Get Mystery Box with random crypto!

የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ** 1445ኛው የኢድ አል | FastMereja.com

የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች
**
1445ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ይከበራል።

በዕለቱ በአዲስ አበባ ስታዲዮም እና በዙሪያው በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የሶላት ስነ-ስርዓት ይካሄዳል።

ፕሮግራሙ በሚካሄድበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ የተዘረዘሩት መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፦

• ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ

• ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው አጎና ሲኒማ ላይ

• ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ

• ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ

• ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

• ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ 22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ

• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ

• ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ አቧሬ ሴቶች አደባባይ ላይ

• ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

• ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ

• ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

• ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ አጠገብ

• ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ

• ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ

• ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ

መንገዶቹ ከሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ሶላቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙሟቸው አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

ለእምነቱ ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የፍቅርና የሰላም እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።