Get Mystery Box with random crypto!

በቦሌ ክፍለ ከተማ የጸጥታ ሁኔታ ዙሪያ ያተኮረ ግምገማ ተካሄደ፡፡ የክፍለ ከተማ አስተዳደሩና የ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

በቦሌ ክፍለ ከተማ የጸጥታ ሁኔታ ዙሪያ ያተኮረ ግምገማ ተካሄደ፡፡

የክፍለ ከተማ አስተዳደሩና የሁሉም ወረዳዎች አመራሮች በተሳተፉበት በዚህ ግምገማ በተለይም በትምህርት ቤቶች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል በአመራሩ፣ በኅብረተሰቡ እና በጸጥታ መዋቅሮች በመከናወን ላይ ባሉ ተግባራትና በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው በሚገቡ ሥራዎች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቀጥል ለማስቻል በየወረዳዎቹ የሕዝብ ውይይቶች መካሄዳቸውን በግምገማ መድረኩ ላይ የገለጹት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዓለምጸሐይ ሺፈራው፣ ከውይይቶቹ የተገኘውን ግብዓት በመውሰድ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንቅስቃሴ ለማክሸፍ ሁሉም አመራር በከፍተኛ ቁርጠኝነት የመሪነት ሚናውን በበለጠ መወጣት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡

ታኅሳስ 6/2015