Get Mystery Box with random crypto!

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር የማኅበራዊ አገልግሎትመስጫ መሠረ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር የማኅበራዊ አገልግሎትመስጫ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

በስምምነቱ መሠረት አየር መንገዱ በክፍለ ከተማው በ40 ሚሊየን ብር ወጪ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ መሠረተ ልማቶችን የሚገነባ ሲሆን፣ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ሺፈራው የኢትጵያ አየር መንገድ የሕዝብና የአገር ኩራት መሆኑነን አውስተው፣ ክፍለ ከተማው በ90 ቀናት ሰው ተኮር ተግባራት ዕቅዱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለማሳካት አየር መንገዱ በአጋርነት በመሰለፉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ “ሥራዎቻችንን በጥራት በማከናወን የኅብረሰባችንን ጥያቄ ለመመለስ ለምናደርገው ርብርብ የሁሉም አካላት ድጋፍ ወሳኝ ነው” ሲሉም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አክለው ተናግረዋል፡፡

ጥቅምት 26/2015