህቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ human_intelligence — የስብዕና ልህቀት
የሰርጥ አድራሻ: @human_intelligence
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 89.08K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።
#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-09-12 10:37:36
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል  በሰላም አደረሳችሁ።

አዲሱ አመት የሰላም፤የፍቅር፤ የሰኬት አመት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን !!
12.8K viewsedited  07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-09 22:06:58 እንኳን አደረሰሽ (ለኢትዮጵያ )

ከፀሀይ በታች፥  አዲስ ነገር ባይኖርም
መልካም አዲስ አመት፥ ማለት  አናቆምም።
ዘመን ባይለወጥ፥ አዲስ ቀን ባይወጣ
ከድጥ ወደ ማጡ፥  ቢሆንም የኛ እጣ ።
እንኳን አደረሰሽ ማለት አላቆምም
በሚመሩሽ እንጂ፥ እኔ ባንቺ አላዝንም ።

እንኳን አደረሰሽ እንደ አምና ፥ ካች አምና
ፀሀይም ባትኖር፥ ሌሊትሽ ባይነጋ
መላው መሬትሽም፥ ቢርስ በሰው እንባ
ዘመን ቢተካካም፥   አዲስ ቀን ባይወጣ ።

በእንጥፍጣፊ ተስፋ፥  ከልቤ በቀረው
እንኳን አደረሰሽ ፥ ዛሬም እልሻለው።

ኬቲኤል

@Human_intelligence
13.1K viewsedited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-01 19:54:07 #አንጀት_አርስ_እውነታ!

ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳንችም በህይወት አንገኝም፡፡ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡

እስኪ ወደ ኋላ 150 አመት እንሂድ፡፡ወቅቱ 1872 ገደማ ነው የሚሆነው፡፡ያኔ የሰው ልጅ እንደ እቃ በአደባባይ ተደርድሮ የሚሸጥበት ወቅት ነበር፡፡በወቅቱ ብርቅ የነበረውን የፊት መስታወት ለማግኘት ሲሉ የገዛ ዘመዶቻቸውን የሸጡ ሰዎች ዛሬ የታሉ? መስታወትንስ ዛሬ ላይ እንደ ሀብት የሚያስበው ማን ነው? ማንም፡፡ጨው ወይም ጌጥ ወይም ሌላ ነገር ለማግኘት ሲሉ የተሻሻጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ዛሬ ላይ እነዚያ ሰዎች የሞቱላቸው የገደሉላቸው የተካካዱባቸው የተሻሻጡላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ይህ ነው የሚባል የረባ ዋጋ ያላቸው አይደሉም፡፡በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት ነበሩ፡፡የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ በጣም የሚያስቁ ናቸው፡፡

አስታውሳለሁ ፥ የሀይስኩል ተማሪ እያለሁ የትምህርት ቤቱ ፌመስ ለመሆን ብዙ ነገር አደርግ ነበር፡፡ዛሬ ከጥቂት አመታት በኋላ እንኳን ያኔ የነበረኝ ዝና ፥ በትምህርት ቤቱ መማሬንም የሚያስታውስ ሰው የለም፡፡አስቡት የዛሬ 150 አመት ደግሞ … ጭራሽ ትምህርት ቤቱም ላይኖር ይችላል፡፡

አሁን አሁን ላይ ዘመኑ የኢንተርኔት በመሆኑ ኢንተርኔት ትዝታችንን ያስቀምጥልናል ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ግን እስኪ በዚህ ዘመን እንኳ ዝነኛ የሆኑትን እናስታውስ፡፡ማይክል ጃክሰን በጊዜው ዝነኛ ነበር፡፡ነገር ግን ከሞተ ገና ሁለት አስርት አመታት እንኳ ሳይሞላው እየተረሳ ነው፡፡ዛሬ ላይ ካለው ትውልድ ማይክልን የሚያስታውሰው በጣም ጥቂቱ ነው፡፡እሱንም ገና ካወቁት ነው፡፡ ከ150 አመታት በኋላ ደግሞ ማይክል ጃክሰን የሚለው ስም ጨርሶ ለማንም የማይታወቅ ይሆናል፡፡

ማጠቃለያው፥ ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ዛሬ ልትሞትለት እና ልትገድልለት የተዘጋጀኸው መሬት ከዚህ ቀደምም ብዙዎች ተጋድለውለት ሞተው ጭራሽ እንዳልነበሩ ሁሉ ተረስተዋል፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ አንተ እንደ ትልቅ ሀብት የምታያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡

እና ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መጠላለፍ ከጀርባ መወጋጋት መቀናናት መፎካከር ይቅርብን፡፡ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ቀደምንም ዘገየንም መጨረሻችን መቃብር ነው፡፡

@Human_intelligence
12.9K viewsedited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-20 21:25:01 አገር ለናንተ ምንድን ናት?
በተስፋሁን ከበደ
ፍራሽ አዳሽ

የትኛው ነው ትክክል በሀገር ውስጥ ራስን መፈለግ ወይስ በራስህ ውስጥ ሀገርን መፈለግ?

@Human_intelligence
12.8K viewsAbel, edited  18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-14 19:57:47 የራስህን ቅጥር ገንባ!!!

ከሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ውስጥ የትኛው የበለጠ ቅር ያሰኝሃል?
ሀ) የጓደኛህ ደሞዝ መጨመር እና ያንተ ደሞዝ ምንም አለመጨመር
ለ) የጓደኞችህ ደሞዝ አለመጨመር፤ ያንተም እንደዚያው መሆን
ሐ ) የጓደኞችህ አማካይ ደሞዛቸው መቀነስና ያንተም እንደዚያው መሆን፡፡

«ሀ» ብለህ የምትመልስ ከሆነ እንደ አብዛኛው ሰው  አንተም የቅናት ሰለባ ነህ። አንድ የሩሲያዊያን ወግ አለ፡፡ አንድ ገበሬ አንድ ምትሃተኛ አምፖል ያገኛል፡፡ አንፖሏን ጫን ሲላትም አንድ ፍላጎቱን ብቻ የምታሟላላት ቀጭን የምትሃት ብርሃን ብቅ ትላለች፡፡ ገበሬው በዚች ነገር ላይ ጥቂት አሰብ አደረገና እንዲህ አለ፡- «ጎረቤቴ ላም አለው፤ እኔ ግን የለኝም፡፡ አሁን የእሱም እንደትሞትበት እፈልጋለሁ፡፡› አለ ይባላል።


ይህ ምንም ያህል ፀያፍ ቢመስልም አንተም እንደ ገበሬው ( አይነት የምታስብባቸው አጋጣሚዎች አሉ፤ እመን! የስራ ባልደረባህ ከፍተኛ ቦነስ ሲቀበል አንተ ግን የምስክር ወረቀት ብቻ ተሰጠህ እንበል፤ ትቀናለህ፡፡ ይህ የኢ-ምክንያታዊ ባህሪያትን ትስስሮሽ ይፈጥራል። ከዚያ በኋላ ይሄን ባልደረባህን አትረዳውም፤ ምናልባት በቻልከው መጠን እንቅፋት ልትሆንበትም ትችላለህ። እግሩ ሲሰበር በውስጥህ ምስጢራዊ ደስታ ይሰማሃል።
ከሁሉም ስሜቶች ይልቅ ቅናት ፀያፍ ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም ይህ በአንፃራዊነት ለመቀያየር ቀላል ነው፡፡ ከንዴት፣ ከፍርሃት እና ከመከፋት አንፃር ማለቴ ነው፡፡ ‹‹ከእሱ የሚገኝ ምንም ጥቅም የለምና ቅናት ከሁሉም ስሜቶች ፀያፉ ስሜት ነው›› ይላል ባልዛክ።

ባጭሩ ቅናት ለራስ የመመኘት ጥብቅ ፍላጎት የሚያመጣው ጊዜ ማባከን ነው።
ቅናትን ብዙ ነገሮች ሊያመጡት ይችላሉ፤ ባለቤትነት፣ ደረጃ፣ ጤና፣ እድሜ፣ ችሎታ፣ ታዋቂነት፣ ቁንጅና ወዘተ፡፡ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ቀጥተኛ ቅናት የሚያድርብን በብዙ ነገር ከሚመሳሰሉን ሰዎች ላይ ነው፡፡ ከመቶ አመታት በፊት ባሉ ስኬታማዎች አንቀናም፡፡ በእንስሳት ወይም በእፅዋትም አንቀናም፡፡ በከተማችን በሌላኛው ክፍል ባሉ ባለሃብቶች እንጂ በአለማችን በዚህኛው ክፍል ባሉ ባለሃብቶች አንቀናም፡፡ እኔም እንደ ጸሐፊ በሙዚቀኞች፣  በማናጀሮች ወይም በጥርስ ሃኪሞች አልቀናም፡፡ ይቺን ነገር አርስቶትል በሚገባ ጠቅሷታል፡፡ ‹‹ገጣሚ በገጣሚ ይቀናል!››

. . ሌላው በብዛት የምናየው የመወዳደሪያ ሜዳ ማህበራዊ ሚዲያው ነው። ዛሬ ላይ ፌስቡክ ብዙ ተጠቃሚዎቹን ብስጭትና ለዝለት እንደዳረገ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የሃምቦልድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ይህ ለምን እንደሆነ ለማጥናት ሞክረው ነበር፡፡ ውጤቱን? ገምተህ ይሆናል፡፡ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው ቅናት ነው፡፡ ይህ በቀላሉ የሚገባን ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ፌስ ቡክ የተሰራው ራሱ ተመሳሳይ ሰዎች ራሳቸውን የሚያወዳድሩበት መድረክ ተደርጎ ነው፡፡  በውስጥ ያሉት እንደ መውደድ (like) እና መጋራት (share) ያሉት ይዘቶቹም በከፍተኛ ሁኔታ ደስታን ለሚፈታተኑ ማወዳደሪያነቶች የተስማሙ ናቸው፡፡


ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ጓደኛህ በፌስ ቡክ ላይ የሚጭነው አንድ ፎቶ ከእውነተኛ ሕይወቱ ጋር ያን ያህል የሚገናኝ አይደለም፡፡ ፎቶ ብዙ ማበጃጀቶች የተጨመሩበትና አንተን ሌሎች የፌስ ቡክ ጓደኞችህ እየበለጡህ እንደሆነ እንድታስብ በሚያደርግ መልኩ የሚመጡ ናቸው፡፡ ይህም እነሱ በእውነተኛው ሕይወታቸው እየሆነ ካሉት በላይ የተቀባባ ነው፡፡

እንደዛሬው ዘመን ሰዎች ራሳቸውን ከሌሎች ጋር ማወዳደር የየእለት ተግባራቸው ያደረጉበት ዘመን የለም፡፡ ኢንተርኔት ቅናትን ወደ ወረርሺኝነት አሸጋግሮታል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ ውድድርን በአግባቡ ከተቆጣጠርክ በኋላ በመደበኛው ሕይወትህ ውስጥ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደርንም መቀነስ አለብህ፡፡ አስተውሉ በሁሉም ነገር አንደኛ መሆን  አይቻልም፡፡ በአለም ትልቁን የገንዘብ መጠን ሊኖራችሁ ይችላል ግን በአለም በጣም ውብ የሆነ ፊት አይኖራችሁም፡፡ አንድ ለማኝ ሊያስቀናችሁ ይችላል፡፡ የለማኙ አካል፣ ፊት፣ አይኖቹ እናንተ ካላችሁ ሊበልጥ ይችላል እናም ያ..ያስቀናችኋል፡፡ አንድ ለማኝ አንድ ንጉስን ሊያስቀና ይችላል፡፡
እና ይህንን ሁልጊዜ  አስታውሱ ሁሉም ነገር ሊኖራችሁ በፍፁም  አይችልም።

ወደ መፍትሄ ስንመጣ ቅናትን መቆጣጠር የሚቻለው እንዴት ነው? በመጀመሪያ ደረጃ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደር አቁም፡፡ ያን ጊዜ ከቅናት የፀዳ ሕይወትን ትኖራለህ፡፡ ራስህን ከሌሎች ጋር ከማወዳደር ሕይወት ውጣ፡፡ ይህ ወርቃማ ህግ ነው፡፡ ሁለተኛ የራስህን "የችሎታ ክልል "ፈልግና በራስህ ሙላው። የራስህን ቅጥር ገንባ እና ራስህን ከቀድሞ ራስህ ጋር ብቻ አወዳደር።

ሮልፍ ዶብሊ

የስብዕና ልህቀት
@Human_intelligence
13.7K viewsAbel, 16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-07 21:13:37
“ጦርነት ሲጀምር-ፖለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ፡፡ ባለፀጎች ምግብ ያቀርባሉ፡፡ ድሆች ልጆቻቸውን ይለግሳሉ፡፡ ጦርነቱ ሲያበቃ-ፖለቲከኞች ቀሪ ጥይቱን ይሰበስባሉ፡፡ ባለፀጎች ከጦርነቱ በተረፈው ሐብታቸው ማደግ ይጀምራሉ፡፡ ድሆች ግን ልጆቻቸውን በመቃብር ስፍራ ይፈልጋሉ”
ሰርቦች
13.4K viewsAbel, edited  18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-29 21:33:09 ውብ ጥቅሶች

1."ጥበብ የትናንት ረቂቅ ሚስጢር ስትሆን፤ ውበት ደግሞ የነገ ቃልኪዳን ናት።"

ኦሊቨር ሆልምስ

2."አስተሳሰብህና ምግባርህ ስብዕናህን ውብ ያደርጉታል።"
ስኮት ዌስተርፊልድ

3."ህይወትን ለቸረህ ፈጣሪህ ለስጦታው የምትከፍለው ምላሽ በህይወት ዘመንህ የምትሰራው ታላቅ ስራ ነው።"
ቢሊ ሚልስ

4."መልካም ሰው ላይ ምድራዊ በሮችን መዝጋት ይቻል ይሆናል ፣ መልካም ስራው በየሰው ልብ ውስጥ የከፈተለትን በር መዝጋት ግን አይቻልም።"

ምንዳርያለው ዘውዴ

5."እውነተኛ ፍቅር ልክ እንደ መንፈስ ነው ሁሉም ቢያወራውም የሚያዩት ጥቂቶቹ ናቸው።"

ፍራንኮይስ

6."ከምግብ ረሀብ ይልቅ የፍቅርን ርሀብ ማስታገስ ከባድ ነው።"
ቴሬዛ

7."ሁሌም ስንገናኝ ፈገግታ አይለየን፣ ፈገግታ ለመዋደድ በር ከፋች ነው።"

ማዘር ቴሬዛ

8."ፈገግታዬን ላዘኑ ልቦች ሁሉ እንድለግስ ነብሴ በልቤ መስኮት ፤ ልቤ ደግሞ በዓይኔ ውስጥ ትሳቅ።

ዮጋናንዳ

9."አንዳንድ ነገሮች አሉ አስር ጊዜ ተጠይቀው ፤ አስር ጊዜ ተመልሰው ፤አስር ጊዜ የሚጠየቁ።"
ሰለሞን ደሬሳ

10."ስለ ራሳችን ብዙ የምናወራው ፤ እውነተኛ ማንነታችንን ለመደበቅ ነው።"
ያልታወቀ

11."ልባዊ ፈገግታ የለበስከውን የነተበ ልብስ እንኳ ይደብቅለሀል።"

ሊ ሚልደን

12. ."ህይወት የፈለገነውን ያህል ሳይሆን የሚበቃንን ብቻ የምናነሳለት የልደት ኬክ ናት።"
ጆርጅ ሀሪሰን

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
14.9K viewsAbel, edited  18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-27 08:00:32 ልማድና ጥንቃቄ

“ልማድ በመጀመሪያ እንደ እንግዳ ይመጣል፣ ከዚያም እንደ ጓደኛ ይከርማል፣ በመጨረሻም እንደ ጌታ ይገዛል” – Anonymous

የሰውን ዘር የሚያሳስቡትና ብዙ የሚጠነቀቅላቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ የሚያሳስቡን ጉዳዮች ምናልባት ትኩረት ብንሰጣቸውም ሆነ ባንሰጣቸው ብዙም ችግር የማያመጡ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ግን ካልተጠነቀቅንና ካላሰብንባቸው ለአደጋ የሚያጋልጡን ናቸው፡፡ ከእነዚህ እጅጉን ልናስብባቸውና ልንጠነቀቅላቸው ከሚገቡን ሁኔታዎች ቀዳሚው የልማድ ጉዳይ ነው፡፡ እንደውም፣ ልማድ በቀዳሚነት ሊታሰብበት የሚገባና የሁሉ ነገር መሰረት ነው ብንል አንሳሳትም፡፡ ሰው ከልማድ ውጪ መኖር አይችልም፤ ወይ ጤናማ ልማድ ወይም ደግሞ ጤና-ቢስ! ከልማድ ውጪ መኖር ያለመቻልህን ሁኔታ መቀየር ስለማትችል፣ አንደኛህን ጤናማ ልማዶችን የማዳበር ውሳኔ ውስጥ ግባ፡፡

ዛሬ ብዙ አስበህበትና ሞክረህ በፍጹም ልትላቀቅ ያልቻልከውና ክፉ ውጤት ሊያስከትልብህ የሚችል አንድ ልማድ ካለብህ፣ ቆም ብለህ አስብ፡፡ መጀመሪያ ስትሞክረው እንደ እንግዳ ነገር ነው የቆጠርከው፡፡ ከዚያም ስትለምደው ልክ እንደ ጓደኛ ይናፍቅህ ጀመረ፡፡ የኋላ ኋላ መዘዙን እያየኸውና ልማዱ እያስገደደህ ሲመጣ መላቀቅ እስኪያቅትህ ድረስ አለቃህና ጌታህ እንደሆነ ማሰብ አያስቸግርህም፡፡ ለዚህ ነው የየእለት ልማዳችን ጉዳይ እጅግ ወሳኝ እንደሆነና በጣሙን ልንጠነቀቅለት የሚገባን ጉዳይ እንደሆነ ደግሞና ደጋግሞ የሚነገረን፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
12.7K viewsAbel, edited  05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 19:43:18 የዓለም ወርቃማ ጥቅሶችና አባባሎች

✓ We must all learn to live together as brothers, or we are all going to perish together as fools.
-Martin Luther King Jr.
➢ “ሁላችንም እንደ ወንድማማቾች ተፈቃቅረን መኖር ካልቻልን፤ እንደ ሞኞች ተያይዘን መጥፋታችን አይቀርም::”

✓ Love is fire. But whether it's gonna warm your heart or burn your house down you can never tell.
Jason Jordan.
“ፍቅር እሳት ሲሆን፤ መቼ ልብህን እንደሚያሞቀው፣ መቼ ቤትህን እንደሚያቃጥለው አታውቅም፡፡”


✓ Success is not the key to happiness. Happiness is the key to success. If you love what you are doing, you will be successful.
Albert Schweitzer.
➢ “ደስታ የስኬት ቁልፍ እንጂ፤ ስኬት የደስታ ቁልፍ አይደለችም፡፡ የምትሰራውን የምትወደው ከሆነ ስኬታማ ትሆናለህ::”


✓ The bad news is time flies. The good news is you're the pilot— Michael Althsuler.
➢ “መጥፎው ዜና ጊዜ መብረሩ ሲሆን፤ መልካሙ ዜና ደግሞ አብራሪው አንተ መሆንህ ነው፡፡”


✓ Every king was once a crying baby & every building was once a picture. It's not about where you are today but where u will reach tomorrow.
Anonymous.
➢ ሁሉም ንጉስ ባንድ ወቅት የሚያለቅስ ህፃን ነበር፤ እያንዳንዱ ህንፃ ንድፍ ነበር፤ ወሳኙ ነገር የዛሬው አንተነትህ ሳይሆን ለነገ የምትሰራው ማንነትህ ነው፡፡

✓ Age wrinkles the body. Quitting wrinkles the soul.
Anonymous.
➢ “እድሜ ቆዳን ሲሸበሽብ፤ ተስፋ መቁረጥ ነብስን ያነትባል፡፡”

✓ I don't know the key to success, but the key to failure is trying to please everybody.
Bill Cosby.
“የስኬትን ሚስጥር አላውቀውም፤ የውድቀት ሚስጥር ግን ሁሉንም ለማስደሰት መሞከር ነው፡፡”

✓ God gave us a gift of 86,400 seconds today. Have
we used one to say Thank you? William Arthur Ward.
➢ “ፈጣሪ በዛሬዋ ቀን 86,400 ሴኮንዶችን ሲሰጠን፤ አንድዋን ሴኮንድ እንኳ ለምስጋና አውለናታልን?”


A successful marriage requires falling in love many times, always with the same person.
Mignon McLaughlin.
➢ “ስኬታማ ትዳር ማለት ከአንድ ሰው ጋር በተደጋጋሚ በፍቅር መውደቅ ማለት ነው፡፡”


✓ What is success? It is a toy balloon among children armed with pins
Gene Fowler.
➢ “ዝና፣ መርፌ በያዙ ብዙ ህፃናት መካከል ተወጠሮ የሚንከባለል ፊኛ ነው::


✓ Success is more permanent when you achieve it without destroying your principles. Walter Cronkite.
➢ “የራስህን እምነትና ፍልስፍና ሳታጣ የምታገኘው ስኬት ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡”

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
17.0K viewsAbel, 16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-17 23:51:06 መሰውር - ኘሌቶ

ምንጭ ፦ ፍልስፍና (ከዘርዐ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ)
ፀሀፊ ፦ ፍሉይ አለም

በመንገድህ ላይ አንዲት አሮጊት አጋጠመችህ፤ እናም ይህቺ ሴት ትንሽ፣ ግን እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነን ስጦታ ሰጠችህ - አስማተኛ ቀለበት!

ይህም ቀለበት አንተን ለሌሎች እንዳትታይ አድርጎ ይሰውርሃል፤ ወደፈለግከው ስፍራ መጓዝ ትችላለህ፤ ማንም ሰው አንተን ማየት አይችልም፡፡

ጥያቄውም ይህ ነው በዚህ ቀለበት ምን ታደርጋለህ? ይህን አስማታዊ ኃይል እንዴት ትጠቀመዋለህ?

“የጋይጂ ቀለበት” ሪፐብሊክ በተሰኘው የፕሌቶ ዘመን አይሽሬ ስራ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ መጽሐፉ የፕሌቶ ታላቅ ወንድም ስለሆነውና ግላውኮን ጋይጂ ስለተባለ አንድ ተራ በግ ጠባቂ ታሪክ ይነግረናል።

ይህ እረኛ ከክርስቶስ መወለድ ሰባት መቶ አመታት በፊት የሊድያ ግዛት ተብላ በምትጠራው ስፍራ ይኖር ነበር፡፡ (ይህን ግዛት አሁን ላይ በቱርክ ውስጥ እናገኘዋለን።)

ፕሌቶ ታሪኩን እንዲህ ይተርከዋል፡-

ከእለታት በአንዱ ቀን በእጅጉ ሃይለኛ
የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በሊድያ ግዛት ውስጥ ተከሰተ፡፡ በምድር ገጽ ላይም ትልቅ መሰንጠቅ ተፈጠረ፡፡ በስንጥቁ መሃልም እረኛው ጋይጂ አንድ የተደበቀ ዋሻ ተመለከተ፡፡ በዋሻው ውስጥም ጋይጂ ከነሐስ የተሰራ የፈረስ ሐውልት አገኘ፡፡ በዚህ ሐውልት ውስጥ በከፊል የበሰበሰ የአንድ ግዙፍ ሰው ሙት አካል ይገኝበት ነበር፡፡ በአስክሬኑ የቀኝ እጅ አንደኛው ጣት ላይም ወርቃማ ቀለበት ያብረቀርቅ ነበር፡፡ እናም ጋይጂ ይህንን ቀለበት ለራሱ ወሰደው፡፡

እረኛው ይህ ቀለበት ተራ ቀለበት እንዳልነበረ ለመረዳት ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ በቀለበቱ አናት ላይ ያለችውን ጌጥ ሲያሽከረክራት፣ ጋይጂ ሰው እንዳያየው ሆኖ ተሰወረ፡፡ ቀለበቱ ለጋይጂ የመሰወርን ኃይል ሰጠው።

አስደናቂ የመሰወር ኃይልን እንዳገኘም፣ ይህ ተራ የበጎች እረኛ ወደ ቤተ መንግስት ቅጥር ዘለቀ፡፡ በዚያን ዕለት ምሽትም ከንግስቲቷ ጋር ተኛ፡፡ ንጉሱንም ገደለው፡፡ ንግስናንም ተቀበለ፡፡ እናም ራሱን የሊድያ ግዛት ገዢ አድርጎ ሾመ።

ፕሌቶ በዚህ ታሪክ ውስጥ ለማስተላለፍ የሞከረው ዋነኛ ሃሳብ ቢኖር ይህ ነው ሰዎች መጥፎ ድርጊቶችን የማያደርጉት ብያዝስ በሚል ፍራቻ ነው።

ሙሉ ለሙሉ የማንታይበት እና የምንሰወርበት ኃይል ቢኖረን - ከውርደት፣ ከመያዝ አልያም ከመታየት ፍራቻ እንላቀቃለን፡፡ ፕሌቶም - የመሰውርን ኃይል ያገኘ እና የሌላን ሰው ንብረት ላለመዝረፍ ያሰበ አልያም መጥፎ ተግባርን መፈጸም ያልፈለገ ቢኖር፣ እርሱ የአለማችን ሞኝ ሰው ነው' ይለናል፡፡

አንተስ የመሰወር ኃይል ቢኖርህ ምን ታደርጋለህ?

በአጠገብህ ያለ ጓደኛህን ጠይቀው፤ ራስህንም ጠይቅ፡፡

የሚያስገርም፣ የሚያስቅ አልያም የሚያሳቅቅ ምላሽን ታገኛለህ ። እናስ የመሰውር ኃይል ቢሰጥህ ባንክ ቤት አትዘርፍም? ልክ እንደ ጋይጂ ወደ ቤተመንግስት ለመግባት አትሞክርም? ከዚህም ሲከፋ ለመናገር የሚከብዱ ወንጀሎችንስ አትፈጽምም?

እናም... እኛን ወንጀልን ከመፈጸም የከለከለን ነገር ቢኖር “ሰው ምን ይለኛል' የሚለው ሃሳብ ብቻ ነው።

የፕሌቶ 'ሰዎች መልካም የሚሆኑት በምርጫቸው ሳይሆን ተገደው ነው' የሚለው ሃሳብ ለዘመናት ብዙ ፈላስፋዎችን አጨቃጭቋል። ሆኖም ይህ የጋይጂ ቀለበት ከሁለት ሺ አመታት በላይ ያስቆጠረ አፈ-ታሪክ ቢሆንም፣ ከምንግዜም በላይ አሁን ላይ ላለነው ሰዎችም የሚሰራ ምሳሌ ነው።

ለምሳሌ፤ ትክክለኛ ማንነታቸውን የማይገልጽ የፌስቡክ አካውንት ያላቸው ግለሰቦች፣ ማን እንደሆኑ አይታወቁምና እጅግ በዘቀጠ ሁናቴ ጸያፍ ስድቦችን ሲወራወሩ አልያም ጠብ አጫሪ እና በህግ ሊያስጠይቋቸው የሚችሉ የጥላቻ ንግግሮችን ሲዘሩ ይውላሉ፡፡

ሌላ ምሳሌ የሚሆነን እና የዘመናዊው ዓለም የመሰውር ቀለበት የሆነው ገንዘብ ነው፡፡ አስተውለህ ከሆነ የናጠጡ ሃብታሞች ምን ያህልም ጥፋት ቢያጠፉ ከህግ አይን የሚሰውራቸው ኃይል አላቸው፡፡ በገንዘባቸው ከምንም አይነት የወንጀል ውንጀላ ነጻ ይሆናሉ፡፡ ይህ ደግሞ በእጅጉ ጨካኝ የሆኑ እና ስለ ሌላው ግድ የሌላቸውን ህሊና አልባ ሰዎችን ፈጥሯል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
15.4K views20:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ