Get Mystery Box with random crypto!

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

የሰርጥ አድራሻ: @fanatelevision
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 186.78K
የሰርጥ መግለጫ

This is FBC's official Telegram channel.
For more updates please visit www.fanabc.com

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-06-16 17:57:14
ኔዘርላንድስ ፖላንድን 2 ለ 1 አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ተጋጣሚዋን ፖላንድን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡

ቡክሳ በ16ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ፖላንድ ተጋጣሚዋን ስትመራ ብትቆይም÷ ጋክፖ በ29ኛው ደቂቃ ኔዘርላንድስን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡

በምድብ አራት የተደለደሉት ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች አንድ አቻ ሆነው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

ይሁን እንጅ ከዕረፍት መልስ ዌግሆርስት በ83ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ኔዘርላንድስ 2 ለ 1 ማሸነፍ ችላለች፡፡

የዛሬ የጨዋታ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉም 1 ሠዓት በምድብ ሦስት የሚገኙት ስሎቬኒያ እና ዴንማርክ እንዲሁም ምሽት 4 ሠዓት ላይ ሰርቢያ ከእንግሊዝ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
5.1K views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 16:55:04
ወላይታ ድቻ ከመመራት ተነስቶ ሀድያ ሆሳዕናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ27ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ከመመራት ተነስቶ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ሀድያ ሆሳዕና በመጀመሪያው አጋማሽ በተመስገን ብርሃኑ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 እየመራ ወደ መልበሻ ክፍል አምርቷል፡፡

ከዕረፍት መልስ በአብነት ደምሴ ጎል አቻ መሆን የቻለው ወላይታ ድቻ÷ ብሩክ ማርቆስ በ83ኛው ደቂቃ በራስ ላይ ባስቆጠራት ግብ ተጋጣሚውን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የፕሪሚየር ሊጉ ቀሪ መርሐ-ግብር ሲቀጥል÷ 12 ሠዓት ላይ ሻሸመኔ ከተማ ኢትዮጵያ መድንን ይገጥማል፡፡
5.8K viewsedited  13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 14:51:39
የነቀምቴ ጉዲና ቱምሳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የንግዱን ዘርፍ ያሳልጣል- ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የነቀምቴ ጉዲና ቱምሳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የንግድ እና ቱሪዝም መስኩን በይበልጥ ለማሳለጥ ከፍተኛ ሚና አለው ሲሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የነቀምቴ ጉዲና ቱምሳ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት የፌደራል፣ የኦሮሚያ ክልል እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት…

https://www.fanabc.com/archives/250018
7.9K viewsedited  11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 14:35:16

7.2K views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 13:26:41
በ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ 3 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024 የአውሮፓ ዋንጫ መርሐ-ግብር ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዚህም ቀን 10 ሠዓት ላይ በምድብ አራት የተደለደሉት ፖላንድ እና ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ይጫወታሉ፡፡

እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት በምድብ ሦስት የሚገኙት ስሎቬኒያ ከዴንማርክ እና ምሽት 4 ሠዓት ላይ ሰርቢያ ከእንግሊዝ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ከትናንት በስቲያ ዓርብ ምሽት የጀመረ ሲሆን እስከ አሁን በተካሄዱት ጨዋታዎችም÷ ጀርመን ስኮትላንድን 5 ለ 1፣ ስዊዘርላንድ ሀንጋሪን 3 ለ 1፣ ስፔን ክሮሽያን 3 ለ 0 እንዲሁም ጣልያን አልባኒያን 2 ለ 1 ረትተዋል፡፡
7.6K views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 13:05:13
የኢድል አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የኢድ ሶላት በመዲናዋ በደመቀና ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ መጠናቀቁን የጋራ ግብረ-ሃይሉ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1445ኛው የኢድል አል አድሃ (አረፋ) በዓል የኢድ ሶላት በአዲስ አበባ በደመቀና ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ሃይል አስታውቋል፡፡

የኢድ ሶላት በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች በታደሙበት እጅግ በደመቀና በዓሉን በሚመጥን ሃይማኖታዊ ሥርዓት መጠናቀቁን ነው የጋራ ግብረ-ሃይሉ የገለጸው፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስቀድሞ የተደረገውን ዝግጅት የሚመጥን የተግባር አፈፃፀም ላሳዩ መላው የፀጥታ አካላትን አመስግኗል፡፡

እንዲሁም ለበዓሉ ሠላማዊነት ለፀጥታ ሐይሉ ሥራ ተባባሪ በመሆን የድርሻቸውን ለተወጡ የዕምነቱ ተከታዬችና ለሰላም ወዳዱ የከተማው ነዋሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል ምስጋና አቅርቧል፡፡

የጋራ ግብረ-ሃይሉ ለመላው የዕምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅር፣ የሠላም፣ የጤና እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
7.2K viewsedited  10:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 12:32:39
የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ የዓለም ሀገራት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ በዓሉ በመካ እና መዲና ለዒድ ሰላት ከሀገሪቱና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በመጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት እየተከበረ ነው፡፡

በዚህም ምእመኑ (ሃጃጆች) የሃይማኖታዊ ሥርዓቱ አካል የሆነውን ጠጠር የመጣል ተግባርና ሌሎች ሥርዓቶችን ከመግሪብና ከኢሻ ሰላት በኋላ እንደሚያከናውኑ ተገልጿል፡፡

ለዚህ ሥነ-ስርዓትም በሙዝዳሊፋህ ምሽቱን ማሳለፋቸው ነው የተገለጸው፡፡

በተመሳሳይ የተባበሩት ዓረብ ኤሜሬቶች፣ ቱርክ፣ ኦማን፣ ኳታር፣ ባህሬን፣ ኩዌት፣ ዮርዳኖስ፣ ፍልስጤም፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዝያ፣ ሊቢያና ግብጽ በዓሉን በተለያዩ ሥነ-... https://www.fanabc.com/archives/249992
7.1K views09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-16 12:21:53
የኢትዮጵያና የሩሲያ የመንግስት ለመንግስትና የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል - አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና የሩሲያ የመንግስት ለመንግስትና የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ ከሰኔ 9 እስከ 12 ቀን 2016 በሚካሔደውና ‘‘ዎርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር’’ በሚል መሪ ሃሳብ በሩሲያ ቪላዲቮስቶክ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፎረም ላይ እየተሳተፈ ነው።

ከፎረሙ ጎን ለጎንም አቶ አደም ፋራህ ከሩሲያ ዩናይትድ ፓርቲ ምክትል የጽሕፈት ቤት ሃላፊ ክሊኖቭ አንድሬ ጋር ተወያይተዋል።

አቶ አደም በውይይታቸው ላይ በኢትዮጵያና በሩሲያን መካከል ያለውን ጠንካራ ታሪካዊ ግንኙነት ያነሱ ሲሆን ፥ ኢትዮጵያ በተለያዩ አጋጣሚዎች ችግሮች ሲገጥሟት ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጎን በመሆን ላሳየችው ድጋፍና ወዳጅነት ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆን በዲፕሎማሲው ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን አንስተው ፥ …

https://www.fanabc.com/archives/249986
5.7K viewsedited  09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-07 21:53:41
በአፋር ክልል የሚገኙ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የሚገኙ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢጃራ ተስፋዬ የተንዳሆ እና አላሎ ባድ የጂኦተርማል ፕሮጀክቶችን ጎብኝተው ፕሮጀክቶቹ ያሉበትን ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡ የጉብኝቱ ዓላማ ፕሮጀክቶቹ ያሉበትን ችግር ለመፍታትና ወደ ስራ ለማስገባት መሆኑን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/248977
8.7K viewsedited  18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-07 21:11:19
ፕሬዚዳንት ፑቲን ሀገራቸው ኒውክሌር ለመጠቀም የሚያስችል የሉዓላዊነት ስጋት እንደሌለባት አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአሁኑ ወቅት ሀገራቸው ኒውክሌር ለመጠቀም የሚያስችል የሉዓላዊነት ስጋት እንደሌለባት አስታወቁ። ሩሲያ ኒውክሌር ለመጠቀም የሚያስገድዳት ወቅታዊ ስጋት ባይኖርም አንዳንድ የምዕራባውያንን ዒላማ ለመምታት ለሌሎች ሀገራት የጦር መሳሪያዎችን ልትልክ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል። የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መጠቀም የሚቻለው ልዩ በሆኑ ጉዳዮች ብቻ ነው ሲሉ በሴንት ፒተርስበርግ…

https://www.fanabc.com/archives/248971
9.8K viewsedited  18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ