Get Mystery Box with random crypto!

የኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የአመራሮች ቡድን በቦሌ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር የ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የኢፌዴሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የአመራሮች ቡድን በቦሌ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር የአራት ወራት የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ሱፐርቪዥንና ምልከታ አካሄደ፡፡
ቡድኑ ከክፍለ ከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በበጀት ዓመቱ በልዩ ልዩ ዘርፎች የተከናወኑ ሥራዎችን ለመገምገብ በተዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት የቀረበለትን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያዳመጠ ሲሆን፣ በሪፖርቱ ዙሪያ ላነሳቸው ጥያቄዎችም በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
ከሪፖርቱ በተጨማሪ ቡድኑ በክፍለ ከተማው እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶች የሚገኙበትን ደረጃ ተዘዋውሮ የተመለከተ ሲሆን፣ በዋነኛነት በትምህርት፣ በከተማ ግብርና እና በሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት በማድረግ በተመረጡ ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታ ተደርጓል፡፡
ኅዳር 19/2015