Get Mystery Box with random crypto!

ሜላት ንጉሴ በምን ምክንያት እንደታሰረች አልታወቀም። #FastMereja በማህበራዊ ሚዲያ | FastMereja.com

ሜላት ንጉሴ በምን ምክንያት እንደታሰረች አልታወቀም።
#FastMereja
በማህበራዊ ሚዲያ የተቸገሩ ወገኖችን ድጋፍ እንዲያገኙ፣ ስራ ፈላጊ እና ድርጅቶችን በማገናኘት ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ከሚጠቀሙ ግለሰቦች መካከል ተጠቃሽ ናት።

ዛሬ ግንቦት 27/2016 ዓም የፀጥታ አካላት በመኖሪያ ቤቷ በመምጣት ይዘዋት ሊሄዱ እንደሆነ በፌስቡክ ገጿ ካስታወቀች በኋላ በርካቶች እንዴት ሆና ይሆን ብለዋል።

ሜላት ንጉሴ በፀጥታ አካላት ከቤቷ ተወስዳ ቀኑን ሙሉ አዲስ አበባ ፖሊስ እንደነበረች በስፍራው ከነበሩ ሰዎች ፋስት መረጃ ሰምቷል ለምን እንደተያዘች የተለያዩ የፀጥታ አካላትን ቢጠይቁም እነሱ እንደማያውቁ እንድትያዝ ብቻ ትዕዛዝ እንተሰጣቸው ገልጿል።

የተያዘችበት ምክንያት እና ክሱን ለማወቅ የተደረገው ሙከራ ዛሬ ሳይሳካ ቀርቷል ያሉት ወዳጆቿ ሜላት ንጉሴ ዛሬ እስር ቤት እንድታድር ሆኗል ብሏል።