Get Mystery Box with random crypto!

በቦሌ ክፍለ ከተማ በከተማ ግብርና ላይ የተሠማሩ ነዋሪዎች ተጠቃሚነታቸው እያደገ ነው። በወረዳ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

በቦሌ ክፍለ ከተማ በከተማ ግብርና ላይ የተሠማሩ ነዋሪዎች ተጠቃሚነታቸው እያደገ ነው።

በወረዳ 11 በጓሮ አትክልት ልማት እና በንብ ማነብ የተሠማሩ ነዋሪዎች በማኅበር ተደራጅተው ሥራቸውን በማሳደግ ውጤታማ ለመሆን መቻላቸውን ለመመልከት የተቻለ ሲሆን፣ አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች ከተሟሉላቸው ሥራቸውን የበለጠ ለማስፋፋት ማቀዳቸውን ተናግረዋል። የማኅበሩ አባላት የሆኑት አቶ ወንዱ ጌታቸው እና አቶ አበበ ዳዲ በንብ ማነብ ሥራ ላይ በመሠማራት ከአንድ ቀፎ በዓመት 20 ኪሎ ግራም ማር በማምረት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። በጓሮ አትክልት ልማት በመስኖ በመጠቀም ጎመን፣ ቆስጣ እና ሌሎች አትክልቶችን በማምረት ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት አባላቱ፣ የገበያ ችግር እንዳላጋጠማቸውና ምርታቸውን ለአካባቢው ነዋሪዎችና ወደ አካባቢው ለሚመጡ ሰዎች በመሸጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን በመግለጽ ከራሳቸው በተጨማሪ ከ20 በላይ ለሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር መቻላቸውን አክለው አስታውቀዋል። የማዳበሪያ አቅርቦት እና የነዳጅ እጥረትና የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት አለመኖር ችግር እንደፈጠረባቸው አባላቱ ገልጸው፣ እነዚህ ችግሮች ከተፈቱ ምርታቸውን ከማሳደግ ባለፈ የከብት እና የዶሮ እርባታንም ለመጨመር እንዲሁም በአካባቢው ያለውን የተፈጥሮ ፍልውሃ በመጠቀም የጀመሩትን የመዝናኛ ሪዞርት ሥራ ለማስፋት ማቀዳቸውን አመልክተዋል።

ታኅሳስ 18/2015