Get Mystery Box with random crypto!

የራስህን ቅጥር ገንባ!!! ከሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ውስጥ የትኛው የበለጠ ቅር ያሰኝሃል? ሀ) | የስብዕና ልህቀት

የራስህን ቅጥር ገንባ!!!

ከሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ውስጥ የትኛው የበለጠ ቅር ያሰኝሃል?
ሀ) የጓደኛህ ደሞዝ መጨመር እና ያንተ ደሞዝ ምንም አለመጨመር
ለ) የጓደኞችህ ደሞዝ አለመጨመር፤ ያንተም እንደዚያው መሆን
ሐ ) የጓደኞችህ አማካይ ደሞዛቸው መቀነስና ያንተም እንደዚያው መሆን፡፡

«ሀ» ብለህ የምትመልስ ከሆነ እንደ አብዛኛው ሰው  አንተም የቅናት ሰለባ ነህ። አንድ የሩሲያዊያን ወግ አለ፡፡ አንድ ገበሬ አንድ ምትሃተኛ አምፖል ያገኛል፡፡ አንፖሏን ጫን ሲላትም አንድ ፍላጎቱን ብቻ የምታሟላላት ቀጭን የምትሃት ብርሃን ብቅ ትላለች፡፡ ገበሬው በዚች ነገር ላይ ጥቂት አሰብ አደረገና እንዲህ አለ፡- «ጎረቤቴ ላም አለው፤ እኔ ግን የለኝም፡፡ አሁን የእሱም እንደትሞትበት እፈልጋለሁ፡፡› አለ ይባላል።


ይህ ምንም ያህል ፀያፍ ቢመስልም አንተም እንደ ገበሬው ( አይነት የምታስብባቸው አጋጣሚዎች አሉ፤ እመን! የስራ ባልደረባህ ከፍተኛ ቦነስ ሲቀበል አንተ ግን የምስክር ወረቀት ብቻ ተሰጠህ እንበል፤ ትቀናለህ፡፡ ይህ የኢ-ምክንያታዊ ባህሪያትን ትስስሮሽ ይፈጥራል። ከዚያ በኋላ ይሄን ባልደረባህን አትረዳውም፤ ምናልባት በቻልከው መጠን እንቅፋት ልትሆንበትም ትችላለህ። እግሩ ሲሰበር በውስጥህ ምስጢራዊ ደስታ ይሰማሃል።
ከሁሉም ስሜቶች ይልቅ ቅናት ፀያፍ ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም ይህ በአንፃራዊነት ለመቀያየር ቀላል ነው፡፡ ከንዴት፣ ከፍርሃት እና ከመከፋት አንፃር ማለቴ ነው፡፡ ‹‹ከእሱ የሚገኝ ምንም ጥቅም የለምና ቅናት ከሁሉም ስሜቶች ፀያፉ ስሜት ነው›› ይላል ባልዛክ።

ባጭሩ ቅናት ለራስ የመመኘት ጥብቅ ፍላጎት የሚያመጣው ጊዜ ማባከን ነው።
ቅናትን ብዙ ነገሮች ሊያመጡት ይችላሉ፤ ባለቤትነት፣ ደረጃ፣ ጤና፣ እድሜ፣ ችሎታ፣ ታዋቂነት፣ ቁንጅና ወዘተ፡፡ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ቀጥተኛ ቅናት የሚያድርብን በብዙ ነገር ከሚመሳሰሉን ሰዎች ላይ ነው፡፡ ከመቶ አመታት በፊት ባሉ ስኬታማዎች አንቀናም፡፡ በእንስሳት ወይም በእፅዋትም አንቀናም፡፡ በከተማችን በሌላኛው ክፍል ባሉ ባለሃብቶች እንጂ በአለማችን በዚህኛው ክፍል ባሉ ባለሃብቶች አንቀናም፡፡ እኔም እንደ ጸሐፊ በሙዚቀኞች፣  በማናጀሮች ወይም በጥርስ ሃኪሞች አልቀናም፡፡ ይቺን ነገር አርስቶትል በሚገባ ጠቅሷታል፡፡ ‹‹ገጣሚ በገጣሚ ይቀናል!››

. . ሌላው በብዛት የምናየው የመወዳደሪያ ሜዳ ማህበራዊ ሚዲያው ነው። ዛሬ ላይ ፌስቡክ ብዙ ተጠቃሚዎቹን ብስጭትና ለዝለት እንደዳረገ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የሃምቦልድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ይህ ለምን እንደሆነ ለማጥናት ሞክረው ነበር፡፡ ውጤቱን? ገምተህ ይሆናል፡፡ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው ቅናት ነው፡፡ ይህ በቀላሉ የሚገባን ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ፌስ ቡክ የተሰራው ራሱ ተመሳሳይ ሰዎች ራሳቸውን የሚያወዳድሩበት መድረክ ተደርጎ ነው፡፡  በውስጥ ያሉት እንደ መውደድ (like) እና መጋራት (share) ያሉት ይዘቶቹም በከፍተኛ ሁኔታ ደስታን ለሚፈታተኑ ማወዳደሪያነቶች የተስማሙ ናቸው፡፡


ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ጓደኛህ በፌስ ቡክ ላይ የሚጭነው አንድ ፎቶ ከእውነተኛ ሕይወቱ ጋር ያን ያህል የሚገናኝ አይደለም፡፡ ፎቶ ብዙ ማበጃጀቶች የተጨመሩበትና አንተን ሌሎች የፌስ ቡክ ጓደኞችህ እየበለጡህ እንደሆነ እንድታስብ በሚያደርግ መልኩ የሚመጡ ናቸው፡፡ ይህም እነሱ በእውነተኛው ሕይወታቸው እየሆነ ካሉት በላይ የተቀባባ ነው፡፡

እንደዛሬው ዘመን ሰዎች ራሳቸውን ከሌሎች ጋር ማወዳደር የየእለት ተግባራቸው ያደረጉበት ዘመን የለም፡፡ ኢንተርኔት ቅናትን ወደ ወረርሺኝነት አሸጋግሮታል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ ውድድርን በአግባቡ ከተቆጣጠርክ በኋላ በመደበኛው ሕይወትህ ውስጥ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደርንም መቀነስ አለብህ፡፡ አስተውሉ በሁሉም ነገር አንደኛ መሆን  አይቻልም፡፡ በአለም ትልቁን የገንዘብ መጠን ሊኖራችሁ ይችላል ግን በአለም በጣም ውብ የሆነ ፊት አይኖራችሁም፡፡ አንድ ለማኝ ሊያስቀናችሁ ይችላል፡፡ የለማኙ አካል፣ ፊት፣ አይኖቹ እናንተ ካላችሁ ሊበልጥ ይችላል እናም ያ..ያስቀናችኋል፡፡ አንድ ለማኝ አንድ ንጉስን ሊያስቀና ይችላል፡፡
እና ይህንን ሁልጊዜ  አስታውሱ ሁሉም ነገር ሊኖራችሁ በፍፁም  አይችልም።

ወደ መፍትሄ ስንመጣ ቅናትን መቆጣጠር የሚቻለው እንዴት ነው? በመጀመሪያ ደረጃ ራስህን ከሌሎች ጋር ማወዳደር አቁም፡፡ ያን ጊዜ ከቅናት የፀዳ ሕይወትን ትኖራለህ፡፡ ራስህን ከሌሎች ጋር ከማወዳደር ሕይወት ውጣ፡፡ ይህ ወርቃማ ህግ ነው፡፡ ሁለተኛ የራስህን "የችሎታ ክልል "ፈልግና በራስህ ሙላው። የራስህን ቅጥር ገንባ እና ራስህን ከቀድሞ ራስህ ጋር ብቻ አወዳደር።

ሮልፍ ዶብሊ

የስብዕና ልህቀት
@Human_intelligence