Get Mystery Box with random crypto!

“ኪነጥበብ የመጤ ባሕል ተጽዕኖን ለመከላከል” መጤ ባሕልን ለመከላከልና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

“ኪነጥበብ የመጤ ባሕል ተጽዕኖን ለመከላከል”

መጤ ባሕልን ለመከላከልና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማጎልበት የሚያስችል አሳታፊ ቴአትር በቦሌ ክፍለ ከተማ ለዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ቀረበ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ መድረኮች ኩነቶች ዝግጅት ዳይሬክቶሬት አማካይነት የተዘጋጀው ቴአትር ለተማሪዎቹ በቀረበበት መድረክ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ መድረኮች ኩነቶች ዝግጅት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰርጸ ፍሬስብሐት ባደረጉት ንግግር ቢሮው የማኅበረሰቡን ሥነ ምግባር ለማነጽ ባለፉት ዓመታት በስፋት እየሠራ እንደሚገኝ አውስተው፣ እንደዚህ ዓይነት አሳታፊ ቴአትሮች ተዝናኖትን ማዕከል በማድረግ አመለካከትነ በመፈተሽ ዕውቀትን እያጋሩ አዎንታዊ የማኅበረሰብ ለውጥ ለማምጣት አስፈላጊ በመሆናቸው በትምህርት ቤቶች እንዲቀርቡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ “ዛሬ ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ መበራከትን ተከትሎ ሁሉም መረጃ ሰጪና ተቀባይ ሆኗል” ያሉት አቶ ሰርጸ፣ ቴክኖሎጂው መልካም ቢሆንም ከግብረገብነት ያፈነገጠና ከሞራላዊነት የራቀ መልዕክት ማስተላለፍ ተገቢ ባለመሆኑ የቴአትሩ ጭብጥ ይህንን ማዕከል በማድረግ ተማሪዎች ነጋቸውን ብሩህ አድርገው ይመለከቱ ዘንድ ለተማሪዎቹ እንዲቀርብ መደረጉን አመልክተዋል፡፡