Get Mystery Box with random crypto!

በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች የሚካሄደው ሳምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ በወረዳ 1 ተካሄደ፡፡ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች የሚካሄደው ሳምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ በወረዳ 1 ተካሄደ፡፡

በጽዳት ንቅናቄው ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌትነት ሙሀባው ጽዱና ለኑሮ ምቹ የሆነች አዲስ አበባን ለመፍጠር ኅብረተሰቡ አካባቢውን የማጽዳት ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡ በክፍለ ከተማው በሚገኙ ወረዳዎች ጽዳትን የማኅበረሰቡ የዘወትር ተግባር ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በስፋት ሲከናወኑ መቆየታቸውን ያወሱት አቶ ጌትነት፣ ግለሰቦችና ተቋማት በጽዳት ሥራ ውስጥ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ሥራ ላይ መዋሉን በመጥቀስ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችና በክፍለ ከተማው የሚገኙ ድርጅቶች ከጽዳት ሠራተኞችና ከሽርክና ማኅበራት ጋር በመቀናጀት ለአካባቢ ጽዳት በእኔነት መንፈስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የካቲት 11/2015