Get Mystery Box with random crypto!

በ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ 3 ጨዋታዎች ይደረጋሉ አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

በ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ 3 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024 የአውሮፓ ዋንጫ መርሐ-ግብር ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

በዚህም ቀን 10 ሠዓት ላይ በምድብ አራት የተደለደሉት ፖላንድ እና ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ይጫወታሉ፡፡

እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት በምድብ ሦስት የሚገኙት ስሎቬኒያ ከዴንማርክ እና ምሽት 4 ሠዓት ላይ ሰርቢያ ከእንግሊዝ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ከትናንት በስቲያ ዓርብ ምሽት የጀመረ ሲሆን እስከ አሁን በተካሄዱት ጨዋታዎችም÷ ጀርመን ስኮትላንድን 5 ለ 1፣ ስዊዘርላንድ ሀንጋሪን 3 ለ 1፣ ስፔን ክሮሽያን 3 ለ 0 እንዲሁም ጣልያን አልባኒያን 2 ለ 1 ረትተዋል፡፡