Get Mystery Box with random crypto!

የኢድል አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የኢድ ሶላት በመዲናዋ በደመቀና ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መል | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

የኢድል አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የኢድ ሶላት በመዲናዋ በደመቀና ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ መጠናቀቁን የጋራ ግብረ-ሃይሉ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1445ኛው የኢድል አል አድሃ (አረፋ) በዓል የኢድ ሶላት በአዲስ አበባ በደመቀና ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ሃይል አስታውቋል፡፡

የኢድ ሶላት በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች በታደሙበት እጅግ በደመቀና በዓሉን በሚመጥን ሃይማኖታዊ ሥርዓት መጠናቀቁን ነው የጋራ ግብረ-ሃይሉ የገለጸው፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስቀድሞ የተደረገውን ዝግጅት የሚመጥን የተግባር አፈፃፀም ላሳዩ መላው የፀጥታ አካላትን አመስግኗል፡፡

እንዲሁም ለበዓሉ ሠላማዊነት ለፀጥታ ሐይሉ ሥራ ተባባሪ በመሆን የድርሻቸውን ለተወጡ የዕምነቱ ተከታዬችና ለሰላም ወዳዱ የከተማው ነዋሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል ምስጋና አቅርቧል፡፡

የጋራ ግብረ-ሃይሉ ለመላው የዕምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅር፣ የሠላም፣ የጤና እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።