Get Mystery Box with random crypto!

የሕዝብን ቅሬታ፣ በተግባር መፍታት!” በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ለረዥም ዓመታት ከፍተኛ የሕዝብ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የሕዝብን ቅሬታ፣
በተግባር መፍታት!”
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ለረዥም ዓመታት ከፍተኛ የሕዝብ ቅሬታ ሲቀርብበት የነበረው የአስተዳደሩ መግቢያ መንገድ በአዲስ መልክ ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነ።
የወረዳው አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳኜ አስፋው እንደገለጹት ወደ ወረዳው አስተዳደር ቅጥር ግቢ የሚያስገባው መንገድ ለእግረኞችም ሆነ ለተሽከርካሪዎች ምቹ ያልሆነ በመሆኑ ለበርካታ ዓመታት ነዋሪዎች ከፍተኛ ቅሬታ ሲያቀርቡበት የነበረ ሲሆን፣ የወረዳው አስተዳደር ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመተባበር መንገዱን በአስፓልት ገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን አድርጓል። የመንገዱ መሠራት ለአገልግሎት ፈላጊዎችም ሆኑ የአስተዳደሩ ሠራተኞች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ያስረዱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የወረዳው አስተዳደር ሌሎችም ቅሬታ የቀረበባቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች የመፍታት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አክለው አስታውቀዋል።
አስተያየታቸውን ለቦሌ ኮሚዩኒኬሽን የሰጡ ተገልጋዮች በበኩላቸው መግቢያው ወደ ወረዳው አስተዳደር ለሚመጡ ተገልጋዮች በተለይም ለአካል ጉዳተኞች በጣም አስቸጋሪ በመሆኑ ወደ ቅጥር ግቢው ገብተው ለመስተናገድ ይቸገሩ እንደነበር አውስተው፣ አሁን ላይ መንገዱ በአዲስ መልክ ተሠርቶ ለአገልግሎት በመብቃቱ ችግራቸው መፈታቱን አመልክተዋል።
መጋቢት 25/2015