Get Mystery Box with random crypto!

ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የሰርጥ አድራሻ: @bolecommunication
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 911

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-02-02 10:02:48
190 views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 10:02:47
192 views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 10:01:52 “ኅብረብሔራዊ አንድነትን አጠናክሮ ለማስቀጠል
ኅብረተሰቡ በባለቤትነት መሳተፍ ይኖርበታል!”

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ አገራዊና ክፍለ ከተማ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ከክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ከአሥራ አንዱም ወረዳዎች የተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተሳተፉበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በቀረበው የውይይት መነሻ ሰነድ ላይ እንደተገለጸው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት በሰላምና ጸጥታ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል፣በልዩ ልዩ ዘርፎች የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች እንዲሁም በሰው ተኮርና የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በርካታ ሥራዎችን ያከናወነ ሲሆን፣ መንግሥት እንደ ከተማም ሆነ እንደአገር በርካታ ጠቀሜታዎችን የሚሰጡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እያከናወነ ባለበት ወቅት የኢትዮጵያን ብልጽግና የማይሹ ኃይሎች በየአቅጣጫው አጀንዳ በመፍጠር ማኅበረሰቡ በእምነት፣ በዘር፣ በቋንቋ እና በሌሎች ጉዳዮች እንዲከፋፈል የሚያደርጉትን ሴራ በማክሸፍ ረገድ በክፍለ ከተማው በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸው ተመልክቷል፡፡ በተለይም የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ነዋሪው የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኝ፣ የልማት ፍሬዎች ተቋዳሽ እንዲሆንና ሁለንተናዊ ብልጽግና እንዲረጋገጥ በመደበኛና በ90 ቀናት ዕቅድ አመርቂ ተግባራት መከናወናቸወ በሰነዱ ተወስቷል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በክፍለ ከተማውና በወረዳዎች በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን አውስተው፣ ለዚህ ስኬት መመዝገብ የአመራሩና የነዋሪው ቅንጅት ከፍተኛ ሚና እንደነበረው ተናግረዋል፡፡ የሰላም ጉዳይ ከማንኛውም ጉዳይ የሚበልጥ አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነ የተናገሩት ተሳታፊዎች፣ በመሆኑም መንግሥት ሰላምን የማስከበር ኃላፊነቱን በቁርጠኝነት ሊወጣ እንደሚገባው በመግለጽ፣ ያልተፈቱ የመሠረተ ልማት፣ የሰነድ አልባና መሰል ችግሮች መፍትሄ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ውይይቱን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ የክፍለ ከተማው አስተዳደርና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ በርካታ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን አውስተው፣ በሂደቱ የነበሩ ጥንካሬዎችና ድክመቶችን በመለየት በቀጣይ ወራት ኅብረተሰቡን ሊያረካ የሚችል አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ “እንደአገር ያጋጠመንን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመረዳት አገራዊ ለውጡ ያለፈበትን መንገድ መለስ ብሎ መመልከት ያስፈልጋል” ያሉት አቶ ጥራቱ፣ ፈተናዎችን በድል ለመወጣትና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ኅብረተሰቡ በባለቤትነት መሳተፍ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡ ከነዋሪዎች የተነሱ ልዩ ልዩ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት አስተዳደሩ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝም አቶ ጥራቱ አክለው አስታውቀዋል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው በበኩላቸው አስተዳደሩ በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸው፣ ሰላምን የማይሹ ኃይሎች በተለያየ መንገድ የአገርን ሰላም ለማደፍረስ ያደረጉት ሙከራ በክፍለ ከተማው እንዳይሳካ ኅብረተሰቡ ከጸጥታ አካሉና ከሰላም ሠራዊት ጋር ተቀናጅቶ ባደረገው ርብርብ የክፍለ ከተማው ሰላም እንዲጠበቅ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል፡፡ ለሰላም መደፍረስና ለብልሹ አሠራር መንስኤ የሚሆኑ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶችን በማስወገድ የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ይረጋገጥ ዘንድ የነዋሪው ኅብረተሰብ ሚና ወሳኝ በመሆኑ ይህ ቅንጅታዊ ተግባር የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አሳስበዋል፡፡

ጥር 24/2015
187 views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 07:58:33 እናመሰግናለን!

የከተራና የጥምቀት በዓላት በቦሌ ክፍለ ከተማ በሰላም ተከብረው ተጠናቅቀዋል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። በእነዚህ ሥራዎች ሰላማዊ የበዓል አከባበር ድባብ እንዲኖር የተቀናጀ እንቅስቃሴ በመደረጉ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር ሊከበር ችሏል።

ለዚህ ስኬት የሃይማኖት አባቶች፣ የቤተ ክርስቲያን አካላት፣ የክፍለ ከተማችን የሰላም ሠራዊት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የጸጥታ አካላትና መላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች እንዲሁም የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስም ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፣ እንደሁልጊዜው ሁሉ ሰላማችንን በአስተማማኝ ደረጃ ለማረጋገጥ አብሮነታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አደራ ለማለት እወዳለሁ።

ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ጥር 12/2015
251 viewsedited  04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 07:58:13
242 views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 12:29:54 የተከበራችሁ የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች፣
አርሶ አደሮች፣
ወጣቶች፣
ሴቶች፣
ባለሀብቶች፣
እንኳን ለከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የጥምቀት በዓል አገራችን ኢትዮጵያ ለዓለም ካበረከተቻቸው ታላላቅ ባሕላዊ ቅርሶች መካከል አንደኛው ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የባሕልና የሳይንስ ድርጅት (ዩኔስኮ)ም ይህንን ታላቅ በዓል በዓለም የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ውስጥ መዝግቦታል፡፡
ይህ ታላቅ በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያዊያን የጋራ በዓል ነው፡፡ በዚህ በዓል ከኢትዮጵያዊያን ባሻገር ከመላው ዓለም የሚመጡ ቱሪስቶችና ሚዲያዎች ወደአገራችን በብዛት የሚጎርፉበትና የሚታደሙበት በመሆኑ ለአገራችን የገጽታ ግንባታ እና ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ በእጅጉ ከፍተኛ ነው፡፡
ዘንድሮም የከተራና የጥምቀት በዓልን በታላቅ ድምቀት ለማክበር በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ በክፍለ ከተማችንም በዓሉ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከባለድርሻ አካላትና ከመላው ሕዝባችን ጋር በጥምረት እየሠራ ይገኛል፡፡

የጥምቀት በዓል ሕዝባዊ የአደባባይ በዓል ነው፣ በመሆኑም በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ሁላችንም የጋራ ኃላፊነት አለብን፡፡ በዘንድሮው በዓል የአገራችንን ሰላም የማይሹ ኃይሎች እኩይ ዓላማቸውን በበዓሉ ወቅት ለማስፈጸም ሙከራዎችን ማድረጋቸው አልቀረም፡፡ መንግሥት እነዚህን የሰላም ማደፍረስ ሙከራዎች በብቃት የማክሸፍ ሥራዎችን እያከናወነ ሲሆን፣ በክፍለ ከተማችንም መሰል ተግባራትን ለመፈጸም የሚደረጉ ሙከራዎች በሰላም ወዳዱ ሕዝባችንና በጸጥታ አካላት የተቀናጀ ርብርብ እየከሸፉ ይገኛሉ፡፡
ሰላማችንን ማስጠበቅ የጋራ ኃላፊነታችንን ነው፡፡ ልማትና ብልጽግናችን ዕውን የሚሆነው ሰላም ሲሰፍን በመሆኑ የጥምቀትን በዓል ስናከብር ሰላማችንን ለመጠበቅ ዘብ ልንቆም ይገባል፡፡ በመሆኑም መላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሰላም ሠራዊት፣ እንዲሁም የክፍለ ከተማችንና የወረዳዎቻችን አመራሮች በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በባለቤትነት መንፈስ እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም ድርሻችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ
264 viewsedited  09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 12:29:54
222 views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 10:37:14
247 views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 10:37:06
213 views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 15:06:03 “ሰላማችንን ማረጋገጥ ቁልፍ ተግባራችን ነው!”

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የክፍለ ከተማውን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ በከፍተኛ ትኩረት በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ አስተዳደሩ የሰላምና ጸጥታ ዘርፉን፣ አመራሩን፣ የጸጥታ አካላትን እና የሰላም ሠራዊትን በማቀናጀት ባከናወነው ሰላምን የማረጋገጥ ቁልፍ ተግባር ባለፉት ጊዜያት እንደ አገር ያጋጠሙ የጸጥታ ሥጋቶች በክፍለ ከተማው እንዳይከሰቱ ያስቻለ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ጸረ ሰላም ኃይሎች የከተማችንን ብሎም የአገራችንን ሰላም አደጋ ላይ ለመጣል የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ሰላም ወዳዱ ሕዝባችን እነዚህን ሙከራዎች ለማክሸፍ ከጸጥታ አካሉ ጋር በመተባበር ለሰላም ዘብ በመቆሙ እነዚህ ሙከራዎች ሳይሳኩ ቀርተዋል፡፡ ለዚህ ስኬት የሕዝባችን ተሳትፎ የሚደነቅና ሊመሰገን የሚገባው ነው፡፡

እነዚህ ኃይሎች ሰላምን ለማደፍረስ ከሚጠቀሙባቸው አጋጣሚዎች መካከል የበዓላት ወቅቶች ይጠቀሳሉ፡፡ በዓላት የሰላምና የአንድነት መድረኮች ናቸው፣ ይሁን እንጂ እነዚህን መድረኮች ለእኩይ ዓላማቸው ማሳኪያ ለመጠቀም ጸረ ሰላም ኃይሎች ሙከራዎችን ማድረጋቸው አልቀረም፡፡ እነዚህ ሙከራዎች በጸጥታ አካላት፣ በሰላም ሠራዊትና በኅብረተሰቡ ቅንጅታዊ ሥራ ሲከሽፉ ቆይተዋል፡፡ ዘንድሮም በክፍለ ከተማችን እና በከተማችን የተከበሩ በዓላት በሰላም መከበራቸው የዚህ ስኬት ዐብይ መገለጫ ነው፡፡

የዘንድሮው የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ ሲሆን፣ ከሃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር ውይይት በማድረግ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ በቀጣይ በየወረዳው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች የሚቀጥሉ ሲሆን፣ በዓሉ የአደባባይ በዓል እንደመሆኑ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ነዋሪው ኅብረተሰብ፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የጸጥታ አካላት፣ የሰላም ሠራዊት እንዲሁም አመራር እንደወትሮው ሁሉ ቅንጅታዊ ሥራቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ለማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡

ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ጥር 2/2015
118 views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ