Get Mystery Box with random crypto!

ከ1997 ዓም ጀምሮ ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አዲስ አበ | FastMereja.com

ከ1997 ዓም ጀምሮ ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ የነበረ ግለሰብ ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
#FastMereja
ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ ለተለያዩ ግለሰቦች የትምህርት ፣ የልደት ፣ የስራ ልምድ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረረገው ክትትል በመኖሪያ ቤት ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጅ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ መምሪያው ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በሚገኘው የግለሰቡ መኖሪያ ቤት ህጋዊ አሰራርን ተከትሎ በተደረገ ብርበራ የ29 የመንግስትና የግል ተቋማት ክብ ማህተሞች፣ ብዛታቸው 26 የልዩ ልዩ የስራ ኃላፊ ቲተሮች ፣ በግለሰቡ አማካኝነት የተዘጋጁ የወሳኝ ኩነት ሰነዶች ፣ የተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ፣ የሰራ ልምድ ፣ የነዋሪነት መታወቂያ ፣ ልዩ ልዩ ደብዳቤዎችና ሰነዶችን በኤግዚቢትነት ይዞ ምርመራው መቀጠሉን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያው አሳታውቋል፡፡

ሀሰተኛ ሰነድ ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት ሆን ተብሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በተለይ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ሀሰተኛ ሰነዶችን እንደሚጠቀሙ የሚታወቅ ነው፡፡ በመሆኑን መንግስታዊ ፣ ግላዊና ሌሎች ተቋማትም ለልዩ ልዩ ጉዳዮች የሚቀርቡላቸውን ሰነዶች እና መታወቂያዎችን ትክክለኝነት የማረጋገጥ ተግባር ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባ እና ህብረተሰቡም መሰል ወንጀሎች ሲያጋጥመው ለፖሊስ ጥቆማ የመስጠት ልምዱን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል።