Get Mystery Box with random crypto!

ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የሰርጥ አድራሻ: @bolecommunication
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 911

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-28 19:00:21
በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙ መምህራን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው።

በክፍለ ከተማው በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን በተለያዩ አገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰባት ክላስተሮች ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

ሚያዚያ 20/2015
መረጃዎቻችንን በአማራጭ ለማግኘት: -
በፌስቡክ፡ www.facebook.com/bolecommunication
በትዊተር: twitter.com/bole_comm
በዩቲዩብ: https://www.youtube.com/channel/UCTc1t2_k9iNhr80vlG5zMJg
ኢንስታግራም: instagram.com/bole_communication
94 views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 12:47:00
159 views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 12:47:00
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በመካሄድ ላይ ነው ።

የክፍለ ከተማውና የአሥራ አንዱም ወረዳዎች አመራሮች በተሳተፉበት በዚህ የግምገማ መድረክ በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ሪፖርቶች የቀረቡ ሲሆን፣ በሪፖርቶቹ መነሻነት ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ እንዲሁም በቀጣይ ሥራዎች አፈጻጸም አቅጣጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል ።

ሚያዚያ 19/2015
መረጃዎቻችንን በአማራጭ ለማግኘት: -
በፌስቡክ፡ www.facebook.com/bolecommunication
በትዊተር: twitter.com/bole_comm
በዩቲዩብ: https://www.youtube.com/channel/UCTc1t2_k9iNhr80vlG5zMJg
ኢንስታግራም: instagram.com/bole_communication
157 views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:52:18
"ጦርነት ይብቃ፣ ሰላምን እናጽና" የምስጋና እና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነዉ

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ግጭት በሰላም ስምምነቱ እልባት እንዲያገኝ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የማመስገንና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ በመካሄድ ላይ ነው።

በመረሀ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት፣ የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ሚያዚያ 15/2005
126 views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:42:31
110 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:42:31
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጄኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ያሠራው ፓርክ እና ሀውልት በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመረቀ።

ለቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ሰዓረ መኮንን በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ የተሰራላቸው የመታሰቢይ ሐውልት ዛሬ ተመርቋል፡፡ በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ "በቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ በጀኔራል ሰዓረ መኮንን ስም ያስገነባነውን ፓርክ እና የመታሰቢያ ሀውልት ስናስመርቅ ከታሪኩ ቀጣዩ ትውልድ እንዲማርበት ሲሆን መሰዋቱ ቢያስቆጨንም የተሰዋለት ዓላማ ታላቅና ትውልድ የሚታነጽበት ሕያው ታሪክ ነውና እንጽናናለን" ብለዋል ።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ የጀኔራል ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦች እንዲሁም የጀኔራል ሰዓረ የቀድሞ ባልደረቦች ተገኝተዋል፡፡

ሚያዚያ 14/2005
115 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:16:21 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እና
የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች ፣

እንኳን ለ1,444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የረመዳን ጾም ሙስሊሞች በትህትናና በፍጹም መታዘዝ በፈጣሪ ፊት የሚቀርቡበትና መልካምነትን በተግባር የሚፈጽሙበት ቅዱስ ወር ነው። ይህንን የተቀደሰ ወር በዱአና በመልካም ተግባራት በማሳለፍ እነሆ ለረመዳን ጾም ፍቺ ዋዜማ ደርሰናል።

የኢድ አልፈጥርን በዓል ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንን ባለን አቅም መደገፍና አይዟችሁ ማለት ይኖርብናል ። ከዚህ አንፃር በክፍለ ከተማችንና በአሥራ አንዱም ወረዳዎቻችን ለ7,000 ወገኖቻችን ማዕድ ያጋራን ሲሆን፣ ሕዝበ ሙስሊሙም ይህንን የበጎነት ተግባር በየአካባቢው በማከናወን በጎነትን በተግባር ማሳየት ይጠበቅበታል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት በዓል እንዲሆን ያለኝን ልባዊ ምኞት በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስም እገልፃለሁ።

ኢድ ሙባረክ!

ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ሚያዚያ 12/2015
111 views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:15:52
100 views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:09:53
80 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:09:48
76 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ