Get Mystery Box with random crypto!

በቦሌ ክ/ከተማ ፅዱና ውብ ክ/ከተማ የመፍጠር ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል በዛሬው እለት በቦሌ ክ/ከተማ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

በቦሌ ክ/ከተማ ፅዱና ውብ ክ/ከተማ የመፍጠር ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል
በዛሬው እለት በቦሌ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በቀጣይ 90 ቀናት ፅዱና ውብ አካባቢን የመፍጠር ንቅናቄ በወረዳ 07 ጉሊት አካባቢ በከፍተኛ ህዝብ ተሳትፎ የተጀመረ ሲሆን በእለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር አቶ ሳዲቅ ሽኩር አዲስ አበባ እንደ ስሟ ፅዱ ውብና አዲስ የማድረግ ተግባር የሁሉም ህብረተሰብ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ባሳለፍነው 2 አመታት በተሰሩ ህብረተሰቡን ያሳተፋ ንቅናቄዎች ውጤት ማምጣት መጀመሩን በዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ አዲስ አበባ ተሸላሚ መሆኗ አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የቦሌ ክ/ከተማ ም/ብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ሰይፋ በበኩላቸው የቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ባለፍት ጊዜያት በርካታ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን ማከናወን የተቻለ ሲሆን ፅዱና ውብ ክ/ከተማ የመፍጠር ተግባር አንዱና ዋናው አድርጎ እየተሰራ መሆኑን ገልፅዋል። የቦሌ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት ሙሀባው በመጪዎቹ 3 ወራት በፅዳትና ውበታቸው ተምሳሌት የሆኑ ብሎኮችን ለመፍጠር እንደሚሰራ የገለፁ ሲሆን ሁሉም ነዋሪ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ጥቅምት 26/2015