Get Mystery Box with random crypto!

ዝክረ ብሒለ አበው

የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የሰርጥ አድራሻ: @behileabew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 345

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-07-19 03:20:38 እሁድ እድገናኝ መድሎተ ፅድቅን እንኮምኩም። ሌላ ቀጠሮ እንሠርዝ አራት ኪሎ ቅዲስ ባሎወልድ ግቢ 9:00--11:30
በመገኘታችን ብቻ እናተርፋለን ከተሳተፍንማ እንዴታ
3 viewsእሱበ ዐይናለም, 00:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 23:01:25 ስለ ተሳትፎአችሁ አመሰግናለሁ ።
ደርዝ ያልያዘች ተርመስመስ ያለ ሀሣብ እያየሁ ነው።
ትልቁን አዳራሽ መስራትም ሆነ ቤቴልሔሙን መስራት አሁን ያለውን አዳራሽ ቀለም ቀብቶ መድረኩን ሸራ ከመወጠር አያግደንም እባካችሁ አጀንዳ አትደርቡ።
አሁን ቀለምና ሸራዋን ገዝተን እንላክ ከዛም እዛው አዳራሽ ላይ ተሠባስበን እየተመካከርን ቤቴልሔሙንም አዳራሹንም እንሰራለን። ባለ 10,000 ስንጨርስ ስለ 10,000,000 እናወራለን
10 viewsእሱበ ዐይናለም, 20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:59:51 የታሰበው አዳራሽ እስኪሰራ ይህንን ማደሱ ጥያቄውስጥ አይገባም።
ለማደስ የሠራተኛ ሳይጨምር 10,000 ይፈጃል ብለዋል እንረባረብ። በአይነት ማቅረብ ይቻላል።
2 viewsእሱበ ዐይናለም, 20:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 08:59:12 መድሎተ ፅድቅ ቅፅ አንድን አንብበን የበኩላችንን ሀሳብ እናቅርብ እናም እንወያያለን ተባብለን ነበር ግን ነቅቶ የመሳተፍ ችግር ጎብኝቶናል።
መቼም ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን ልንነቃ ይለናል።
አስክሬናችን ላይ ችግኝ የሚተክል መሪ ይዞ መተኛት ከመሪያችን በላይ መታመም ይሆናል።
ከፊት ይልቅ አሁን እንንቃ እንሰባሰብ ህብረታችንን እናጠናክር። በየግላችን እሮጠን ምን አመጣን ለሠይጣን የተመቸን ከመሆን ውጪ።
እናም እላለሁ እንበርታ እናበርታ እንምከር እንመካከር ለስንፍና እጅ አንስጥ። በጋራ እንቁም ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነውና እንጠነካከር።
18 viewsእሱበ ዐይናለም, 05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 20:54:24
96 viewsbisrat, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 20:48:30 #በዓለ_ጰራቅሊጦስ
ከዕርገተ ክርስቶስ በኋላ
ደቀመዛሙርቱ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ተሰብስበው በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ በዓለ ሃምሳ
የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ ዐውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፡፡
ተቀምጠው የነበሩበትን ቤት ሞላው እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡
በሁሉም መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው ፡፡መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር፡፡
በዓሉን ለማክበር የተሰበሰቡ አይሁድ ተደነቁ፡፡ በየቋንቋቸው ሲናገሩ ሰሙ፡፡ “እነዚህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? የገዛ
ቋንቋችንን እንዴት ሊያውቁና ሊናገሩ ቻሉ?” በማለት ተጠያየቁ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ የመንፈስ ቅዱስ መምጣት ያስገኘውን ጥቅም፤
የእግዚአብሔር መንፈስ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ማደሩን፤ የትንሣኤውን ወንጌል፤ የማዳኑን ዜና፤ የምሥራቹን ድምፅ ሰበከላቸው፡፡
እነርሱም “ምን እናድርግ?” በማለት ከልባቸው ተመለሱ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም “ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ
እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ” አላቸው፡፡
ሦስት ሺሕ ሰዎች በአንድ ስብከት ተመለሱ ተጠመቁም፡፡ ያም ዕለት የቤተክርስቲያን የልደት ቀን ይባላል፡፡
ጰራቅሊጦስ ማለት አጽናኝ፤ በመንገድ ደጋፊ፤ ረዳት ማለት ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ አማኞችን ለማጽናናት ወደ ዓለም ስለመጣ
ጰራቅሊጦስ ተብሏል፡፡ የአገልጋዮች ሩጫ፣ የምእመናን ጉዞ የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት አፈጻጸም ያለ መንፈስ ቅዱስ አይከናወንም፡፡
መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው መንፈስ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያን መሪ እና የመምህራን መምህር ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ሰጪና ምስጢር ገላጭ ነው፡፡
ጰራቅሊጦስ ማለት አጽናኝ (ረዳት) ማለት ነው፡፡ እርሱም መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስ
አማኞችን ለማጽናናት ወደ ዓለም መጣ፡፡ መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያንን የልደት በዓል በእሳት ላንቃና በዓለም ቋንቋ አከበረ፡፡
መንፈስ ቅዱስ የሊቃውንት ምስጢር ገላጭ የፍጥረታት ሕይወት ሰጭ ነው፡፡
94 viewsbisrat, edited  17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 18:11:08
142 viewsbisrat, 15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 18:10:17 #ሐሙስ_ግንቦት_25
✣✢✣✢✣✢✢✣
#የ2014_ዓ.ም_የጌታችን_ዕርገት_መታሰቢያ_ዕለት_ነው

‹‹አምላክ በእልልታ ፤ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ›› (መዝ.46:5)


✥ጌታችን ከሞት ከተነሣ በኋላ ለሐዋርያት ሦስት ጊዜ ተገልጦላቸዋል፡፡ የመጀመሪያው መግደላዊት ማርያም ለሐዋርያት ትንሣኤውን ካበሠረቻቸው በኋላ እሑድ ማታ ሐዋርያት በአንድነት በተሰበሰቡበት 
‹‹ሰላም ለእናንተ ይሁን›› ብሎ ተገለጠላቸው እፍ ብሎም ሥልጣነ ክህነትን ሰጣቸው፡፡ 
ሁለተኛው ደግሞ ሐዋርያው ቶማስ ጌታ ትንሣኤውን ሲገልጥላቸው በቦታው ስላልነበረ ካላየሁ አላምንም ብሎ ነበረ ፤ ጌታችን የቅዱስ ቶማስን ጥርጣሬ ለማራቅ ዳግመኛ በተሰበሰቡበት ተገለጠላቸው ፤ ሦስተኛው ደግሞ ሐዋርያት ዓሣ ለማጥመድ በጥብርያዶስ ባሕር ወርደው ብዙ ደከሙ ነገር ግን አንድም ዓሣ አላገኙም ፤ ኋላ ጌታችን ተገልጦ መረቡን ወደ ቀኝ እንዲጥሉ በማዘዝ 153 ታላላቅ ዓሦችን እንዲያገኙ አደርጓል፡፡ 
✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢
ጌታችን ለሐዋርያት ከሞት ከተነሣ በኋላ በኅብረት እንዳለ ሦስት ጊዜ ተገልጦላቸዋል ፤ ከትንሣኤው በኋላ ባሉት ፵ (40) ቀናትም ለሐዋርያት መጽሐፈ ኪዳን የተባለውን የቤተ ክርስቲያናችንን ጸሎት አስተምሯቸዋል፡፡ 
✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤✤
ጌታችን ከሞት ከተነሣ በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጻፉ ብዙ ተአምራትን አድርጓል ፤ ይህን አስመልክቶ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንዲህ አለ ‹‹ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ›› (ዮሐ. 20፤30)፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሐዋርያት አለቃ ለቅዱስ ጴጥሮስ የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑትን ምዕመናን እንዲጠብቅ ትልቅ መንፈሳዊ ሓላፊነት ሰጥቶታል፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተነሣ 40 ቀን በሆነው ጊዜ ፤ ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ መከራ እንደተቀበለ እንደሞተ ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን እንደተነሣ በመስበክ ምስክሮቹ እንደሚሆኑ ‹‹እስከ ምድር ዳርም ድረስ መስክሮቼ ትሆናላችሁ›› በማለት ነገራቸው፡፡ አያይዞም ‹‹አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ›› በማለት አባታዊና አምላካዊ አደራን ሰጣቸው።
✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣✣
 ቀጥሎም ሐዋርያትን ወደ ቢታንያ ይዞአቸው ወጣ ፤ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ላይ ሆኖ ፤ እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ፤ እያዩትም ከፍ ክፍ አለ ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው ፤ በሰማያት ሰማያዊ የሆነ ምስጋና ተሰማ ፤ ሉቃነ መላእክት አምላካቸውን ሉቀበለ ወረደ ፤ ነገደ መላእክትም ሁሉ ያመሰግኑ ነበረ፡፡ መድኃኔ ዓለምም በክብር ወደ ሰማያት ዐረገ ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ምድር ወድቀው ሰገደለት ፤ ቀና ብለውም ወደ ሰማያት ሲያርግ ትኩር ብለው ሲመለከቱት ሳለ ሁለት መላእክት ተገልጠው ‹‹ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል፡፡›› (ሐዋ. 1፤11) በማለት አሰናበቷቸው ፤ ሐዋርያትም በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኝተው ከደብረ ዘይት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ፤ በተነገራቸውም ትእዛዝ መሠረት ሐዋርያት አንድ ልብ ሆነው በጸሎት ይተጉ ነበረ፡፡
(ሉቃ. 24 ፤ 50 ፤ ሐዋ. 1 ፤ 1 - 12) 
✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢✢
የጌታችን ዕርገት ልዩ ነው ፤ በሥልጣኑ በፈቃዱ ይህን አድርጓልና፡፡ አስቀድሞ ነቢዩ ኤልያስ ወደ ሰማያት አርጓል ነገር ግን የእርሱ ዕርገት በእግዚአብሔር ኃይል ፣ ፈቃድና ሥልጣን ነበረ፡፡ ሁሉ የሚቻለው መድኃኔ ዓለም ግን በክብር በምስጋና በፈቃዱ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ 
✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥✥
#ጥያቄዎችን_በመመለስ_በረከት_ያግኙ

1.ጌታችን ከተነሣ በስንተኛው ቀን ዐረገ? 

2.ጌታችን ያረገበት ተራራ የትኛው ነው? 

3.በዚያ ተራራ ላይ ከዕርገቱ በፊት የተፈጸመ አንድ ታሪክ ጥቀሱ? 

4.የጌታችን ዕርገት ከቅዱሳን ዕርገት በምን ይለያል? 

5.ጌታ ሲያርግ ለሐዋርያት የሰጠው ተስፋ ምንድን ነበር?

ወስብሐት ለእግዚአብሔር✥
123 viewsbisrat, 15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 11:41:30
130 viewsbisrat, 08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 11:39:17 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!!!
 #ግንቦት_20:-
#የከበረ_ጻድቅ_ኢትዮጵያዊው_ንጉሥ_ዐፄ_ካሌብ_ዕረፍቱ_ነው፡፡

<<እርሱም የናግራን ሰማዕታትን ደም የተበቀለና በኋላም ንግሥናውን ትቶ ዓለምን ንቆ በመመንኮስ ዋሻ የገባ ነው፡፡ የነገሠበትን የወርቅ ዘውዱንም በጌታችን መቃብር ላይ አስቀምጡልኝ ብሎ ለኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ዮሐንስ ልኮለታል>>

ከክርስቶስ ልደት 524 ዓመት በኋላ በናግራን ሀገር በክርስቲያኖች በአይሁዶችና በአረማውያን መካከል ከባድ ፀብ ተነሣ፡፡ ማዝሩቅ ወይም ፊንሐስ የተባለው የሂማሪያው ንጉሥ የአይሁዶችንና የአረመኔዎቹን ምክር እየተቀበለ ክርስቲያኖቹን ፈጃቸው፣ አብያተ ክርስቲያናቱንም ሁሉ አቃጠለ፡፡ አረማዊው ንጉሥ ‹አምላካችሁን ክርስቶስን ብትክዱት ሕይወታችሁ ይጠበቃል።ሕዝቡም ‹‹ጌታችንን አንክድም›› እያሉ ተገደሉ፡፡ በዚህም ጊዜ የተገደሉት ቁጥራቸው 4252 ሆነ።

የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባ ጢሞቴዎስ ለሀገረ ናግራን ክርስቲያኖች ደማቸውን ይበቀልላቸው ዘንድ ለኢትዮጵያው ንጉሥ ለዐፄ ካሌብ መልአክት ላከ፡፡
ዐፄ ካሌብም መልእክቱ ሲደርሰው ፈጥኖ ተነሣና በዋሻ ከሚኖር ከአቡነ ጰንጠሌዎን በረከትን ተቀብሎ ለአቡነ አረጋዊም በጸሎት እንዲያስቡት ፡ ‹‹ፊንሐስ የተባለ አረማዊ የናግራን ክርስቲያኖችን ደም በከንቱ ያፈሰሰ፣ ቤተ ክርስቲያንን የመዘበረና ያጠፋ ፍጹም የእግዚአብሔር ጠላት ወደሚሆን ሄጄ እዋጋው ዘንድ ተዘጋጅቻለሁ፡፡ ስለዚህ አባቴ ሆይ! አንተም በበኩልህ ጸሎት አድርግልኝ፣ የጻድቅ ጸሎት ትራዳለች፣ ኃይልንም ታሰጣለች፣ በጠላት ላይ ድልንም ታቀዳጃለችና›› የሚል ደብዳቤ ላከ።

አባታችን አቡነ አረጋዊም ለንጉሡ  ‹ወደ ጦሩ ግንባር ሂድ፣ እግዚአብሔር ጠላቶችህን ከእግርህ በታች ያስገዛልህ፣ ለአንተም ግርማ ሞገስ ይስጥህ፣ በሰላም ይመልስህ›› ብለው መርቀው ላኩለት፡፡ ከዚህ በኋላ ዐፄ ካሌብ ልብሰ መንግሥቱን አውልቆ ጥሎ ማቅ ለብሶ በፍጹም ልመና ብዙ ጸሎት አደረገ፡፡

ከዚህም በኋላ ዐፄ ካሌብ ሰባ ሺህ ጦሩን አዘጋጅቶ ወደ የመን ሳባ በመርከብ ተጓዘና ከከሐዲው ፊንሐስ ጋር ጦር ገጠመ፡፡ ከሐዲውን ንጉሥ ፊንሐስን ራሱ ዐፄ ካሌብ ገጠመውና በፈረሱ ላይ እንደተቀመጠ በጨበጣ በጦር ወግቶ ገደለውና ወደ ባሕር ገልብጦ ጣለው፡፡ ከዚያም ዐፄ ካሌብ ዛፋር ወደምትባለው ከተማ ሄዶ እርሷንም ተቆጣጠራት፡፡ በእዚያም ያሉ የፊንሐስን ሹማምንቶች እያፈላለገ በአደባባይ እንዲገደሉ በማድረግ የክርስቲያኖቹን ደም በሚገባ ተበቀለ፡፡ የናግራንንም ሕንፃዎዋን አደሰ፤ የሰማዕታቱንም መታሰቢያ አቆመ፡፡ ወደ እስክንድርያው አባ ጢሞቴዎስና ወደ ሮሜው ንጉሥ ዮስጢኖስም የድል መልእክት ላከላቸውና እነርሱም ሰምተው እጅግ ተደሰቱ፡፡ በአንጾኪያ፣ በእስክንድሪያ፣ በሮም፣ በቊስጥንጥንያና በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ይህን ሲሰሙ በእጅጉ ተደሰቱ፡፡ ይህም የሆነው በ525 ዓ.ም ነው፡፡ ጠፍተው የሄዱ ክርስቲያኖችንም ሰበሰባቸውና ወደቀደመ ቦታቸው መለሳቸው፣ ቤተክርስቲያናቸውን አነጸላቸው፡፡ ከሳባ ሀገር የማረከውን ንብረት ሁሉ ለቤተክርስቲያን ሰጥቶ ዓሥር ሺህ ጠባቂ ሠራዊት ሰቷቸው ወደ አክሱም በሰላምና በፍጹም ደስታ ተመለሰ፡፡

ከዚህ በኋላ ዐፄ ካሌብ ‹ይህን ያደረገልኝን አምላኬን በምን ላስደስተው?› ሲል አሰበና ዓለምን ንቆ፣ መንግሥቱንና ክብሩን ትቶ መንኩሶ በዋሻ ለመቀመጥ ወሰነ፡፡›› ዐፄ ካሌብ ዓለምን ንቆ፣ ልብሰ መንግሥቱን አውልቆ የውኃ መንቀልና አንዲት ምንጣፍ ብቻ ይዞ አባ ጰንጠሌዎን ገዳም አጠገብ ከሚገኝ ዋሻ ውስጥ ገባ።
አባ ጰንጠሌዎንንም ‹አመንኩሰኝ› አለውና የመላእክትን አስኬማ አልብሶ አመነኮሰው፡፡ ዳግመኛም ከዋሻው ወጥቶ ዓለምን በዓይኑ እንዳያይ ማለ፡፡ ዋጋው እጅግ የከበረውንና በነገሠ ጊዜ የጫነውን ዘውዱን ከጌታችን መካነ መቃብር ወይም በር ላይ ይሰቀልለት ዘንድ ከአደራ ደብዳቤ ጋር ለኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳት ለአባ ዮሐንስ ላከለት፡፡ ዳግመኛም ንጉሡ ዐፄ ካሌብ ለአቡነ አረጋዊ ወደ ምንኩስናው ዓለም መግባቱን አሳወቀ እነርሱ በደስታ መረቁት፡፡

ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ዐፄ ካሌብ ይህን ዓለም በመናቅ በበረሃ በዋሻ 12 ዓመት በጾም በጸሎት በብዙ ተጋድሎ ሲኖር ቆይቶ በግንቦት 20 ቀን ዐርፎ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የማያልፍ ሰማያዊ ክብርን ወረሰ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
150 viewsbisrat, 08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ