Get Mystery Box with random crypto!

የተከበራችሁ የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች እና መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለጌታች | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የተከበራችሁ የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች
እና
መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
የክርስትና አስተምህሮ እንደሚያስረዳን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሕይወቱን የሰጠው ስለሰው ልጅ ፍጹም ፍቅር ነው፡፡ የስቅለቱና የትንሣኤው ዓላማ እኛም አርአያነቱን ተከትለን በፍቅር እንድንኖርና መስጠትን የሕይወታችን አካል እንድናደርግ ነው፡፡

የስቅለትና የትንሣኤ በዓላት የመስዋዕትነት፣ የይቅርታ፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ በአጠቃላይ ውብ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን ይበልጥ ከሚያጎሉና ከሚያደምቁ በዓላት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም የአብሮነት መንፈስ እንዲሆን ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ ወደ ምድር ስንመጣ ንጹሕ ሆነን እንደተፈጠርን ሁሉ በንጽሕናና በቅንነት መኖር እና ሕዝባችንን በሀቅ ማገልገል እንደሚኖርብን አደራ እያልኩ፣ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ እንዲሁም የአብሮነት እንዲሆን ያለኝን ልባዊ ምኞት በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስም እገልጻለሁ፡፡

መልካም በዓል!

ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ሚያዚያ 7/2015