Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን አደረሰሽ (ለኢትዮጵያ ) ከፀሀይ በታች፥  አዲስ ነገር ባይኖርም መልካም አዲስ አመት፥ | የስብዕና ልህቀት

እንኳን አደረሰሽ (ለኢትዮጵያ )

ከፀሀይ በታች፥  አዲስ ነገር ባይኖርም
መልካም አዲስ አመት፥ ማለት  አናቆምም።
ዘመን ባይለወጥ፥ አዲስ ቀን ባይወጣ
ከድጥ ወደ ማጡ፥  ቢሆንም የኛ እጣ ።
እንኳን አደረሰሽ ማለት አላቆምም
በሚመሩሽ እንጂ፥ እኔ ባንቺ አላዝንም ።

እንኳን አደረሰሽ እንደ አምና ፥ ካች አምና
ፀሀይም ባትኖር፥ ሌሊትሽ ባይነጋ
መላው መሬትሽም፥ ቢርስ በሰው እንባ
ዘመን ቢተካካም፥   አዲስ ቀን ባይወጣ ።

በእንጥፍጣፊ ተስፋ፥  ከልቤ በቀረው
እንኳን አደረሰሽ ፥ ዛሬም እልሻለው።

ኬቲኤል

@Human_intelligence