Get Mystery Box with random crypto!

ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የቴሌግራም ቻናል አርማ bolecommunication — ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication
የሰርጥ አድራሻ: @bolecommunication
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 911

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-12-04 10:43:16
የኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የአመራሮች ቡድን በቦሌ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር የአራት ወራት የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ሱፐርቪዥንና ምልከታ አካሄደ፡፡
ቡድኑ ከክፍለ ከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በበጀት ዓመቱ በልዩ ልዩ ዘርፎች የተከናወኑ ሥራዎችን ለመገምገብ በተዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የቀረበለትን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያዳመጠ ሲሆን፣ በሪፖርቱ ዙሪያ ላነሳቸው ጥያቄዎችም በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
ከሪፖርቱ በተጨማሪ ቡድኑ በክፍለ ከተማው እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶች የሚገኙበትን ደረጃ ተዘዋውሮ የተመለከተ ሲሆን፣ በዋነኛነት በትምህርት፣ በከተማ ግብርና እና በሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት በማድረግ በተመረጡ ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታ ተደርጓል፡፡
ኅዳር 19/2015
100 views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 17:10:40
በቦሌ ክፍለ ከተማ በ90 ቀናት ዕቅድ በወረዳዎች እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በክፍለ ከተማው አመራሮች ተጎበኙ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ የተመራ የከተማና የክፍለ ከተማው አስተዳደር አመራሮች ቡድን በወረዳ 2፣ 5 እና 14 እየተከናወኑ ያሉ የ90 ቀናት ዕቅድ ሥራዎችን ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ፣ የሥራ ቦታን ውብና ምቹ ማድረግ፣ የሰንበት ገበያ፣ የከተማ ግብርና እና ሌሎች ሥራዎች በቡድኑ ምልከታ ተደርጎባቸዋል።
ኅዳር 10/2015
155 views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 16:55:37
123 views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 16:55:29
123 views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 09:03:42
“ኪነጥበብ የመጤ ባሕል ተጽዕኖን ለመከላከል”

መጤ ባሕልን ለመከላከልና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማጎልበት የሚያስችል አሳታፊ ቴአትር በቦሌ ክፍለ ከተማ ለዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ቀረበ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ መድረኮች ኩነቶች ዝግጅት ዳይሬክቶሬት አማካይነት የተዘጋጀው ቴአትር ለተማሪዎቹ በቀረበበት መድረክ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ መድረኮች ኩነቶች ዝግጅት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰርጸ ፍሬስብሐት ባደረጉት ንግግር ቢሮው የማኅበረሰቡን ሥነ ምግባር ለማነጽ ባለፉት ዓመታት በስፋት እየሠራ እንደሚገኝ አውስተው፣ እንደዚህ ዓይነት አሳታፊ ቴአትሮች ተዝናኖትን ማዕከል በማድረግ አመለካከትነ በመፈተሽ ዕውቀትን እያጋሩ አዎንታዊ የማኅበረሰብ ለውጥ ለማምጣት አስፈላጊ በመሆናቸው በትምህርት ቤቶች እንዲቀርቡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ “ዛሬ ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ መበራከትን ተከትሎ ሁሉም መረጃ ሰጪና ተቀባይ ሆኗል” ያሉት አቶ ሰርጸ፣ ቴክኖሎጂው መልካም ቢሆንም ከግብረገብነት ያፈነገጠና ከሞራላዊነት የራቀ መልዕክት ማስተላለፍ ተገቢ ባለመሆኑ የቴአትሩ ጭብጥ ይህንን ማዕከል በማድረግ ተማሪዎች ነጋቸውን ብሩህ አድርገው ይመለከቱ ዘንድ ለተማሪዎቹ እንዲቀርብ መደረጉን አመልክተዋል፡፡
53 views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 07:14:35 ውይይቱን የመሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የቦሌ ክፍለ ከተማ ከተማ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ፍጹም ኃይሌ በበኩላቸው የቦሌ ክፍለ ከተማ ባለፉት ዓመታት በሀብት ማሰባሰብ ሥራው በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን አውስተው፣ በዘንድሮው ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የታየውን ዝቅተኛ አፈጻጸም ለማሻሻል ወረዳዎችና ክፍለ ከተማው ቁልፍ አጀንዳ አድርገው በትኩረት መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ በየደረጃው ያሉ የሴክተር ጽ/ቤቶችም ከጽ/ቤቱ ጋር ተቀናጅተው በመረጃ ማሰባሰብና ልውውጥ እንዲሁም በሀብት ማሰባሰብ ሥራዎች ላይ ሊሠሩ እንደሚገባ አቶ ፍጹም አክለው ተናግረዋል፡፡

ጥቅምት 30/2015
መረጃዎቻችንን በአማራጭ ለማግኘት: -
በፌስቡክ፡ www.facebook.com/bolecommunication
በትዊተር: twitter.com/bole_comm
በዩቲዩብ: https://www.youtube.com/channel/UCTc1t2_k9iNhr80vlG5zMJg
ኢንስታግራም: instagram.com/bole_communication
87 views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 07:13:47
“ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የኅብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል”
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በስኬት እንዲጠናቀቅ የሚደረገው ሕዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበት ተገለጸ፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ታደሰ እንደገለጹት የሕዳሴው ግድብ ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ፈተናዎች ውስጥ በነበረችበት ወቅትም ቢሆን ለአንድም ደቂቃ ግንባታው ሳይቋረጥ በጠንካራ ርብርብ አፈጻጸሙ 88 ከመቶ የደረሰ ሲሆን፣ ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ ከ60 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ ይህንን ሀብት የማሰባሰብ ሥራ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ተቋማትና ኅብረተሰቡን በማስተባበር መከናወን ይኖርበታል፡፡ በ2015 በጀት ዓመት ከቦሌ ክፍለ ከተማ 100 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን የገለጹት አቶ ተስፋዬ፣ በአንደኛው ሩብ ዓመት ለመሰብሰብ ከታቀደው 25 ሚሊየን ብር ውስጥ ለመሰብሰብ የተቻለው 30 ከመቶውን ብቻ በመሆኑ በቀሪዎቹ ጊዜያት የታቀደውን ሀብት ለማሰባሰብ የሁሉም አካላት ርብርብ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
81 views04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 06:44:24
አንጋፋው የኦሮሚኛ ድምጻዊ አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በሙዚቃ ሥራዎቹ ትልቅ ክብር ያገኘው አሊ ቢራ ለረዥም ጊዜ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በአንጋፋው ድምጻዊ አሊ ቢራ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።
146 views03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 22:01:35
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር የማኅበራዊ አገልግሎትመስጫ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

በስምምነቱ መሠረት አየር መንገዱ በክፍለ ከተማው በ40 ሚሊየን ብር ወጪ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ መሠረተ ልማቶችን የሚገነባ ሲሆን፣ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ሺፈራው የኢትጵያ አየር መንገድ የሕዝብና የአገር ኩራት መሆኑነን አውስተው፣ ክፍለ ከተማው በ90 ቀናት ሰው ተኮር ተግባራት ዕቅዱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለማሳካት አየር መንገዱ በአጋርነት በመሰለፉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ “ሥራዎቻችንን በጥራት በማከናወን የኅብረሰባችንን ጥያቄ ለመመለስ ለምናደርገው ርብርብ የሁሉም አካላት ድጋፍ ወሳኝ ነው” ሲሉም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አክለው ተናግረዋል፡፡

ጥቅምት 26/2015
164 views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 21:20:00
በቦሌ ክ/ከተማ ፅዱና ውብ ክ/ከተማ የመፍጠር ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል
በዛሬው እለት በቦሌ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በቀጣይ 90 ቀናት ፅዱና ውብ አካባቢን የመፍጠር ንቅናቄ በወረዳ 07 ጉሊት አካባቢ በከፍተኛ ህዝብ ተሳትፎ የተጀመረ ሲሆን በእለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር አቶ ሳዲቅ ሽኩር አዲስ አበባ እንደ ስሟ ፅዱ ውብና አዲስ የማድረግ ተግባር የሁሉም ህብረተሰብ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ባሳለፍነው 2 አመታት በተሰሩ ህብረተሰቡን ያሳተፋ ንቅናቄዎች ውጤት ማምጣት መጀመሩን በዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ አዲስ አበባ ተሸላሚ መሆኗ አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የቦሌ ክ/ከተማ ም/ብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ሰይፋ በበኩላቸው የቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ባለፍት ጊዜያት በርካታ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ማከናወን የተቻለ ሲሆን ፅዱና ውብ ክ/ከተማ የመፍጠር ተግባር አንዱና ዋናው አድርጎ እየተሰራ መሆኑን ገልፅዋል። የቦሌ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት ሙሀባው በመጪዎቹ 3 ወራት በፅዳትና ውበታቸው ተምሳሌት የሆኑ ብሎኮችን ለመፍጠር እንደሚሰራ የገለፁ ሲሆን ሁሉም ነዋሪ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ጥቅምት 26/2015
174 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ