Get Mystery Box with random crypto!

በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት እግቱ ገለፀች #FastMereja በሜትር | FastMereja.com

በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት እግቱ ገለፀች
#FastMereja
በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) ገለፀች። ፋስት መረጃ የእግቱን መልዕክት እንደተመለከተው ትላንትና በከተማችን የሚሰራ የሜትር ታክሲ ሹፌር ሊደፍረኝ ነበረ ያለችው ድምፃዊቷ ከቤት ስወጣ ያደረሰኝን ሹፌር አመሻለሁ ሲለኝ ፕሮግራሜን ስጨርስ ቤቴን ስለሚያውቀውም መጀመሪያ በሰላም ስላደረሰኝም ወደ ቤት እንዲመልሰኝ ደወልኩለት ትንሽ ቢያረፍድም መጣ ስትል የተፈጠረውን አብራርታለች።

ቤት ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ መኪናውን አቁሞ ሲታገለኝ እወጋሻለሁ ብሎ ሲያስፈራራኝ፣ አምልጬ ወደ ቤት ገብቻለሁ። ሲታገለኝ ልብሴ ስለተቀደደ ኪሴ ውስጥ የነበረ ገንዘብ ሙሉበሙሉ መኪና ውስጥ ወድቆብኛል ብላለች።

ትማሩበታላችሁ፣ የእኔን ስህተት ተዘናግታችሁ አትደግሙትም ብዬ አምናለሁ ስትል እግቱ የደረሰባትን ገልፃለች።
****
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja