Get Mystery Box with random crypto!

ወላይታ ድቻ ከመመራት ተነስቶ ሀድያ ሆሳዕናን አሸነፈ አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ | FBC (Fana Broadcasting Corporate)

ወላይታ ድቻ ከመመራት ተነስቶ ሀድያ ሆሳዕናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ27ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ከመመራት ተነስቶ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ሀድያ ሆሳዕና በመጀመሪያው አጋማሽ በተመስገን ብርሃኑ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 እየመራ ወደ መልበሻ ክፍል አምርቷል፡፡

ከዕረፍት መልስ በአብነት ደምሴ ጎል አቻ መሆን የቻለው ወላይታ ድቻ÷ ብሩክ ማርቆስ በ83ኛው ደቂቃ በራስ ላይ ባስቆጠራት ግብ ተጋጣሚውን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የፕሪሚየር ሊጉ ቀሪ መርሐ-ግብር ሲቀጥል÷ 12 ሠዓት ላይ ሻሸመኔ ከተማ ኢትዮጵያ መድንን ይገጥማል፡፡