Get Mystery Box with random crypto!

ልማድና ጥንቃቄ “ልማድ በመጀመሪያ እንደ እንግዳ ይመጣል፣ ከዚያም እንደ ጓደኛ ይከርማል፣ በመጨረ | የስብዕና ልህቀት

ልማድና ጥንቃቄ

“ልማድ በመጀመሪያ እንደ እንግዳ ይመጣል፣ ከዚያም እንደ ጓደኛ ይከርማል፣ በመጨረሻም እንደ ጌታ ይገዛል” – Anonymous

የሰውን ዘር የሚያሳስቡትና ብዙ የሚጠነቀቅላቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ የሚያሳስቡን ጉዳዮች ምናልባት ትኩረት ብንሰጣቸውም ሆነ ባንሰጣቸው ብዙም ችግር የማያመጡ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ግን ካልተጠነቀቅንና ካላሰብንባቸው ለአደጋ የሚያጋልጡን ናቸው፡፡ ከእነዚህ እጅጉን ልናስብባቸውና ልንጠነቀቅላቸው ከሚገቡን ሁኔታዎች ቀዳሚው የልማድ ጉዳይ ነው፡፡ እንደውም፣ ልማድ በቀዳሚነት ሊታሰብበት የሚገባና የሁሉ ነገር መሰረት ነው ብንል አንሳሳትም፡፡ ሰው ከልማድ ውጪ መኖር አይችልም፤ ወይ ጤናማ ልማድ ወይም ደግሞ ጤና-ቢስ! ከልማድ ውጪ መኖር ያለመቻልህን ሁኔታ መቀየር ስለማትችል፣ አንደኛህን ጤናማ ልማዶችን የማዳበር ውሳኔ ውስጥ ግባ፡፡

ዛሬ ብዙ አስበህበትና ሞክረህ በፍጹም ልትላቀቅ ያልቻልከውና ክፉ ውጤት ሊያስከትልብህ የሚችል አንድ ልማድ ካለብህ፣ ቆም ብለህ አስብ፡፡ መጀመሪያ ስትሞክረው እንደ እንግዳ ነገር ነው የቆጠርከው፡፡ ከዚያም ስትለምደው ልክ እንደ ጓደኛ ይናፍቅህ ጀመረ፡፡ የኋላ ኋላ መዘዙን እያየኸውና ልማዱ እያስገደደህ ሲመጣ መላቀቅ እስኪያቅትህ ድረስ አለቃህና ጌታህ እንደሆነ ማሰብ አያስቸግርህም፡፡ ለዚህ ነው የየእለት ልማዳችን ጉዳይ እጅግ ወሳኝ እንደሆነና በጣሙን ልንጠነቀቅለት የሚገባን ጉዳይ እንደሆነ ደግሞና ደጋግሞ የሚነገረን፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence