Get Mystery Box with random crypto!

በባንክ አካውንታችሁ ውስጥ 86,400 ብር ተቀማጭ አላችሁ እንበልና እና የሆነ ሰው ከአካውንታችሁ | የስብዕና ልህቀት

በባንክ አካውንታችሁ ውስጥ 86,400 ብር ተቀማጭ አላችሁ እንበልና እና የሆነ ሰው ከአካውንታችሁ ላይ 10 ብር ሰረቃችሁ እንበል። አስር ብሩን ለማስመለስና የወሰደባችሁን ሰው ለመያዝ ብላችሁ 86,390 ብሩን ታባክናላችሁ ወይስ ዝም ብላችሁ ትታችሁ መኖራችሁን ትቀጥላላችሁ? አዎ በእርግጠኝነት ትታችሁ መኖርን ትቀጥላላችሁ።

እንግዲህ በቀን ውስጥም 86,400 ሰከንድ ጊዜ አለን። ስለሆነም የአንድ አሉታዊ ሰው 10 ሰከንድ ንግግር 86,390 ሰከንዳችንን እንዲረብሸን መፍቀድ የለብንም። ሕይወት ከዚያ በላይ ትልቅ ናትና ለትናንሽ ነገር ጊዜዎን አያጥፉ።

@Human_Intelligence