Get Mystery Box with random crypto!

ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የሰርጥ አድራሻ: @bolecommunication
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 911

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-01-11 15:05:45
117 views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 09:29:59
150 views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 09:29:57 “ሀብታችንን፣
ዕውቀታችንን
ያለምንም ስስት
የአንድነታችን መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ እናውላለን”

“ቦሌ 5150” በሚል ስያሜ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ የጎዳና ላይ የዱላ ቅብብል ሩጫ ማዘጋጀቱን የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

መርሐ ግብሩን አስመልክቶ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመላው ኢትዮጵያዊያን የአንድነትና የልማት መገለጫ የሆነ አገራዊ ፕሮጀክት መሆኑን አውስተው፣ ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት ዕውን ለማድረግ የቦሌ ክፍለ ከተማ ባለፉት ጊዜያት በሀብት ማሰባሰብ ዘርፍ ሰፊ ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡ በ2014 በክፍለ ከተማው ለግድቡ ግንባታ ሀብት ለማሰባሰብ የተያዘው ዕቅድ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ያመለከቱት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ በ2015 በጀት ዓመትም የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ አዳዲስ መንገዶችን በመቀየስ አስተዳደሩ እየሠራ መሆኑንና የ “ቦሌ 5150” የጎዳና ላይ የዱላ ቅብብል ሩጫም የዚህ ተግባር አንድ አካል መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ታደሰ በበኩላቸው “ሀብታችንን፣ ዕውቀታችንን ያለምንም ስስት የአንድነታችን መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ እናውላለን” በሚል መሪ ቃል ጥር 28 ቀን 2015 በዓይነቱ ልዩ የሆነ የጎዳና ላይ የዱላ ቅብብል ሩጫ እንደሚካሄድ ገልጸው፣ የውድድሩ መጠሪያ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ ሥራ ሲጀምር የሚያመነጨውን 5,150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን መሠረት በማድረግ 5,150 ሜትር የሚሸፍንና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚያሳትፍ ውድድር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ከዱላ ቅብብሉ ጎን ለጎን ድርጅቶች፣ ባለሀብቶች እንዲሁም መላው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ቦንድ በመግዛት እንዲሳተፉ እንደሚደረግ የገለጹት ኃላፊው፣ በዚህ በይዘቱ የመጀመሪያ በሆነው የዱላ ቅብብል ሩጫና ተያያዥ መርሐ ግብሮች በበጀት ዓመቱ ከክፍለ ከተማው ለመሰብሰብ የታቀደውን ሀብት ለማሳካት መላው የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችና የተለያዩ አጋር አካላት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጥር 1/2015
149 viewsedited  06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 11:45:56
230 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 11:45:43
222 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 06:36:25 እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ለሰው ልጆች የመዳን የምሥራች የተበሰረበት ታላቅ ዕለት ነው። ልደት የሚከበርበት የገና በዓል የመሰባሰብ፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ በዓል ሆኖ በድምቀት ይከበራል።

በገና በዓል ድጋፍ የሚፈልጉ ወገኖቻችንን ማገዝና አለንላችሁ ማለት ይኖርብናል። ከዚህ አንፃር የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማው ለሚኖሩ አቅመ ደካማ ወገኖች የማዕድ ማጋራትና የቤት ስጦታን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን አበርክቷል። በዚህ ድጋፍ ውስጥ አጋርነታችሁን ላሳያችሁን ባለሀብቶችና ተቋማት፣ ድጋፉን ላስተባበሩ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እና ባለሙያዎች በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

በዓሉን በደስታ ለማክበር ሰላም ወሳኝ ነው። በመሆኑም በበዓሉ ወቅት ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ለመከላከል የጸጥታ አካላት፣ የክፍለ ከተማችን የሰላም ሠራዊት እና መላው ነዋሪ ኅብረተሰብ ተቀናጅተው የሰላም ዘብነታቸውን በተለመደው ተነሳሽነት አጠናክረው እንዲቀጥሉ አደራ ለማለት እወዳለሁ።

መልካም በዓል!

ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ
113 views03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 06:36:09
109 views03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 16:05:26
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ያዘጋጀው የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም የፎቶ ዐውደ ርእይ ተከፈተ።
ዐውደ ርዕዩን የከፈቱት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው ባደረጉት ንግግር የክፍለ ከተማው አስተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት በልማት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በልዩ ልዩ ዘርፎች መጠነ ሰፊ ተግባራትን ማከናወኑን አውስተው፣ የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት እነዚህን ተግባራት ክፍት ዐውደ ርዕዩን በዝግጅት ኅብረተሰቡ ሥራዎቹን እንዲያውቃቸው በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።
በፎቶግራፍ ዐውደ ርዕዩ የአስተዳደሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ለዕይታ መቅረባቸውን የተናገሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ተክሌ በበኩላቸው ዐውደ ርዕዩ ኅብረተሰቡ የተከናወኑ ሥራዎችን እንዲመለከትና ግንዛቤ እንዲጨብጥ በማድረግ በኩል የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል።
ታኅሳስ 27/2015
114 views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 15:26:47
“ከተባበርንና ከተሳሰብን የማንወጣው ችግር የለም”
ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማው የሚኖሩ አቅመ ደካማ ወገኖችን መኖሪያ ቤቶች በማደስ አስረከበ፡፡

በክፍለ ከተማው በሚገኙ ወረዳዎች በባለሀብቶችና በተቋማት ድጋፍ የታደሱት ቤቶች የቁልፍ ርክክብ በተካሄደበት ወቅት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው ባደረጉት ንግግር በበጎ ፍቃደኞች ትብብር ታድሰው ለአገልግሎት የበቁት መኖሪያ ቤቶች ለኑሮ አመቺ ያልሆኑ እንደነበሩ አውስተው፣ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ችግር ለማቃለል በጎ ፍቃደኞች፣ ባለሀብቶችና ድርጅቶች ከክፍለ ከተማውና ከወረዳዎች ጎን በመቆም ላበረከቱት ቀና አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ “ከተባበርንና ከተሳሰብን የማንወጣው ችግር የለም” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ አሁንም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ በርካታ ዜጎች በመኖራቸው ኢትዮጵያዊ የመተጋገዝ ባሕልን በማጠናከር ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፉ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቤቶቻቸው የታደሱላቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው ችግራቸውን ተመልክተው የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ በገንዘባቸውና በጉልበታቸው ድጋፍ ላደረጉላቸው በጎ አድራጊዎች እንዲሁም ለቦሌ ክፍለ ከተማና ለወረዳዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ታኅሳስ 27/2015
116 views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 13:39:57
ቦሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት የገና በዓል ማዕድ ማጋራት ቅድመ ዝግጅት
194 views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ