Get Mystery Box with random crypto!

በኳታር ዶሃ ትልቅ የህክምና ማዕከል የከፈቱት ኢትዮጵያዊው ዶ/ር አማኑኤል ቶሎሳ #FastMereja | FastMereja.com

በኳታር ዶሃ ትልቅ የህክምና ማዕከል የከፈቱት ኢትዮጵያዊው ዶ/ር አማኑኤል ቶሎሳ
#FastMereja
ዶ/ር አማኑኤል ቶሎሳ በ18 አመታቸው ወደ ፊንላድ ሀገር በማቅናት ሚዲካል ስኩል በመግባት ትምህርታቸውን ተከታተሉ፣ ከፊንላድ ወደ ካናዳ፣ ካናዳ እየሰሩ እያሉ ኳታር ሀገር ተጠርተው በኳታር ዶሃ ሰፊ ልምድ ያላቸው እውቅ የአጥንት ቀዶ ህክምና ባለሙያ ለመሆን በቅቷል።

ዶ/ር አማኑኤል ያላቸውን ሰፊ ልምድ በመጠቀም ዶክ ሜዲካል ሴንተር በዶሃ መክፈት የቻሉ ሲሆን። ዶክ ህክምና ላይ ስፔሻላይዝድ አድርጎ የሚሰራ በኳታር ዶሃ የሚገኝ ተዋቂ የጤና አገልግሎት መስጫ ማዕከል ነው። ማዕከሉ በነሃሴ 2002 በአልሳድ ኳታር ተቋቋመ። በተጨማሪ የDOC ዳያግኖስቲክ እና ኢሜጂንግ ማዕከልን በመስከረም 2015 አቋቁሟል:: ማዕከሉ በስራ ከ150 በላይ ሠራተኞችን ቀጥሮ በማሰራት ላይ ይገኛል።

ዶ/ር አማኑኤል ቶሌሳ በአጽንኦት እንደሚገልጹት ማዕከሉ ሁለንተናዊ የጤና አጠባበቅ ሁኔታን ከዘመናዊ የህክምና ተግባራት እና ከባህላዊ ህክምናዎች ጋር አጣምሮ የያዘ ነው። ማዕከሉ የኳታርን ማህበረሰብ እና የጂሲሲ ነዋሪዎችን ባህል እና ፍላጎታቸውን በጠበቀ መልኩ በልዩ እንክብካቤ የህክምና ፍላጎቶች ለማሟላት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ዶክ ሕክምና ማዕከል ኦርቶፔዲክስ እና ትራማቶሎጂ፣ የሩማቶሎጂ፤የውስጥ ሕክምና፤ የቤተሰብ ሕክምና፤መልሶ ማቋቋም እና ማገገም፤ ዲያጎነስቲክ ኢሜጂንግ እና የላቦራቶሪ አገልግሎቶች ጨምሮ በርካታ ህክምናዎች በማዕከሉ ይሰጣል።

ዶ/ር አማኑኤል ቶሎሳ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ ያለው የህክምና አገልግሎት እንደሚያስፈልግ በመገንዘብ እነዚህን አገልግሎቶች በህክምና ቱሪዝም ለወገኖቻቸው ለማዳረስ አላማ አንግበው ተነስተዋል። ይህ ፕሮግራም ከኢትዮጵያው ወደ ኳታር ሄደው መታከም ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን ፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ ኢንሹራንስ ላላቸው ታካሚዎች እና የንግድ ተጓዦች በኳታር ከፍተኛ ደረጃ የአጥንት ህክምና እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የዶክ ሜዲካል ሴንተር ቢሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሲሆን ከእነርሱም መካከል በኢትዮጵያ ስመጥር በሆኑ የአጥንት ስፔሻሊስቶች የታገዘ የምክር አገልግሎት፣ ወረቀት ስራዎችን የቪዛ ሂደቶችን የኤርፖርት ዝውውሮችን እና ከመስተንግዶ ጋር የተያያዙ እገዛዎችን ይገኙበታል::

ታካሚዎች ወደ ኳታር ዶሃ ሲሄዱ በማዕከሉ ቋንቋ ችግር እንዳይገጥማቸው በሀገራቸው ቋንቋ እንዲስተናገዱ ሁኔታዎችን አመቻችቷል።

ጥላሁን ደሳለኝ