2022-05-14 12:10:08
በቦሌ ክፍለ ከተማ ጎሮ አይሲቲ ፓርክ በየንኮማድ ኮንስትራክሽን አጋርነት አረንጓዴ የመንገድ አካፋይ ልማት ሥራ ተጀመረ። በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው ባደረጉት ንግግር የመንገድ አካፋይ አረንጓዴ ልማት ሥራው የአረንጓዴ አሻራ የ2014/15 መርሐ ግብር አካል መሆኑን ገልጸው፣ በክፍለ ከተማው ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ ከ1 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ በመሠራት ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል። አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ የግሉ ዘርፍ ሚና የጎላ መሆኑን የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ፣ የንኮማድ ኮንስትራክሽን በራስ ተነሳሽነት የልማት ሥራውን ለማከናወን ተባባሪ በመሆኑ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ስም ምስጋና በማቅረብ ይህንን አርአያነት ያለው ተግባር ሌሎችም ባለሀብቶች ተከትለው የልማት ሥራው ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
345 views09:10