2023-04-03 15:51:45
የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት "ሰላም የልማትና የዕድገት መሠረት በመሆኑ ለሰላማችንና ለብልጽግናችን መረጋገጥ እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም ባለቤት ሆነን ድርሻችንን እንወጣለን" ብለዋል። የኑሮ ውድነትና የትራንስፖርት ችግር ለሰላም መደፍረስ መንስኤ ሊሆኑ ስለሚችሉ መንግሥት በትኩረት ሊሠራበት እንደሚገባ ያሳሰቡት ተሳታፊዎቹ፣ በሚዲያዎችና ሌሎች መንገዶች የአገርን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ አካላትን መላው ኅብረተሰብ ከሰላምና ጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሴራቸውን ሊያከሽፉ እንደሚገባ አመልክተዋል።
ውይይቱን የመሩት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ፣ በልዩ ልዩ በዓላት አከባበር እንዲሁም በሕልውና ዘመቻው ወቅት በደጀንነት ያበረከቱት አስተዋጽኦ የማይዘነጋ መሆኑን ገልጸው፣ አሁንም ሕዝቡ የሰላም ባለቤት በመሆኑ ለክፍለ ከተማው፣ ለከተማውና ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ ከመንግሥት ጎን በመቆም የማይተካ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ በአብሮነትና ተከባብሮ በመኖር የካበተ ልምድ እንዳለው ያወሱት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መላኩ ታምሩ በበኩላቸው፣ ይህንን እሴት ለመናድ በብሔርና በሃይማኖት የሚከፋፍሉ አካላትን መላው ነዋሪ ኅብረተሰብ እንደአንድ በመቆም ሊመክታቸውና የሰላም ዘብ መሆኑን በተግባር ሊያሳይ እንደሚገባ አሳስበዋል።
መጋቢት 25/2015
119 views12:51