2022-12-27 15:39:59
በቦሌ ክፍለ ከተማ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ ለማድረግ ከመምህራን ጋር አጠቃላይ መግባባት መደረሱ ተገለጸ፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በክፍለ ከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተካሄዱ ውይይቶችን በተመለከተ ባካሄዱት ግምገማ ላይ እንደተገለጸው በየትምህርት ቤቶቹ በተደረጉ ውይይቶች በቅርቡ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች በተፈጠረው ችግር በመማር ማስተማር ሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በተመለከተ እንዲሁም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቀጥል መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃና ምክክር የተደረገ ሲሆን፣ ከውይይቶቹ በኋላም የመማር ማስተማር እንቅስቃሴው ሰላማዊ እንዲሆንና ትምህርት ቤቶችም ሰላማዊ የትምህርት ሥራ እንዲያከናውኑ ለማስቻል ከመግባባት ላይ መደረሱ ተመልክቷል፡፡
ታኅሳስ 18/2015
60 views12:39