Get Mystery Box with random crypto!

FastMereja.com

የሰርጥ አድራሻ: @fastmereja
ምድቦች: ዜና , ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.93K
የሰርጥ መግለጫ

FastMereja.net

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-06-04 19:48:20
ሜላት ንጉሴ በምን ምክንያት እንደታሰረች አልታወቀም።
#FastMereja
በማህበራዊ ሚዲያ የተቸገሩ ወገኖችን ድጋፍ እንዲያገኙ፣ ስራ ፈላጊ እና ድርጅቶችን በማገናኘት ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ከሚጠቀሙ ግለሰቦች መካከል ተጠቃሽ ናት።

ዛሬ ግንቦት 27/2016 ዓም የፀጥታ አካላት በመኖሪያ ቤቷ በመምጣት ይዘዋት ሊሄዱ እንደሆነ በፌስቡክ ገጿ ካስታወቀች በኋላ በርካቶች እንዴት ሆና ይሆን ብለዋል።

ሜላት ንጉሴ በፀጥታ አካላት ከቤቷ ተወስዳ ቀኑን ሙሉ አዲስ አበባ ፖሊስ እንደነበረች በስፍራው ከነበሩ ሰዎች ፋስት መረጃ ሰምቷል ለምን እንደተያዘች የተለያዩ የፀጥታ አካላትን ቢጠይቁም እነሱ እንደማያውቁ እንድትያዝ ብቻ ትዕዛዝ እንተሰጣቸው ገልጿል።

የተያዘችበት ምክንያት እና ክሱን ለማወቅ የተደረገው ሙከራ ዛሬ ሳይሳካ ቀርቷል ያሉት ወዳጆቿ ሜላት ንጉሴ ዛሬ እስር ቤት እንድታድር ሆኗል ብሏል።
8.4K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-03 21:22:40
ማሳሰቢያ

የአዲስ አበባ ፖሊስ በከተማዋ እየተከናወነ ባለው የመንገድ ኮሪደር ልማት እና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ወደ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስዱ አንዳንድ መንገዶች በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል።
በመሆኑም ክቡራን መንገደኞቻችን ለበረራ በምትመጡበት ወቅት ይህን ታሳቢ በማድረግ ሊከሰት ከሚችል መዘግየት ራሳችሁን እንድትጠብቁ እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
6.0K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-03 17:46:04 በኳታር ዶሃ ትልቅ የህክምና ማዕከል የከፈቱት ኢትዮጵያዊው ዶ/ር አማኑኤል ቶሎሳ
#FastMereja
ዶ/ር አማኑኤል ቶሎሳ በ18 አመታቸው ወደ ፊንላድ ሀገር በማቅናት ሚዲካል ስኩል በመግባት ትምህርታቸውን ተከታተሉ፣ ከፊንላድ ወደ ካናዳ፣ ካናዳ እየሰሩ እያሉ ኳታር ሀገር ተጠርተው በኳታር ዶሃ ሰፊ ልምድ ያላቸው እውቅ የአጥንት ቀዶ ህክምና ባለሙያ ለመሆን በቅቷል።

ዶ/ር አማኑኤል ያላቸውን ሰፊ ልምድ በመጠቀም ዶክ ሜዲካል ሴንተር በዶሃ መክፈት የቻሉ ሲሆን። ዶክ ህክምና ላይ ስፔሻላይዝድ አድርጎ የሚሰራ በኳታር ዶሃ የሚገኝ ተዋቂ የጤና አገልግሎት መስጫ ማዕከል ነው። ማዕከሉ በነሃሴ 2002 በአልሳድ ኳታር ተቋቋመ። በተጨማሪ የDOC ዳያግኖስቲክ እና ኢሜጂንግ ማዕከልን በመስከረም 2015 አቋቁሟል:: ማዕከሉ በስራ ከ150 በላይ ሠራተኞችን ቀጥሮ በማሰራት ላይ ይገኛል።

ዶ/ር አማኑኤል ቶሌሳ በአጽንኦት እንደሚገልጹት ማዕከሉ ሁለንተናዊ የጤና አጠባበቅ ሁኔታን ከዘመናዊ የህክምና ተግባራት እና ከባህላዊ ህክምናዎች ጋር አጣምሮ የያዘ ነው። ማዕከሉ የኳታርን ማህበረሰብ እና የጂሲሲ ነዋሪዎችን ባህል እና ፍላጎታቸውን በጠበቀ መልኩ በልዩ እንክብካቤ የህክምና ፍላጎቶች ለማሟላት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ዶክ ሕክምና ማዕከል ኦርቶፔዲክስ እና ትራማቶሎጂ፣ የሩማቶሎጂ፤የውስጥ ሕክምና፤ የቤተሰብ ሕክምና፤መልሶ ማቋቋም እና ማገገም፤ ዲያጎነስቲክ ኢሜጂንግ እና የላቦራቶሪ አገልግሎቶች ጨምሮ በርካታ ህክምናዎች በማዕከሉ ይሰጣል።

ዶ/ር አማኑኤል ቶሎሳ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ ያለው የህክምና አገልግሎት እንደሚያስፈልግ በመገንዘብ እነዚህን አገልግሎቶች በህክምና ቱሪዝም ለወገኖቻቸው ለማዳረስ አላማ አንግበው ተነስተዋል። ይህ ፕሮግራም ከኢትዮጵያው ወደ ኳታር ሄደው መታከም ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን ፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ ኢንሹራንስ ላላቸው ታካሚዎች እና የንግድ ተጓዦች በኳታር ከፍተኛ ደረጃ የአጥንት ህክምና እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የዶክ ሜዲካል ሴንተር ቢሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን ከእነርሱም መካከል በኢትዮጵያ ስመጥር በሆኑ የአጥንት ስፔሻሊስቶች የታገዘ የምክር አገልግሎት፣ ወረቀት ስራዎችን የቪዛ ሂደቶችን የኤርፖርት ዝውውሮችን እና ከመስተንግዶ ጋር የተያያዙ እገዛዎችን ይገኙበታል::

ታካሚዎች ወደ ኳታር ዶሃ ሲሄዱ በማዕከሉ ቋንቋ ችግር እንዳይገጥማቸው በሀገራቸው ቋንቋ እንዲስተናገዱ ሁኔታዎችን አመቻችቷል።

ጥላሁን ደሳለኝ
6.5K viewsedited  14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-03 17:46:02
5.8K views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-03 16:22:35 በአዲስ አበባ የተገደለው የፋኖ አባል ሽኝት አስክሬን በሌለበት ጎንደር ውስጥ ተደረገ
#FastMereja
ባለፈው ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የተገደሉት ሁለት የፋኖ አባላት ቤተሰቦች አስከሬናቸውን ሳያገኙ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ጎንደር ውስጥ መፈጸማቸውን ተናገሩ።

ፖሊስ በአማራ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን አባላት ናቸው ያላቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሽብር ድርጊት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሶባቸው መገደላቸውን መግለጹ ይታወሳል።

የሁለቱ ወጣቶችን ሞት ተከትሎ ወላጆቻቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አስከሬናቸውን አግኝተው ቀብር ለመፈጸም ለፌደራል ፖሊስ እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ መጠበቃቸውን ተናግረዋል።

በወቅቱ የሁለቱ ሟቾች እናቶች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ፖሊስ አስከሬናቸውን ሰጥቷቸው ከቤተሰብ እና ከዘመድ ጋር ለመቅበር ለቀናት አዲስ አበባ ቢቆዩም ምላሽ ሳያገኙ በመቅረታቸው ሐዘናቸው መክበዱን ገልጸው ነበር።

ዛሬ ግንቦት 26/2016 ዓ.ም. ጎንደር ውስጥ አስከሬኑ በሌለበት በባህላዊ መንገድ በቤተሰብ እና በወዳጆች የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ የተፈጸመው የናሁሰናይ አንዳር ጌ ሲሆን፣ በዚህም ወቅት በርካታ ሕዝብ ታድሞ እንደነበር አንድ የቤተሰብ አባል ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የአቤኔዘር ጋሻው የሽኝት ሥነ ሥርዓትም በተመሳሳይ ቤተሰቡ አስከሬኑ ባላገኘበት ሁኔታ ቀደም ብሎ መከናወኑን የቤተሰቡ አባላት ገልጸዋል።

ሚያዝያ 4/2016 ዓ.ም. ፖሊስ የፋኖ ቡድን አባላት ናቸው ያላቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ እና አቤኔዘር ጋሻው ከሀብታሙ አንዳርጌ ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ “የሽበር ጥቃት ለመፈፀም ተልዕኮ ይዘው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የፀጥታ ኃይሉ ደርሶበት” በተደረገ የተኩስ ልውውጥ መገደላቸውን ማስታወቁ አይዘነጋም።

ለሁለት ወራት ለሚጠጋ ጊዜ አስከሬናቸውን ለማግኘት ቤተሰባቸው ለፖሊስ እና ለሚመለከታቸው የፌደራሉ መንግሥት አካላት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያርቡም ምላሽ ሳያገኙ መቅረታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የናሁሰናይ ቤተሰብ እንዳሉት አስክሬን ለማግኘት በአዲስ አበባ ፖሊስ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ድረስ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

“ሁለት ወር ሊሞላው ትንሽ ቀን ነው የቀሩት። ብዙ ደከምን። ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ጠይቀን ምላሽ ስናጣ ተስፋ ቆረጥን።”

የሁለቱን ሟቾች አስከሬን አግኝተው ለመቅበር ቤተሰቦቻቸው ለፌደራል ፖሊስም ሆነ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ላቀረቡት ጥያቄ ሲሰጣቸው የነበረው ምላሽ “እኛን አይመለከትም” የሚል መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።

በዚህም ሳቢያ ቤተሰቡ ለሟቾች ሽኝት ለማድረግ እና እርም ለማውጣት በአካባቢው ‘ደመር’ ተብሎ በሚታወቀው ባህላዊ ሥነ ሥርዓት አማካይነት ሐዘናቸውን ለመወጣት መወሰናቸውን የቤተሰብ አባሉ ገልጸዋል።

በዚህም ለናሁሰናይ አንዳርጌ ዘመድ አዝማድ እና ሌሎች ለቀስተኞች በተገኙበት ዛሬ ሰኞ ግንቦት 26/2016 ዓ.ም. ጉንደር ከተማ ውስጥ በሚገኘው አባ ጃሌ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ፍትሃት እና የሽኝት ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።

ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት የቤተሰብ አባል እና አንድ የጎንደር ከተማ ነዋሪ በከተማው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ተሰማርተው እንደነበር ለቢቢሲ ገልጸዋል።

እንደ ቤተሰብ አባሉ ገለጻ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ለቀስተኛ ካለ አስከሬን በተካሄደው የስንብት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደም ወደ ቤተ-ክርስቲያን እያመራ ሳለ “የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች የናሁሰናይ ፎቶ እና ስም ያለበትን ባነር በኃይል ተቀብለዋል” ብለዋል።

“ፒያሳ አደባባይ ስንደርስ ባነሮቹን አምጡ ሲሉ እኔ እራሴ እንዲወስዱ እንዲፈቀድላቸው አድረግሁ፤ ሁለት ባነሮች ወስደዋል። ከዚህ ውጪ የተፈጠረ ምንም ነገር የለም” ሲሉ አብራርተዋል።

በባነሮቹ ላይ ሰፍሮ የነበረው የናሁሰናይ ሙሉ ስም እና ማዕረግ፣ የትውድ ቀን እና ሕይወቱ ያለፈበት ቀን መሆኑን የቤተሰብ አባሉ ተናግረዋል።

ከናሁሰናይ ጋር አዲስ አበባ ላይ ተገድሎ የነበረው ሌላኛው የፋኖ አባል የአቤኔዘር ጋሻው ተመሳሳይ የደመር ሥነ ሥርዓት ቀደም ብሎ መከናወኑን እኒሁ የቤተሰብ አባል ጨምረው አስታውሰዋል።

ሚያዚያ 4/2016 ዓ.ም. ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ ጋር በተካሄደ የተኩስ ለውውጥ “ፋኖ መሪ ናሁሰናይ አንዳርጌ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ሲሞት፣ አቤኔዘር ጋሻው በተኩስ ልውውጡ ወቅት ተገድሏል” ሲል ፖሊስ መግለጹ ይታወሳል።

አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ ከተገደሉት ሁለቱ በተጨማሪ ሀብታሙ አንድአርጌ የተባለው የቡድኑ አባል ጉዳት ሳይደርስበት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን እና በተኩስ ለውውጡ ወቅት አንድ ግለሰብ መገደላቸውን እንዲሁም ሁለት የፖሊስ አባላት መቁሰላቸው አሳውቆ ነበር።

ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው።
6.4K views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-03 16:22:33
6.0K views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-03 11:32:29 ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በልማት ስራ ምክንያት በከፊል ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ
***
በመንገድ ኮሪደር ልማት እና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
መዚህ መሰረት፡-
- ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
- ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
-ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
እንዲሁም በውስጥ ለውስጥ ወደ ዋናው ቦሌ አየር መንገድ የሚወስዱ መንገዶች ከግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በየዕለቱ የልማት ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከቀኑ 8:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:30 ሰዓት ለተሽከርካሪ በከፊል ዝግ ስለሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዳለባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
6.6K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-30 21:34:47 የድምፃዊት እግቱ ጉዳይ ከምን ደረሰ?
#FastMereja
ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) የደረሰባትን በፋስት መረጃ ካደረስን በኋላ በርካታ ጥያቄዎች ተነስቷል። ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከትራንስፖርት ቢሮ፣ ከባህል እና ቱሪዝም ቢሮ መረጃውን ከተመለከቱ በኋላ ነገሩን ለማጣራት ተደውሎልን ነበር ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ ላደረጋችሁት ተነሳሽነት ፋስት መረጃ ከልብ ያመሰግናል።

እግቱ ምን ደረጃ እንደደረሰች ፋስት መረጃ ድምፃዊቷን ለማውራት ሞክረን ነበር ከፈረስ ጋር እየተነጋገርኩ ነው የደረስኩበትን ነገር አሳውቃለሁ ብላን ነበር።

አሁን ማምሻውን የደረሰችበትን ነገር አሳውቃናለች።

ሙከራውን አምልጣ ቤት እንደገባች መጀመሪያ ወደ ፈረስ ትራንስፖርት ደውላ የደረሰባን ስትነግራቸው ስትሳፈር ኪሎሜትር ስላላስጀመረች ኤቪደንስ ስለሌለ ነገሩን አክብዶታል ብላለች። (መጀመሪያ ከቤት ሲወስዳት በፈረስ ነበር ደውላ የጠራችው ስትመለስ ግን አላስጀመረችም ነበር።)

ከዛ በኋላስ ምን ተፈጠረ?
ፈረስ ትራንስፖርት እና ድምፃዊቷ በአሁኑ ወቅት በመነጋገር አሽከርካሪው ከስራው እንደታገደ እግቱ ለፋስት መረጃ ገልፃለች፣ አሽከርካሪውም ደውሎ እንዳወሩ እና መጀመሪያ ማመን አልፈለገም ነበር ጉዳዩ ሲሪየስ መሆኑን ሲያውቅ ይቅርታ ጠይቆኛል ብላለች።

እኔ ዋና አላማዬ ከእኔ ስህተት ብዙ ሰው እንዲማር ነበር ይፋ ያደረኩት ብላለች። ኮሜንቶቹን በተመለከተ እኔን በመተባበር እንኳን አተረፈሽ ያሉ በርካታ ሰዎች ከልብ አመስግናለሁ። እኔ አሁን በጣም ደህና ነኝ ብላለች።

በጣም የሚያሳዝን ከሰው የማይጠበቅ ሰው እንዴት ሰው ላይ እንደዚህ ይመኛል የሚያስብሉ ኮሜንቶችን ተመልክቻለሁ፣ ሌሎች ሰዎች የደረሰባቸውን ወጥተው እንዳይናገሩ የሚያደርግ ነው፣ በራቸውን የዘጉ ብዙ ነገር የሆኑ አሉ ለእነሱ እንደዚህ መባሉ ጥሩ አይደለም። እኔ ላይ ምንም ለውጥ አያመጣም በማለት አስተያየት ሰጪዎችን በተመለከተ ሃሳቧን ተናግራለች።
***
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja
5.8K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-30 21:34:46
5.3K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-30 18:42:31
ከ1997 ዓም ጀምሮ ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
#FastMereja
ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ ለተለያዩ ግለሰቦች የትምህርት ፣ የልደት ፣ የስራ ልምድ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረረገው ክትትል በመኖሪያ ቤት ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ መምሪያው ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በሚገኘው የግለሰቡ መኖሪያ ቤት ህጋዊ አሰራርን ተከትሎ በተደረገ ብርበራ የ29 የመንግስትና የግል ተቋማት ክብ ማህተሞች፣ ብዛታቸው 26 የልዩ ልዩ የስራ ኃላፊ ቲተሮች ፣ በግለሰቡ አማካኝነት የተዘጋጁ የወሳኝ ኩነት ሰነዶች ፣ የተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ፣ የሰራ ልምድ ፣ የነዋሪነት መታወቂያ ፣ ልዩ ልዩ ደብዳቤዎችና ሰነዶችን በኤግዚቢትነት ይዞ ምርመራው መቀጠሉን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያው አሳታውቋል፡፡

ሀሰተኛ ሰነድ ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት ሆን ተብሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በተለይ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ሀሰተኛ ሰነዶችን እንደሚጠቀሙ የሚታወቅ ነው፡፡ በመሆኑን መንግስታዊ ፣ ግላዊና ሌሎች ተቋማትም ለልዩ ልዩ ጉዳዮች የሚቀርቡላቸውን ሰነዶች እና መታወቂያዎችን ትክክለኝነት የማረጋገጥ ተግባር ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ እና ህብረተሰቡም መሰል ወንጀሎች ሲያጋጥመው ለፖሊስ ጥቆማ የመስጠት ልምዱን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል።
6.1K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ