Get Mystery Box with random crypto!

ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በልማት ስራ ምክንያት በከፊል ዝግ እንደሚሆን የአዲ | FastMereja.com

ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ በልማት ስራ ምክንያት በከፊል ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ
***
በመንገድ ኮሪደር ልማት እና የአስፓልት ንጣፍ ስራ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ የሚወስደው ዋናው መንገድ በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
መዚህ መሰረት፡-
- ከለገሐር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
- ከእስጢፋኖስ በቀጥታ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
-ከኡራኤል በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ አየር መንገድ
እንዲሁም በውስጥ ለውስጥ ወደ ዋናው ቦሌ አየር መንገድ የሚወስዱ መንገዶች ከግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በየዕለቱ የልማት ስራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከቀኑ 8:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12:30 ሰዓት ለተሽከርካሪ በከፊል ዝግ ስለሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥማቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዳለባቸው አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡