Get Mystery Box with random crypto!

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ያዘጋጀው የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወራት | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ያዘጋጀው የ2015 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም የፎቶ ዐውደ ርእይ ተከፈተ።
ዐውደ ርዕዩን የከፈቱት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው ባደረጉት ንግግር የክፍለ ከተማው አስተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት በልማት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በልዩ ልዩ ዘርፎች መጠነ ሰፊ ተግባራትን ማከናወኑን አውስተው፣ የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት እነዚህን ተግባራት ክፍት ዐውደ ርዕዩን በዝግጅት ኅብረተሰቡ ሥራዎቹን እንዲያውቃቸው በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።
በፎቶግራፍ ዐውደ ርዕዩ የአስተዳደሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ለዕይታ መቅረባቸውን የተናገሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ተክሌ በበኩላቸው ዐውደ ርዕዩ ኅብረተሰቡ የተከናወኑ ሥራዎችን እንዲመለከትና ግንዛቤ እንዲጨብጥ በማድረግ በኩል የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል።
ታኅሳስ 27/2015