Get Mystery Box with random crypto!

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እና የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች ፣ እንኳን ለ1,444ኛው የኢ | ቦሌ ኮሚዩኒኬሽን/Bole Communication

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እና
የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች ፣

እንኳን ለ1,444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የረመዳን ጾም ሙስሊሞች በትህትናና በፍጹም መታዘዝ በፈጣሪ ፊት የሚቀርቡበትና መልካምነትን በተግባር የሚፈጽሙበት ቅዱስ ወር ነው። ይህንን የተቀደሰ ወር በዱአና በመልካም ተግባራት በማሳለፍ እነሆ ለረመዳን ጾም ፍቺ ዋዜማ ደርሰናል።

የኢድ አልፈጥርን በዓል ስናከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንን ባለን አቅም መደገፍና አይዟችሁ ማለት ይኖርብናል ። ከዚህ አንፃር በክፍለ ከተማችንና በአሥራ አንዱም ወረዳዎቻችን ለ7,000 ወገኖቻችን ማዕድ ያጋራን ሲሆን፣ ሕዝበ ሙስሊሙም ይህንን የበጎነት ተግባር በየአካባቢው በማከናወን በጎነትን በተግባር ማሳየት ይጠበቅበታል።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት በዓል እንዲሆን ያለኝን ልባዊ ምኞት በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስም እገልፃለሁ።

ኢድ ሙባረክ!

ዓለምጸሐይ ሺፈራው
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ሚያዚያ 12/2015