Get Mystery Box with random crypto!

ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የሰርጥ አድራሻ: @bolecommunication
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 911

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-02 20:28:52 ሳምንታዊው የሰንበት ገበያ በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የገበያ ማዕከላት በዚህም ሳምንት ቀጥሏል።

በሁሉም ወረዳዎች ባሉት የገበያ ማዕከላት የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ኅብረተሰብ በመቅረብ ላይ ናቸው።

መጋቢት 24/2015
144 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 20:28:40
140 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 15:31:14
“ጤናው የተጠበቀ ማኅበረሰብ፣
የበለጸገች አገር መሠረት ነው”

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ አካላት ዕውቅና ሰጠ፡፡

በዕውቅና ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ከድር ዘኪ ባደረጉት ንግግር ጽ/ቤቱ ጤናውን ራሱ የሚያመርት ትውልድ ለመፍጠር እየሠራ መሆኑን ገልጸው፣ በዘርፉ ከመደበኛ ዕቅዱ ባሻገር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አጫጭር ዕቅዶችን በማቀድ ሰፊ ሥራ መከናወኑን አስታውቀዋል፡፡ በክፍለ ከተማው ሥር የሚገኙ አምስት የጤና ተቋማትን ለማሳደግ እንዲሁም በቤተሰብ ምጣኔ፣ በበሽታ መከላከል፣ የእናቶችና የሕፃናትን ጤና ለማስጠበቅ ይረዳ ዘንድ የሁሉም ባለድርሻ አካለት የጋራ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ኃላፊው አክለው አስገንዝበዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ባሉ ጤና ተቋማት ላይ የሚታዩ የአሠራር ክፍተቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተፈቱ ቢሆንም ችግሮቹን ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ የዘርፉ ተዋንያን የሆኑ ባለድርሻዎች ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ በነበራቸው የሥራ አፈጻጸም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ጤና ጣቢያዎችና የክፍለ ከተማ ቡድኖች የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ መሥፍን ኃይሌ የዕውቅና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡

የካቲት 24/2015
163 views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 09:59:32
“የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ፣
ለኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ!”
ወጣቶች በሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ መሥፍን ታደሰ እንደገለጹት በክፍለ ከተማው ነዋሪ የሆኑ ወጣቶችን በማሰልጠን፣ ብድር በማመቻቸት፣ የመሥሪያ ቦታዎችን በመገንባትና በመስጠት ወደሥራ እንዲገቡ በመደረጉ በርካታ ወጣቶች በራሳቸው አቅም ከመፍጠር በሻገር ለሌሎች የስራ ዕድል መፍጠር የቻሉ ሲሆን፣ በተለይም በማርብል፣ ቴራዞና ብሎኬት ምርት ላይ በመሠማራት የኢኮኖሚ አቅማቸውን የሥራ ባሕላቸው እንዲያድግ ጽ/ቤቱ የቅርብ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ አክለው አመልክተዋል፡፡
ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን ያነጋገራቸው ወጣቶች ተደራጅተው በመሥራታቸው እንዲሁም በጽ/ቤቱ በሚደረግላቸው ክትትልና ድጋፍ ከራሳቸው ባለፈ ለሌሎች ወጣቶችም አርአያ መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ ከሲሚንቶ ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ በምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መከሰቱን ያመለከቱት ወጣቶቹ፣ መንግሥት ይህንን ችግር ለመፍታት በሲሚንቶ ዋጋ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
የካቲት 16/2015
107 views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 09:20:35
97 views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 09:20:34
92 views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 10:14:46
“በትምህርት ዘርፍ ውጤታማነታችን ቀጥሏል!”
በ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች መካከል የቦሌ ክፍለ ከተማ በግል ትምህርት ቤቶች በርካታ ተፈታኞችን በማሳለፍ የአንደኝነት ደረጃን አገኘ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና ክፍለ ከተሞች ዕውቅና በሰጠበት ሥነ ሥርዓት ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በግል ትምህርት ቤቶች በርካታ ተማሪዎችን በማሳለፍ ከአሥራ አንዱ ክፍለ ከተሞች አንደኛ በመውጣቱ ዋንጫና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በዕውቅና ሥነ ሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት የችግሮች ሁሉ መፍቻ ቁልፍ መሣሪያ መሆኑን በመገንዘብ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ገልጸው፣ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአዲስ አበባ የተመዘገበው ውጤት አበረታች ቢሆንም ከከተማው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሁሉንም ባለድርሻ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ በመጠቆም የግል ጥረታቸውን ተጠቅመው ውጤታማ የሆኑ ተሸላሚ ተማሪዎች በቀጣዩ የህይወት ምዕራፍ የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች በብቃት አልፈው ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ዜጋ እንደሚሆኑ እምነታቸውን ገልጸዋል።
በ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በቦሌ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች 1,382 ተማሪዎች ለፈተና የተቀመጡ ሲሆን፣ ከመካከላቸው 929 ተማሪዎች ወደከፍተኛ ትምህርት ማለፋቸውና በዚህም ክፍለ ከተማው በግል ትምህርት ቤቶች 67.2 ከመቶ ተማሪዎችን በማሳለፍ በከተማ ደረጃ አንደኛ መውጣቱን ለማወቅ ተችሏል።
የካቲት 13/2015
120 views07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 10:09:42
“የተሳለጠ የፍትህ ሥርዓት፣
ለመብትና ጥቅም መረጋገጥ ወሳኝ ነው!”
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ላሳዩ አካላት ዕውቅና ሰጠ፡፡
በዕውቅና አሰጣጥ መድረኩ ላይ እንደተገለጸው ጽ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የነዋሪውን ኅብረተሰብና የክፍለ ከተማውን አስተዳደር መብትና ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ባከናወናቸው ተግባራት በአብዛኛው ዕቅዱን ማሳካት የቻለ ሲሆን፣ የፍትሐብሔር ጉዳዮችን፣ የደንብ ማስከበር ውሳኔዎችን፣ የደንብ መተላለፍ ወንጀልንና የግል አቤቱታን በተመለከተ የተከናወኑ የአፈጻጸም ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አንቀጸ ዮሐንስ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት በፍትህ ሥርዓቱ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ለማድረግ በዘርፉ የተሠማሩ አካላትና ባለድርሻዎች እንዲሁም ኅብረተሰቡ በጋራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በመጀመሪያዎቹ የበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በክፍለ ከተማው በፍትህ ዘርፍ ለተመዘገበው ውጤት በጽ/ቤቱ ያሉ ዐቃቢያነ ሕግ እና ደጋፊ ባለሙያዎች ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸውም ኃላፊዋ አክለው አመልክተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ መሥፍን ኃይሌ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም ላሳዩ አካላት የዕውቅና የምስክር ወረቀትና ሽልማት አበርክተዋል፡፡
የካቲት 13/2015
114 views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 10:38:16 በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች የሚካሄደው ሳምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ በወረዳ 1 ተካሄደ፡፡

በጽዳት ንቅናቄው ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት ሙሀባው ጽዱና ለኑሮ ምቹ የሆነች አዲስ አበባን ለመፍጠር ኅብረተሰቡ አካባቢውን የማጽዳት ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡ በክፍለ ከተማው በሚገኙ ወረዳዎች ጽዳትን የማኅበረሰቡ የዘወትር ተግባር ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በስፋት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ያወሱት አቶ ጌትነት፣ ግለሰቦችና ተቋማት በጽዳት ሥራ ውስጥ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ መዋሉን በመጥቀስ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችና በክፍለ ከተማው የሚገኙ ድርጅቶች ከጽዳት ሠራተኞችና ከሽርክና ማኅበራት ጋር በመቀናጀት ለአካባቢ ጽዳት በእኔነት መንፈስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የካቲት 11/2015
142 views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 10:38:14
139 views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ