Get Mystery Box with random crypto!

ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የሰርጥ አድራሻ: @bolecommunication
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 911

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-04-20 20:08:35 “ወገናዊ አጋርነት፣
በበዓል ዋዜማ!”
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 1444ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓል በማድረግ ለአቅመ ደካማ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ፡፡
በክፍለ ከተማውና በሁሉም ወረዳዎች በአጠቃላይ ለ7,000 አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የበዓል መዋያ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር የተካሄደ ሲሆን፣ በክፍለ ከተማ ደረጃ በተካሄደው የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው ባደረጉት ንግግር አስተዳደሩ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር አቅመ ደካማ ወገኖች በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩ ለማስቻል የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩን በማዘጋጀቱ ደስታ እንደሚሰማው አመልክተዋል፡፡ የፆም ወቅት ምዕመናን ፈጣሪያቸውን በጸሎት የሚለምኑበት ጊዜ መሆኑን ያወሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ በበዓሉ የተቸገሩ ወገኖችን ማገዝና አብሮነትን በተግባር ማሳየት ከሁሉም እንደሚጠበቅ አክለው አስገንዝበዋል፡፡
የክፍለ ከተማው አስተዳደር ባለፈው ሳምንት የተከበረውን የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ተመሳሳይ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ማካሄዱን ያስታወሱት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አየሉ ጎሹ በበኩላቸው የተለያዩ አካላትን በማስተባበር ለበዓል መዋያ የሚውሉ የምግብ ግብዓቶች ለአቅመ ደካማ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ከመደረጉ ባሻገር የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የቦሌ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍም ለአቅመ ደካማ ወገኖች የበዓል መዋያ የሰንጋ ስጦታ ማበርከቱን አክለው አስታውቀዋል፡፡
ሚያዚያ 12/2015
58 views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:01:21
43 views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:01:02
39 views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 19:54:37 የተከበራችሁ የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች
እና
መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የክርስትና አስተምህሮ እንደሚያስረዳን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሕይወቱን የሰጠው ስለሰው ልጅ ፍጹም ፍቅር ነው፡፡ የስቅለቱና የትንሣኤው ዓላማ እኛም አርአያነቱን ተከትለን በፍቅር እንድንኖርና መስጠትን የሕይወታችን አካል እንድናደርግ ነው፡፡

የስቅለትና የትንሣኤ በዓላት የመስዋዕትነት፣ የይቅርታ፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ በአጠቃላይ ውብ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን ይበልጥ ከሚያጎሉና ከሚያደምቁ በዓላት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም የአብሮነት መንፈስ እንዲሆን ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ ወደ ምድር ስንመጣ ንጹሕ ሆነን እንደተፈጠርን ሁሉ በንጽሕናና በቅንነት መኖር እና ሕዝባችንን በሀቅ ማገልገል እንደሚኖርብን አደራ እያልኩ፣ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ እንዲሁም የአብሮነት እንዲሆን ያለኝን ልባዊ ምኞት በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስም እገልጻለሁ፡፡

መልካም በዓል!

ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ሚያዚያ 7/2015
112 viewsedited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 19:54:35
100 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 15:24:02 የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማው ነዋሪ የሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖችን ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ በቅርቡ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በ90 ቀናት ዕቅድ ባስገነባቸው የአቅመ ደካማ መኖሪያ ሕንፃዎች ውስጥ ቤት የተሰጣቸውና በሕመም ላይ የሚገኙ ወገኖች የተጎበኙ ሲሆን፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ለነዋሪዎቹ የበዓል ስጦታ አበርክተውላቸዋል፡፡
ሚያዚያ 7/2015
100 views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 15:23:49
85 views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 15:19:36
"ልዩ ዓርብ_በቦሌ!"
የዛሬዋ ዓርብ፣ ለኢትዮጵያዊያን ልዩ ዕለት ናት። የሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች ተከታዮች በአንድ ጊዜ ፈጣሪያቸውን በስግደትና በጸሎት የሚያስቡባትና የሚለምኑባት ዓርብ።
የክርስትና እምነት ተከታዮች የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በአብያተ ክርስቲያናት በስግደትና በጸሎት ያከበሩ ሲሆን፣ የእስልምና እምነት ተከታዮችም የጁምአ ሶላትን በመስጅዶች አካሂደዋል።
ሚያዚያ 6/2015
68 views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 15:04:16
48 views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 15:04:15
38 views12:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ