Get Mystery Box with random crypto!

ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የሰርጥ አድራሻ: @bolecommunication
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 911

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-12-22 15:29:41
158 views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 15:28:41
158 views12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 09:22:16
161 views06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 09:22:16
159 views06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 09:22:08 በቦሌ ክፍለ ከተማ የጸጥታ ሁኔታ ዙሪያ ያተኮረ ግምገማ ተካሄደ፡፡

የክፍለ ከተማ አስተዳደሩና የሁሉም ወረዳዎች አመራሮች በተሳተፉበት በዚህ ግምገማ በተለይም በትምህርት ቤቶች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል በአመራሩ፣ በኅብረተሰቡ እና በጸጥታ መዋቅሮች በመከናወን ላይ ባሉ ተግባራትና በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው በሚገቡ ሥራዎች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል ለማስቻል በየወረዳዎቹ የሕዝብ ውይይቶች መካሄዳቸውን በግምገማ መድረኩ ላይ የገለጹት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው፣ ከውይይቶቹ የተገኘውን ግብዓት በመውሰድ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንቅስቃሴ ለማክሸፍ ሁሉም አመራር በከፍተኛ ቁርጠኝነት የመሪነት ሚናውን በበለጠ መወጣት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡

ታኅሳስ 6/2015
132 views06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 16:58:01 “ሰላም ከሌለ አገር ተረካቢ ዜጋ መፍጠር አንችልም” ያሉት የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጡማ አህመድ በበኩላቸው ትምህርት ቤቶች የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ እንዳይሆኑ ከቤተሰብ ጀምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት እንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡

ታኅሳስ 6/2015
212 views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 16:57:57
“ሰላምን ለማረጋገጥ የምክር ቤት አባላት
የሕዝብ ተወካይነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል”

የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡

በውይይቱ ላይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ መሥፍን ኃይሌ ባደረጉት ንግግር ኅብረ ብሔራዊነት የኢትዮጵያዊያን አንዱ መገለጫ መሆኑን አውስተው፣ “የአንዱ መኖር ለሌላው ዋስትና እንጂ ሥጋት አይደለም” ብለዋል፡፡ አንዳንድ አካላት የሕዝቡን በሰላምና በአብሮነት የመኖር እሴቶች ለመናድ እያደረጉ ያሉት አፍራሽ እንቅስቃሴ ሊወገዝ የሚገባው መሆኑን የተናገሩት አፈ ጉባኤው፣ በተለይ ትውልድ በሚታነጽባቸው ትምህርት ቤቶች የሚራገቡ ፖለቲካዊ አጀንዳዎችን በመከላከል ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር እና አጠቃላይ ሰላምም እንዲረጋገጥ የምክር ቤት አባላት ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡


በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት አዲስ አበባ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ከተማ መሆኗን ሁሉም አካል አምኖ መቀበል እንዳለበት ገልጸው፣ ፖለቲካዊ አጀንዳዎችን በትምህርት ቤቶች ለማራመድ የሚደረገው ሙከራ ትክክል አለመሆኑንና ይህንን በሚያደርጉ አካላት ላይ ተገቢው ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የፍትህ አካላትና በየደረጃው የሚገኙ አደረጃጀቶች ተግባራቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባቸው ያሳሰቡት አባላቱ፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና አጠቃላይ ማኅበረሰቡን ያሳተፉ የውይይት መድረኮችን እስከ ብሎክ ድረስ በማካሄድ ችግሮች በግልጽ ቀርበው ምላሽ የሚያገኙበትን መንገድ መፍጠር ብሎም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ምላሽ እንዲያገኙ መሥራት የመንግሥት ተግባር ሊሆን እንደሚገባ አክለው ተናግረዋል፡፡
205 views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 11:36:32
121 views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 11:36:29
115 views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 11:36:23
93 views08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ