Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጄኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ያሠራው ፓርክ እና ሀውልት በከንቲ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጄኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ያሠራው ፓርክ እና ሀውልት በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመረቀ።

ለቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ሰዓረ መኮንን በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ የተሰራላቸው የመታሰቢይ ሐውልት ዛሬ ተመርቋል፡፡ በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ "በቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ በጀኔራል ሰዓረ መኮንን ስም ያስገነባነውን ፓርክ እና የመታሰቢያ ሀውልት ስናስመርቅ ከታሪኩ ቀጣዩ ትውልድ እንዲማርበት ሲሆን መሰዋቱ ቢያስቆጨንም የተሰዋለት ዓላማ ታላቅና ትውልድ የሚታነጽበት ሕያው ታሪክ ነውና እንጽናናለን" ብለዋል ።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ የጀኔራል ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦች እንዲሁም የጀኔራል ሰዓረ የቀድሞ ባልደረቦች ተገኝተዋል፡፡

ሚያዚያ 14/2005