Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.99K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-06-15 18:47:33 አሜሪካ በጥንቆላ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

ዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ከዚህ በፊት ጥንቆላ እና ከዚሁ ጋር የተያያዙ ሁነቶችን በይፋ አግዳ ነበር፡፡

በተለይም በቨርጂኒያ ግዛት ጥንቆላ በተለያዩ መንገዶች በስፋት ከሚፈጸሙባት ግዛቶች መካከል ዋነኛዋ ስትሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የተጠቃሚዎች መብዛት ህጉ እንዲሻር ምክንያት ሆኗል፡፡

የ45 ዓመቷ አሽሊ ብራንተን በዚሁ ግዛት ላለፉት ዓመታ በጥንቆላ ሙያ ተሰማርታ ማሳለፏን እና የደንበኞቿ ቁጥርም በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን ለቪኦኤ ተናግራለች፡፡

ወደ ጥንቆላ ሙያ ከመግባቷ በፊት የስነ ውበት ባለሙያ እንደ ነበረች የምትናገረው ብራንተን ሰዎች ስለ ጥንቆላ ያላቸው አመለካከት ያለ ማስታወቂያ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል ብላለች፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ በተለይም ከባድ ውሳኔ ያለባቸው ሰዎች፣ የተበላሸ የፍቅር ግንኙነት ያላቸው እና ከሀገር ሀገር የሚያጓጉዝ ስራ ያለባቸው ሰዎች ዘብዝተው ወደ እሷ ይመጣሉ፡፡

አብዛኞቹ ደንበኞቿ ለዚሁ ስራ ተብለው የተዘጋጁ ካርዶች ወይም የእጣ ፈንታ ማንበቢያ ካርድን የሚጠቀሙ እንደሆኑ የምታነገረው ይህች አሜሪካዊት ጠንቋይ ደንበኞቿ ትንበያዎቿን እንደሚወዱት እና እንደሚሳካላቸውም አክላላች፡፡

አሜሪካ ጥንቆላን በይፋ ህገ ወጥ ነው ብላ አውጃ ቢሆንም በርካታ የሀገሬው ዜጎች ግን በድብቅ ሲጠቀሙ መቆየታቸውን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

የተጠቃሚዎችን መብዛት ተከትሎ ጥንቆላ ህገ ወጥ መሆኑ የቀረ ሲሆን ባሳለፍነው ዓመት ብቻ ይህ ዘርፍ ለ100 ሺህ አሜሪካዊያን የስራ እድል እንደፈጠረ እና 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱ ተገልጿል፡፡

የቨርጂኒያ ከተማ ህግ አውጪ ምክር ቤት በጥንቆላ ላይ ተጥሎ የነበረውን እግድ በይፋ ማንሳቱ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

በአሜሪካ ከዚህ በፊት በተደረገ ጥናት ከ10 አሜሪካዊያን አራቱ በጥንቆላ የሚያምኑ ሲሆን ከ10ሩ ዜጎች ውስጥም ቢንስ አንዱ ጠንቋዮችን አማክሮ ያውቃል ተብሏል፡፡

ዘገባው የዐል ዐይን ነው።
5.9K views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 17:54:55 በአፋር እና ሶማሊ ክልሎች ወሰን አከባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት ሊቆም የገባል፣ ዘላቂ ሰላም የሚያሰፍን መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ሲል ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አሳሰበ።

በአፋር እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች በአዲስ መልክ ግጭት መቀስቀሱን የጠቆመው ኮሚሽኑ በንጹሃን ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በአዋሳኝ አከባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎችም መፈናቀላቸውን አመላክቷል።

ኮሚሽኑ ሁኔታውን እየተከታተለው መሆኑን አስታውቆ ከሁለት ወራት በፊት በሁለቱ ክልሎች መካከል ተደርሶ የነበረው የሰላም ስምምነት መጣሱ አሳሳቢ ነው ሲል ገልጿል።

በግጭቱ ሳቢያ በንጹሃን ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በግለሰቦች እና የህዝብ ንብረቶች ላይ ውድመት መከሰቱን የተመለከቱ መረጃዎች እንደደረሱት የጠቆመው ኮሚሽኑ በግጭቱ ሳቢያ በአከባቢዎቹ የደረሰው ጉዳት ግጭቶቹን እያባባሰ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ክልሎቹ በየግዜው የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለማርገብ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚያደንቅ የጠቀሰው ኮሚሽኑ በቅርቡ በኢትዮጵያ እስላምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አማካኝነት በተደረገ ውይይት ችግሮቹን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሚያዚያ ወር 2016 ዓ.ም ስምምነት መደረሱን አውስቷል።

ግጭቶቹን ለማስቀረት በፌዴራል እና በክልል ባለስልጣናት የተወሰዱ ላሉ እርምጃዎች እውቅና የሰጠው ኮሚሽኑ ቀጣይ ርምጃዎችን ለመከላከል ተጨማሪ ትኩረት ይሰጥ ሲል አሳስቧል።

ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም የሁለቱ ክልል ባለስልጣናት ፍቃደኝነት የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ የፌደራል መንግስቱ ተጨማሪ ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል ሲሉ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ተፋላሚዎች በኢድ አል አድሃ በዓል መንፈስ ተግባብተው ውጊያው እንዳይባባስ እና ንጹሀን እንዳይጎዱ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ዋና ኮሚሽሯ አክለውም “በአካባቢው የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳያስከትል በኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል መንፈስ እንዲከላከሉ ኮሚሽኑ ጥሪ ያቀርባል” ብለዋል።

ዘገባው የአዲስ ስታንዳርድ ነው።
5.7K views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 13:53:39 የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
**
1445ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ይከበራል።

በዕለቱ በአዲስ አበባ ስታዲዮም እና በዙሪያው በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የሶላት ስነ-ስርዓት ይካሄዳል።

ፕሮግራሙ በሚካሄድበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ የተዘረዘሩት መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፦

• ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ

• ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው አጎና ሲኒማ ላይ

• ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ

• ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ

• ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

• ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ 22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ

• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ

• ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ አቧሬ ሴቶች አደባባይ ላይ

• ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

• ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ

• ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

• ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ አጠገብ

• ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ

• ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ

• ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ

መንገዶቹ ከሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ሶላቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙሟቸው አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

ለእምነቱ ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የፍቅርና የሰላም እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።
5.4K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-12 16:30:38
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡
#FastMereja
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡ ምሁራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው በማስተማር ውጤተማነት፤ ባሰተሟቸው ጥናታዊ ጹሁፎች፤ ላማህበረሰብ ለበረከቱት አካዳሚያዊ አገልግሎትና በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው የ ተቋም አስተዳደር ድምር ውጤት ነው። በዚሁ መሰረት፡-

ፕሮፌሰር ይምጡበዝናሽ ወ/አማኑኤል በሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂ
ፕሮፌሰር አንተነህ በለጠ በፍርማሴዩቲክስ
ፕሮፌሰር ካሳሁን ተስፋዬ በፕላንት ጄኔቲክስ
ፕሮፌሰር አህመደ ሁሴን በአናሊቲካል ኬሚስትሪ
ፕሮፌሰር ታደሰ እጓለ በማይክሮባዮሎጂ
ፕሮፌሰር ተክለሀይማኖት ኃ/ሥላሴ በፕላንት ባዮቴክኖሎጂ
ፕሮፌሰር ተሸመ ሰንበታ በኮንደንስድ ማተር ፊዝክስ
ፕሮፌሰር እንጉዳይ አደመ በካሪኩለም ጥናት
ፕሮፈፌሰር ሀብቴ ተኪኤ በሜዲካል ኢንቶሞሎጂ
ፕሮፌሰር ቃላብ ባዬ በ ሂዩማን ኒውትሪሽን
ፕሮፌሰር ሰለሞን ሙሉጌታ በአርባን ፕላኒንግ
ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ፍሰሀ በፖሊዮኢንቨሮመንታል ጥናት ናቸው።

ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ካደጉት መካከል ሁለት ሴት ምሁራን የሚገኙበት ሲሆን ይህም በአንድ ግዜ ሁለት ሴት ፕሮፌሰሮች ማዕረጉን ያገኙበት ልዩ ያደርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ''ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሰቲ ለመደንገግ በወጣ'' አዋጅ ቁጥር 1294/2015 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ነው በዩኒቨርሲቲው ሴኔት የቀረቡለትን የማዕረግ እድገት ያጸደቀው፡፡
5.4K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-11 18:46:48
ግንቦት 20 ከካላንደር ላይ ተሰረዘ
#FastMereja
ዛሬ በፓርላማ የፀደቀው የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን የወጣው አዋጅ በልማድ ሲከበር የቆየውን ግንቦት 20 ብሔራዊ በአልነቱ አስቀርቷል፡፡

የሰማዕታትን ቀን (የካቲት 12) እና የብሔር ብሔረሰቦች ቀን (ህዳር 29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ ታስበው ይውላሉ ተብሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰንደቀ ዓላማ ቀን፣ የመከላከያ ቀን፣ የሴቶች ቀንና ሌሎችም በዓላት ታስበው የሚውሉ ናቸው ተብሏል፡፡

አዋጁ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ አለባቸው ያላቸውን ተቋማትን ዝርዝር አስቀምጧል፡፡

በዚህም የእለት ከእለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ እና መሰረታዊ አገልግሎቶች የጤና ተቋማትና መድሃኒት ቤቶች ለሕዝብ ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ተቋማት የእሳት አደጋ፣ መከላከል አገልግሎትና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዲሁም ነዳጅ ማደያዎች ክፍት ሆነው እንዲውሉ በአዋጁ ተቀምጠዋል፡፡

ምክር ቤቱ የህዝብ በዓላትና የበዓላትን አከባበር መወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ በአንድ ድምፅ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል ሲል ሸገር ሬዲዮ ዘግበዋል።
***
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja
6.6K views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-11 13:23:50
የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ጸደ
#FastMereja
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ አጸደቀ፡፡ ረቂቅ አዋጁ የተወሰኑ ማስተካከያዎች እንደተደረጉበት ተመላክቷል። አዋጁ በ1 ድምፀ ተቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ " አዋጅ ቁጥር 1334/2016 " ሆኖ ነው የጸደቀው።

የጸደቀው አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት ሲሆን ፤ ክልሎች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ህግ አውጥተው በክልል ደረጃ የሚከበሩ አዋጆችን አከባበር መወሰን ይችላሉ ተብሏል።

ይህ የሚመለከተው እንደ ኢሬቻ፣ ጊፋታ፣ ጨምባላላ፣ አሸንዳ ፣ ሻደይ ፣ አሸንድዬ ፣ እና ሌሎችንም ሲሆን ክልሎች በራሳቸው አዋጆችን አውጥተው አከባበሩን መወሰን እንደሚችሉ ከአዲስ ማለዳ ዘገባ ተመልክተናል።
***
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja
6.6K views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-11 12:08:12 በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ38,203 ተማሪዎች ውስጥ 431 ብቻ ናቸው ለፈተና የተቀመጡት።
#FastMereja
የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ክልል አቀፍ ፈተና እያሰጡ ነዉ። እንደ ምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ መረጃ በ2016 የትምህርት ዘመን በ593 ትምህርት ቤቶች 38ሽ 203 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደሚወስዱ ቢታቀድም በሰላም እጦቱ ምክንያት በ10 ትምህርት ቤቶች 431 ተማሪዎች ብቻ በሁለት ዙር ፈተና የሚወስዱ መሆኑን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ዘገባ ፋስት መረጃ ተመልክቷል።
***
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja
6.1K views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-11 10:16:54 አብዛኞቹ ኢትዮጵያውን ስደተኞችን የያዘች ጀልባ ተገልብጣ ቢያንስ 38 ሞቱ
#FastMereja
አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ከየመን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጣ ቢያንስ 38 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ለነፍስ አድን ሠራተኞች እንደተናገሩት ጀልባዋ 250 የሚጠጉ ሰዎችን አሳፍራ የነበረ ሲሆን፣ ለመገልበጥ የበቃችውም በካበድ ነፋስ ምክንያት ነው ተብሏል።

መሞታቸው ከታወቀው 38 ሰዎች ውጪ ሌሎች 100 ሰዎች የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን፣ እነሱን ለማግኘት ፍለጋ እየተደረገ ነው።

ከየመን ዋና ከተማ አደን በስተምሥራቅ የምትገኘው የሩደም አካባቢ ባለሥልጣናት እንዳሉት አደጋው በደረሰባት ጀልባ ላይ ተሳፈረው ከነበሩት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሲሆኑ፣ የመንን ወደ ወደ ባሕረ ሰላጤው አገራት ለመሸጋገሪያነት ይጠቀሙባታል።

የሩደም አካባቢ አስተዳዳሪ የሆኑት ሃዲ አል-ኹርማ ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት በጀልባዋ ላይ የመስመጥ አደጋው የደረሰው ወደ ባሕር ዳርቻው ከመቃረቧ በፊት ነው።

በስፍራው የነበሩ ሰዎች 250 የሚሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ አደጋው የደረሰባት ጀልባ ላይ የነበሩ በርካታ ሰዎችን ሕይወት ማትረፋቸው ተነግሯል።

“ዓሳ አስጋሪዎች እና ነዋሪዎች አብረዋቸው በጀልባዋ ላይ የነበሩ 100 የሚሆኑት ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን የተናገሩ 78 ሰዎችን በሕይወት አድነዋል” ሲሉ ባለሥልጣኑ ተናግረዋል።

ጨምረውም በአደጋው ምክንያት የጠፉትን ሰዎች ለማግኘት የሚደረገው ጥረት የቀጠለ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅትም ስለደረሰው አደጋ እንዲያውቅ መደረጉ ተገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት እንደሚያመለክተው ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት ብቻ 97,000 ስደተኞች በጦርነት ውስጥ ወደ ምትገኘው የመን ገብተዋል።

በየመን ያለው ጦርነት እና በቅርቡ የየመን ሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባሕር ላይ ጥቃት እየሰነዘሩ ቢሆንም ስደተኞች ወደ አገሪቱ በአደጋኛ የባሕር ጉዞ መግባታቸውን ቀጥለዋል።

ከጂቡቲ በመነሳት በሕገወጥ መንገድ በቀይ ባሕር በኩል ወደ ሳዑዲ አረቢያ እና ሌሎች የባሕረ ሰላጤው አገራት በሚጓዙ ስደተኞች ላይ ተመሳሳይ አደጋ በተደጋጋሚ ሲደርስ ቆይቷል።

በዚህ አደገኛ መንገድ የሚጓዙት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ለሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ከፍተኛ ገንዘብ ከመክፈላቸው በተጨማሪ እንግልት እና በደል እንደሚደርስባቸው ይናገራሉ።

ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ ብቻ በተከታታይ በደረሱ ሁለት አደጋዎች 60 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ባሕር ውስጥ ሰምጠው ለሞት መዳረጋቸው መዘገቡ ይታወሳል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ነው ያስነበበው።
6.1K views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-11 10:16:52
5.2K views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-11 10:09:41
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በዛሬው እለት በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት ጀመረ።
#FastMereja
ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በ182 የፈተና ጣቢያዎች 86,672 ተማሪዎችን እንዲሁም 2,200 ፈታኞችን ፣ 700 ሱፐር ቫይዘሮችን ጨምሮ 182 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችን በማሳተፍ በዛሬው እለት መሰጠት ጀምራል።

ተማሪዎች በጠዋቱ የፈተና ጊዜ አማርኛ እና እንግሊዘኛ ፈተናዎችን የሚወስዱ ይሆናል ተብሏል።
5.6K views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ