Get Mystery Box with random crypto!

ግንቦት 20 ከካላንደር ላይ ተሰረዘ #FastMereja ዛሬ በፓርላማ የፀደቀው የህዝብ በዓላት እ | FastMereja.com

ግንቦት 20 ከካላንደር ላይ ተሰረዘ
#FastMereja
ዛሬ በፓርላማ የፀደቀው የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን የወጣው አዋጅ በልማድ ሲከበር የቆየውን ግንቦት 20 ብሔራዊ በአልነቱ አስቀርቷል፡፡

የሰማዕታትን ቀን (የካቲት 12) እና የብሔር ብሔረሰቦች ቀን (ህዳር 29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ ታስበው ይውላሉ ተብሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰንደቀ ዓላማ ቀን፣ የመከላከያ ቀን፣ የሴቶች ቀንና ሌሎችም በዓላት ታስበው የሚውሉ ናቸው ተብሏል፡፡

አዋጁ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ አለባቸው ያላቸውን ተቋማትን ዝርዝር አስቀምጧል፡፡

በዚህም የእለት ከእለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ እና መሰረታዊ አገልግሎቶች የጤና ተቋማትና መድሃኒት ቤቶች ለሕዝብ ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ተቋማት የእሳት አደጋ፣ መከላከል አገልግሎትና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዲሁም ነዳጅ ማደያዎች ክፍት ሆነው እንዲውሉ በአዋጁ ተቀምጠዋል፡፡

ምክር ቤቱ የህዝብ በዓላትና የበዓላትን አከባበር መወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ በአንድ ድምፅ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል ሲል ሸገር ሬዲዮ ዘግበዋል።
***
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja