Get Mystery Box with random crypto!

ዝክረ ብሒለ አበው

የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የሰርጥ አድራሻ: @behileabew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 345

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-10-31 20:20:02 #ጥቅምት_22_ቅዱስ_ሉቃስ_ወንጌላዊ_በሰማዕትነት_አረፈ።

#ሉቃስ ማለት በላቲኑ ትርጓሜ ብርሃናማ፣ ብርሃን የያዘ ማለት ነው፡፡ቅዱስ ሉቃስ ሀገሩ አንጾኪያ ነው፡፡ አስቀድሞ ከ72ቱ አርድእት ወገን የተቆጠረ ሲሆን ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወርዶ ወነጌልን ሰብኳል ከሐዋርያወ ቅዱስ ጳውሎሰ ጋረ የተገናኘውም በዚሁ ነው፡፡

#ቅዱስ_ሉቃስ የሕክምና ሙያ የነበረው ሲሆን ያጠናውም ከአቴናና እስክንድርያ ሊቃውንት መሆኑ ታውቋል፡፡ ከዚህ ሙያው በተጨማሪ የሥነ ሥዕል ችሎታም እንደነበረው ይነገራል፡፡ ይህንን ችሎታውንም በወንጌሉና በሐዋርያት ሥራ መጽሐፉ ላይ ባለው ሥዕላዊ አገላለጥ ከማንጸባረቁም ሌላ በእጁ የተሳሉ ሥዕሎች በተለያዩ ሀገሮች ይገኛሉ፡፡ የቅዱስ ሉቃስ ስዕሎች እመቤታችን ልጇን አቅፋ ( ምስለ ፍቁር ወልዳ) የሳላቸው ሲሆኑ በኢትዮጵያ በተድባበ ማርያም ፤ በደብረ ዘመዶ ፤ በዋሸራ ፤በጅበላ ሲገኙ ተመሳሳዩም በስፔን ቅድስት ማርያም ካቴድራል እንደሚገኝ ይነገራል ፡፡

#ቅዱስ_ሉቃሰ የድንግልና ሕይወት የነበረው ወንጌላዊ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሰማዕትነት እስካረፈበት ጊዜ ድረስ ደቀ መዝሙር በመሆን አገልግሎታል፡፡

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ በ67 ዓ.ም. በሮማ በሰማዕትነት ሲያርፍ ሉቃስ ወደ ድልማጥያ መጣ፡፡ በዚያም በሽምግልና ዘመኑ ወንጌልን በመስበክ ላይ እያለ አይሁድና ካህናተ ጣዖት ተባብረው ትምህርቱን በመቃወም ተነሡበት፡፡ መስከረም 20 ቀን 68 ዓ.ም. አይሁድና አረማውያን ጉባዔ አድርገው ነገር በመሥራት ለሮም ንጉሥ ከሰሱት፡፡ በዚያን ዘመን ኔሮን እብደቱ ያየለበት ጊዜ በመሆኑ የቅዱስ ሉቃስን ከሮሜ ማምለጥና ወደ ድልማጥያ መምጣት ሲሰማ 200 ወታደሮችን ላከበት ቅዱስ ሉቃስም የሰዎችን መምጣት በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ያሰተምራቸው የነበሩትን ምእመናን ወደየቤታቸው ላከና በድልማጥያ አጠገብ ወደሚገኘው ባሕር ተጠጋ፡፡በባሕሩ አጠገብ አንድ ዓሣ አስጋሪ ቆሟል፡፡

#ቅዱስ_ሉቃስ ወደ ዓሣ አስጋሪው ቀረበና ጨዋታ ጀመሩ፡፡ ቀስ በቀስም ወንጌል ይሰብክለት ጀመር፡፡ ዓሣ አስጋሪውም ቅዱስ ሉቃሰ የሚነግረውን ሁሉ ሥራውን አቁሞ በደስታ ያዳምጠው ነበር፡፡ በመጨረሻ እንካ እነዚህ የሕወይትን መገንድ ይመሩሃል አለና የያዛቸውን መጻሕፍት ሁሉ ሰጠው፡፡ ያም ዓሣ አስጋሪ እጅግ ተደስቶ ዕቃ በሚያስቀምጥበት ቦታ በክብር አኖራቸው፡፡ ቅዱስ ሉቃሰ መጽሐፉን ሰጥቶት ዘወር ሲል የኔሮን ወታደሮች ተረባረቡና ያዙት፡፡ ከዚያም ወደሮም ተወሰደና የኔሮን ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ጥቅምት 22 ቀን አንገቱን ተሠይፎ በአሸዋ በተሞላ ከረጢት አስገብተው በተወለደ በ84 ዓመቱ ወደ ባሕር ወረወሩት፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍቱን ግን ያ ዓሣ አስጋሪ ለዚህ ትውልድ አትርፏቸዋል፡፡

#፩ኛ_የቅዱስ_ሉቃስ_ወንጌል
ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ በዓይኑ የተመለከተውን ከሐዋርያትም የሰማውን ጠንቅቆ በማሰብ 24 ምዕራፍ፣ 1149 ቁጥሮች የያዘ ወንጌል አበርክቶልናል፡፡ ወንጌሉን የጻፈው ከ58-60 ዓ.ም. ባው ጊዜ ውስጥ ቅዱስ ጳውሎስ በእሥር ላይ ባገኘው ዕረፍት መሆኑ ይነገራል፡፡ ወንጌሉ የተጻፈው በግሪክ ቋንቋ ሲሆን የተጻፈለትም ቴዎሎስ ለተባለ የመቄዶንያ / ግሪክ/ ባለሥልጣን ነው፡፡ ወንጌሉ የአሕዛብ ወንጌል እየተባለ ይጠራል፤ የተጻፈው ለእነርሱ ስለሆነ ነው፡፡

#የሐዋርያት_ሥራ
የሐዋርያት ሥራን የጻፈው ቅዱስ ሉቃስ ነው፡፡ ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ከ1-34 ዓ.ም. ያለውን የክርስትና ታሪክ ካሰፈረ በኋላ ቀጣዩንና ከ34-58 ዓ.ም. ያለውን ደግሞ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፉ ላይ ጽፏል፡፡

ከምዕራፍ 1-8 ያለው የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ በኢየሩሳሌም የሚያሳይ ሲሆን ከምዕራፍ 9-12 ያለው ታሪክ ደግሞ በእስጢፋኖስ ሰማኝትነት በተነሣው ስደት የተበተኑት የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ልጆች በአካባቢው ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉዞ የሚያሳይ ነው፡፡
ከምዕራፍ 13 ጀምሮ እስከ ፍጻሜው ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስን ጉዞዎች ተከትሎ የጻፈውና ክርስተና በታናሿ እኪያር በአውሮፓ እንዴት እንደተሰበከ የሚያሳየው ክፍል ነው፡፡

#የሐዋርያት_ሥራ መጽሐፍ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያው የሮም እሥራቱ በቁም እሥር ላይ ሆኖ ወንጌልን እንዲሰብክ ተፈቅዶለት በነበረ ሰዓት በሮም ከሚኖሩ አይሁድ ጋር በ58 ዓ.ም ስለሃይማኖት ያደረገውን ውይይት ተርኮ ያጠናቅቃል፡፡ ወንጌላዊው ሉቃስ የሐዋርያት ሥራን የጻፈው በ58/በ59 ዓ.ም/ ነው፡፡

#ሉቃሰ_ዘላሕም፡- አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ቅዱስ ሉቃስ ለምን በላም እንሚመሰል ሲናገር፣ የመድኃኒታችንን መሥዋዕትነት ሐዲስዋ እምቦሳ በወለደች በንጹሕ ላም ፍሪዳ መስሎ ይናገራልና ይለዋል፡፡ እንዲሁም በከብቶች በረት መወለዱን ስለሚናገርና ታረኩም የላም ወተት ለሕፃን ልጅ ቀላል ምግብ እንደሆነ ሁሉ ለአዲሰ አማኝ ቀለል በሎ የቀረበ ስለሆነ በላም ተመስሏል፡፡

ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን እኛንም በወንጌላዊው ጸሎት ይማረን!!!
25 viewsbisrat, 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 19:14:53
30 viewsbisrat, 16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 19:14:29 #በዘመናችን_የተፈጸመው_ድንቅ_የእመቤታችን_ተአምር

___

“ቆዩ መቤታችን የተራረጠውን ሰውነቴን እንደገና እየቀጣጠለች ስለሆነ እንዳትከፍቱ”

___

ይህ ተአምር የተፈጸመው በ2006 ዓ.ም ነው። እጅግ የታወቀ የሳውዲ ዓረቢያ ባለጸጋ ሰው ነው። ልጅ ስላልነበረው ሶርያ ውስጥ በምትገኝ ጼዴንያ በምትባል ገዳም ስለት የምትሰማ የእመቤታችን ሥዕል መኖሯን ሰምቷል። ሰውዬው በገዳሙ ስለሚፈጸመው ተአምር ስለሰማ በአውሮፕላን ተሳፍሮ ደማስቆ ገባ። ደማስቆ ከደረሰ በኋላ አንድ የታክሲ ሹፌር አግኝቶ ''ጼዴንያ ከምትባል ገዳም ተአምር እንደሚፈጸም ሰምቼ ነው መጣሁት። ባለጸጋ ብሆንም ልጅ የለኝም። ከገዳሙ ሔጄ ልጅ እንዳገኝ ስለት ተስየ ልመጣ ነውና እባክህ ውሰደኝ። ስለቴን ከሰማችኝ ለገዳሟ 800 ሺሕ፣ ለአንተም ወደ ገዳሙ ስለወሰድከኝ 20ሺሕ ዶላር እሰጥሃለሁ'' ብሎት ወደ ገዳሙ ሔዶ ተሳልሞና ተስሎ ተመለሰ።

___

በዓመቱም ወንድ ልጅ ስለወለደ በጣም ደስ አለው። የተሳለውን ስለት ለድረስ ከመነሣ አስቀድሞ ወ ታክሲ ሹፌሩ ደውሎ ''ከዚህ በፊት ጼዴንያ ከሚባለው ገዳም እንደወሰድከኝና ልጅ እንድትሰጠኝ እንደተሳልኩ ታስታውሳለህ'' አለው። የታክሲ ሹፌሩም ''አዎን አስታውሳለሁ'' በማለት መለሰለት። ሰውዬውም ''ስለቴ ስለደረሰልኝ ለገዳሙ የተሳልኩትን፣ ለአንተም ቃል የገባሁትን ልሰጥ በዚህ ቀን ስለምመጣ አውሮፕላን ማረፊያ ጠብቀህ እንድትወስደኝ'' አለው።

___

የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራና የድንግል ማርያምን በረከት በጆሯቸው ቢሰሙም ለበረከት ተሳታፊ ለመሆን ያልታደሉ ሰዎች አሉ። ዙ ሰዎች እግአብሔር ስላደረገው ተአምር ያውቃሉ፤ ይሰማሉም፤ ግን ከበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን አይታደሉም። የታክሲ ሹፌሩም ከእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች የሚመደብ ነው። ባለጸጋው እንደደወለለት ጓደኞቹን ሰብስቦ ''ከሳውዲ ዓረቢያ እንዲህ ዓይነት ሰው ሊመጣ ነው። ይህን ያህል ገንዘብ ይዞ በመምጣት ጼዴንያ ለምትባለው ገዳም ይሰጣል። ገንዘቡን ለገዳሙ ከመስጠቱ በፊት ከአውሮፕላን ሲወርድ ተቀብለን ወደ ሰዋራ ቦታ ወስደን፣ ሰውዬውን ገድለን ለምን ገንዘቡን አንከፋፈልም'' ብለው መከሩ። ሰውዬው ሲመጣ አውሮፕላን ማረፊያ ጠብቀው በታክሲ ወደ ሰዋራ ቦታ ወሰዱት።

___

በመቀጠልም ሰውዬውን ከታክስ አስወርደው የያዘውን ገንዘብ ወሰዱ፤ ከዚያ በኋላ ከአንገቱ ጀምረው አጽቅ፣ አጽቁን ቆራረጡ። አስከሬኑን ከገደሉበት እዳይጥሉት ስለሩ በትልቅ ጆያ ከትተው በታክሲው ከኋላ በኩል ከዕቃ መጫኛው ውስጥ ከትተው ከሚያመቻችው ቦታ ለመጣል ይዘው መሔድ ጀመሩ። አገር አማን ብለው ሲጓዙ ፖሊስ መንገድ ዘግቶ ደንገተኛ ፍተሻ ሲያደርግ ደረሱ። ወደ ኋላ እንዳመለሱ መንገዱ አንድ መስመር ብቻ ያለው በመሆኑ አልቻሉም። አማራጭ ስላልነበራቸው ቆመው መጠበቅ ግድ ሆነባቸው። ፖሊስም መኪኖችን እየፈተሸ እነሱ ካሉበት ደረሰ። እቆሙበት የደረሰው ፖሊስ ታክሲውን ክፈቱ አላቸው። ታክሲው ሲከፈት በትልቅ ሻንጣ ውስጥ ብዙ ገንዘብ ይዘዋል። ፖሊሱም ''እናንተ የታክሲ ሹፌር ናችሁ። ይህን ያህል ገንዘብ ከየት አገኛችሁ'' ሲላቸው ምክንያት ፈጥረው ቢነግሩትም ስላላመናቸው እስቲ የመኪናውን የዕቃ መጫኛ ክፈቱ አላቸው። ሰዎቹ ስለደነገጡ ''አንተ ክፈት፣ አንተ ክፈት'' መባባል ጀመሩ። ድርጊታቸው ፖሊሱ ይበልጥ እንዲጠራጠራቸው አደረገ። ''መኪናው የአንተ አይደለም እንዴ ለምን አትከፍትም'' ብሎ ሹፌሩን ሲያስገድደው ወርዶ ሊከፍት ጎንበስ ሲል “ይህንን የዕቃ መጫኛ እንዳትከፍት” የሚል ድምፅ ከውስጥ ስለሰማ የሠሩትን ያውቃልና ደንግጦ ወደቀ። ፖሊስም በሁኔታቸው ተገርሞ ምን ሆናችሁ ሲላቸው ከተረጋጉ በኋላ ከመጀመሪያው አንሥቶ የፈጸሙትን በዝርዝር ነገሩት።

___

ወዲያው ጋዜጠኞች፣ የካሜራ ባለሞያዎች፣ ፖሊሶች እንዲመጡ ተደረገና የታክሲውን ዕቃ መጫኛ ሊከፍቱ ሲሞክሩ “ቆዩ እመቤታችን የተቆራረጠውን ሰውነቴን እንደገና እየቀጣጠለች ስለሆነ እንዳትፍቱ” የሚል ምፅ ሰሙ። እዲከፍቱ ሲፈቀድላቸው የዕቃ መጫኛውን ሲከፍቱ ሰውዬው ከጆንያ ወጥቶ ቁጭ ብሏል። በሰውነቱ ላይ ምልክት ከመኖሩ ውጭ ምንም የጉዳት ምልክት የለበትም። ከሕይወት ወደ ሞት ተሸጋግሮ የነበረው ሰው ከጆንያ ወጥቶ ሰዎቹ ምን እንዳደረጉት፣ ለምን ወደ ሶርያ እንደመጣ፣ ገንዘቡን ለምን እንደያዘው ፣ ወዴት ሊሔድ እንደነበር ተናገረ።

___

ይህም ተአምር በመጀመሪያ በሶርያ ቲሌቭዥን ቀጥሎም በልዩ ልዩ ቴሌቭዠን ጣቢያዎች ተላለፈ። ለገዳሙ የተሳለውን ገንዘብ አደረሰ። ለታክሲ ሹፌሩም ''አንድ ጊዜ ቃል ገብቻልሃለሁ'' ብሎ 20ሺሕ ዶላር ሰጠው። ይህ በእኛ አገር ተአምረ ማርያ የተጻፈ ሳይን እመቤታችን ዛሬም ተአምር እንደምታደርግ የዓለም ሕዝብ ይረዳ ዘንድ በብዙ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች የተላለፈ ነው።

_ _ _ _ ___

በዚህ በተጨነቅንበት ወቅትም እመቤታችን ከመከራ እንደምትሰውረን፣ ለችግር ብንጋለጥ እንኳ በተአምራት እንደምትታደገን፣ መከራ ላይ ብንወድቅም ለበረከት እንደሚሆንልን በማመን በንስሐ እንዘጋጅ። እምነታችንን እናጥብቅ፣ ራሳችንን ጠብቀን እንኑር።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ከአቅማችን በላይ የሆነውን አምላካችን እግዚአብሔር ከእኛ ያርቅልን። አሜን!!!
30 viewsbisrat, 16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 17:16:19
39 viewsbisrat, 14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 17:13:53 #መልአኩ_ገብርኤል_እና_ወንጌላዊው_ዮሐንስ

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በፍጥሞ ደሴት ያለበደሉ ወንጌልን በመስበኩ ብቻ ለታሰረው ለወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በታላቅ ግርማ ተገለጠለት።

የመላእኩን ክብር የሚያውቅ ቅዱስ ዮሐንስም በእግሩ ስር ወድቆ የጸጋ ስግደት ሰገደለት የዚህን ጊዜ የትህትና ባለቤት የሆነው ቅዱስ ገብርኤል ግን <<እኔም አንተም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነንና አትስገድልኝ>>አለው።

አንዳንድ ተጠራጣሪዎች ታዲያ ለመላእክት ሲገለጡም ሆነ ሳይገለጡ ምንም ዓይነት ስግደት አይገባቸውም በማለት ራእ. 19፥10 ላይ ያለውን (‹‹አትስገድልኝ››) የሚለውን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፡፡

በመሠረቱ ይህ ጥቅስ ለመላእክት የጸጋ ስግደት መስግድ እንደሚገባን እንጂ መስገድ እንደማይገባን የሚገልጽ አይደለም፡፡ ወንጌላዊውና ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ለመልአኩ ገብርኤል መስገዱ ሳያውቀው ሳይረዳው ያደረገው ድርጊት እንዳልሆነ እንድናምን ማንነቱና ሕይወቱ ያስገነዝበናል፡፡ ምክንያቱም የጥበብ፣ የማስተዋል፣ የዕውቀት ጸጋን የሚያድል መንፈስ ቅዱስ አድሮበት እያለ ሳያውቀው አደረገው ብሎ መናገርና ማመን መንፈስ ቅዱስን እንደ መጽረፍ /መስደብ/ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ሰው የሚያመልከውንና የሚሠራውን ሁሉ የሚያውቅ ነው፡፡ በተለይ ቅዱስ ዮሐንስ አካል ከሕልውና ተገልጾለት ምሥጢረ መለኮትን የተናገረ ታላቅ ሰው ሆኖ ሳለ ትንሿ ጉዳይ ተሰውራው ለመልአኩ ገብርኤል ሳያውቅ ሰግዶ ተግሳጽ ደረሰበት ብሎ ማመን ሞኝነት ብቻ ሳይሆን ክህደትም ጭምር ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስን ሰላም ማቃለል ነው፡፡ «መንፈስ ቅዱስ የሰደበ ደግሞ ኃጢአቱ አይሠረይለትም፡፡» (ማቴ. 12፥31-32)፡፡

#የመልአኩ_ገብርኤል_አነጋገር_ታዲያ_እንዴት_ይተረጎማል?

መልአኩ ቅዱስ ዮሐንስን አትስገድልኝ ማለቱ ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡

#1ኛ_ስለ_ትኀትና
ዲያብሎስ ከሥልጣኑ የተሻረው ከክብሩ የተዋረደው በትዕቢቱ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት ግን ትሕትናን ገንዘብ ያደረጉ በመሆናቸው እንደ ሰይጣን ስገዱልን የሚሉ አይደሉም፡፡ ዳሩ ግን እግዚአብሔር ይከበሩ ዘንድ ፈቃዱ በመሆኑ የእግዚአብሔር ሰዎች እንዲወዷቸውና እንዲያከብሯቸው አድርጓል፡፡ ለዮሐንስ በሰገደለት ጊዜ «አትስገድልኝ» ማለቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ከአምልኮተ እግዚአብሔር የሚያወጣ ለጣኦት እንደመስገድ የሚያስቆጥር ሆኖ ሳይሆን መልአኩ ራሱን በዮሐንስ ፊት ዝቅ ከማድረጉ የተነሣ ስለ ትሕትና የተናገረው ነው፡፡ አንድ ሰው ሌላውን ሰው አክብሮ እጅ ቢነሣው /ከመቀመጫው ሲነሳና ሲቀበለው/ éረ አይገባም እንደሚለው ሁሉ ማለት ነው፡፡ ለዚሁም ማረጋገጫ የሚሆነን (ለትሕትና የተናገረ መሆኑን) በምዕራፍ 19 የሰጠውን ማስጠንቀቂያ በምዕራፍ 21 ላይ መድገሙ ነው፡፡ ለትሕትና የተናገረው መሆኑን ያወቀው ዮሐንስ ለመልአኩ ክብር መስጠት እንዳለበትና መስገድ እንደሚገባው ዐውቆ ድጋሚ ሲገለጥለት በድጋሚ ሰግዶለታል፡፡

#2ኛ_ስለ_ሥልጣነ_ክህነት_ክብር_ሲል

የቤተ ክርስቲያን የአጥቢያ ኮከብ ቅዱስ ጳውሎስ የካህናትን ሥልጣን አስመልክቶ ሲያስተምር #ካህናት ሰውን ሁሉ እንደሚዳኙ አታውቁምን? እናንተ ሰውን ሁሉ የምትዳኙ ከሆናችሁ ይህን ትንሹን ነገር ልትፈርዱ አይገባችሁምን? የዚህንስ ዓለም ዳኝነት ተውትና መላእክትን ስንኳ እንድንገዛ አታውቁምን$ (1ቆሮ 6፥2-3) ብሏል፡፡ ከዚህ ትምህርቱ የምገነዘበው ካህናት በሥልጣናቸው መላእክትን ስንኳ ሳይቀር እንደሚያዙ ነው፡፡

ይህንንም ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት እንረዳለን፡፡ በ344 ዓ.ም. በአንጾኪያ ከተማ የተወለደው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እምነትንና ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ትሕትናን፣ በአንድነት ገመድ አስሮ ሕዝቡን ለ7 ዓመት ወንጌልን ሰብኳል፡፡ በ387 ዓ.ም. በአንጾኪያ ከተማ ፖትርያርክነት ተሾሞ ሳለ አንድ ጉዳይ ይገጥመዋል፡፡ ንጉሡ አርቃድዮስና ንግሥቲቱ አውዶክያስ ልጅ እየወለዱ እየሞተባቸው አላድግ ስላላቸው የዚህን ምክንያት ቢጠይቁ ደግ ሰው ክርስትና ባያነሣላችሁ ይሆናል ስላሏቸው ከዮሐንስ አፈወርቅ የበለጠ ደግ ሰው በዘመናችን አለን? በማለት ሴት ልጅ በወለዱ ጊዜ መጥተህ ክርስትና አንሣልን ብለው ላኩበት እርሱም ጥሪውን አክብሮ ሲሆድ በመንገድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከተላከ መልአክ ጋር ይገናኛል፡፡ የበቃ ነውና ረቂቁን መልአክ ሊያየው ችሏል፡፡ ዮሐንስም መልአኩን ‹‹ወዴት ትሄዳለህ?›› ብሎ ጠየቀው መልአኩም ሲመልስለት ‹‹አሁን አንተ የምትሄድባትን ብላቴና ነፍሷን ከሥጋዋ ለይተህ አምጣ ብሎኝ የታዘዝኩትን ለመፈጸም ወደዚያ መሄዴ ነው›› ይለዋል፡፡ ዮሐንስም ‹‹ቆየኝ በጥምቀት ሀብተ ውልድና፣ ስመ ክርስትና ከተሰጣት በኋላ የታዘዝከውን ትፈጽማለህ፡፡ እስከዚያው ግን ከዚሁ አትንቀሳቀስ›› ብሎት በሥልጣነ ክህነቱ ገዝቶት ሄደ፡፡ መልአኩም የዮሐንስን ግዝት ጠብቆ ባለበት ቆመ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ልጅቷን ካጠመቃት በኋላ ንግቶት በሌላ መንገድ ተመለሰ፡፡

 የካህናት ሥልጣናቸው የማይናቅ፣ ትእዛዛቸውም ክብር የሚገባው መሆኑን ስለሚያውቅ ያ መልአክ ወደ ላይም ወደታችም ሳይል አሥር ዓመት ከዚያው ሥፍራ ቆሞ ኖረ፡፡ አሥር ዓመት ሲሆናት ለባል ታጨች ያጠመቅካት ብላቴና እነሆ ለአቅመ ሔዋን፣ ባል ልታገባ ነውና መጥተህ ባርከህ ስደዳት ብለው ለዮሐንስ አፈወርቅ ላኩበት፡፡ እርሱም በጥሪው መሠረት ከዛሬ አሥር ዓመት ልጅቱን ሊያጠምቅ ሲሔድ በሄደበት መንገድ መልአኩን ቆሞ አገኘው፡፡ «ምነው ከዚህ ቆመሃል?» አለው፡፡ መልአኩም ሲመልስለት «የካህናት ማዕረጋቸው የከበረ ነውና መች ወዲያ ወዲህ ያሰኛል፡፡ ቃልህን አክብሬ አንተ ቆይ ካልከኝ ወዲያና ወዲህ ብዬ አላውቅም» አለው ቅዱስ ዮሐንስም በዝንጉዕነቱ ራሱን ወቅሶ መልአኩን የታዘዘውን ያደርግ ዘንድ አሰናብቶታል፡፡ ከላይ በተገለጸው ታሪክ ብናይ በፍጥሞ ደሴት መልአኩ ለዮሐንስ ወንጌላዊ አትስገድልኝ ማለቱ ዮሐንስ ካህንም ነውና ሥልጣኑ ሊያከብር እንደሚገባው ለመግለጽ ሽቶ ነው፡፡ በክብር ዮሐንስ ከመልአኩ ይበልጣልና፡፡

ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን የመላኩ ጥበቃው አይለየን!!! አሜን
32 viewsbisrat, 14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 15:24:49 #ጥቅምት_17_ቅዱስ_እስጢፋኖስ_ሊቀ_የዲያቆናት_ሁኖ_በሐዋርያት_እጅ_የተሾመበት_ዕለት_ነው።

ልዩ ስሟ ሐኖስ በተባለ ቦት በእግዚአብሔር ፈቃድ ቅዱስ በሆነው ጋብቻ የሚኖሩ ስምኦንና  ሃና የሚባሉ ባልና ሚስት ነበሩ፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይሳጠቸው ዘንድ በጾምና ጸሎት በሱባኤ ጸንተው ከኖሩ በኋላ የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ አምላክ ጥር 1 ቀን የተባረከ ልጅ ሰጣቸው።
ስሙንም እስጢፋኖስ ብለው ሰየሙት #እስጢፋኖስ፦የስሙ ትርጉም - አክሊል ማለት ነው፡፡

ከመጥምቁ ዮሐንስ እግር ሥር በመሆን ተምሯል፡፡ በሐዋርያት ዘመን ሁሉም ያላቸውን እያመጡ አንድ ላይ ይኖሩና ይመገቡ ስለነበር ሕዝቡን መመገብ እንዲሁም ቃሉን ማገልገል ለሐዋርያት እጅግ እየከበደ መጣ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ይህን በማስተዋል ሕዝቡን ሰብስበው ከመካከላቸው በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች እንዲመርጡ እና ሕዝቡን እንዲያገለግሉ አደረጓቸው፡፡ ሕዝቡም በሐዋርያት ቃል እጅግ ተደስተው ሰባት ሰዎችን መርጠው በሐዋርያት ፊት አቆሙአቸው ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱና ዋነኛው ቅዱስ እስጢፋኖስ ነበር፡፡ ሐዋርያትም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጭነው ጥቅምት 17 ቀን ሊቀ-ዲያቆናት አድርገው በሰባቱ ዲያቆናት ላይ ሾሙት፡፡

 ከዚያን ዕለት ጀምሮ ዲያቆናት የሐዋርያትን ቤተ ክርስቲያን ማገልግል ጀመሩ፡፡ ዲያቆን ማለት አገልጋይ ማለት ሲሆን በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ለድሆች በትክክል እርዳታ ለማድረስ፣ በማዕድም ለማገልገል ተመርጠው ነበር፡፡ በኋላም እየቆየ ዲቁና በቤተ ክርስቲያን እንደ አንድ ማዕርግ ሆነ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ዲያቆናት ጠባይና አገልግሎት በመልእክቱ ጽፏል፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስ በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ምልክትና ተዓምራትን ያደርግ ነበር፡፡ ብዙ አይሁድም ሲከራከሩት የሚናገርበትን መንፈስ መቋቋም ግን አልቻሉም ነበር፡፡

#ቅዱስ_እስጢፋኖስ_በአህዛብ_ፊት_ያደረገው_ተአምራት:-
ሊቀዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ በአህዛብ መካከል ቆሞ ሲያስተምር ከቆየ በኋላ አንድ አንደበቱ ዲዳ የሆነ ሰው አጠገቡ ቢመጣ በጆሮው የህይወት እስትንፋስ እፍ ቢልበት መስማት የማይችለው መስማት ቻለ፡፡ በዚህም ጣኦት አምላኪውን ናኦስ እና ተከታዮቹ ሁሉ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተመለሱ፡፡

ጣኦት አምላኪው ናኦስ በድርጊቱ በጣም በመናደዱ የተነሣ በአጠገቡ የቆመውን በሬ ልክ ናኦስ በጆሮው ቢተነፍስበት በሬው በምትሃት ለሁለት ተሰንጥቆ በመሞቱ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተመለሱት በናኦስ ምትሃታዊ ድርጊት በመሣባቸው እንደገና ወደ ናኦስ ተመለሱ፡፡ የአህዛብ ልቡና ወላዋይ እንዳይሆንና እንዳይጠፉም በማሰብ ናኦስ ለሁለት ሰንጥቆ የገደለውን በሬ በእግዚአብሔር ኃይልና ድንቅ ሥራ ደግሞ ህይወት ዘርቶ ማስነሳት እንደማይችሉ በማስተማር ልቦናቸው ወላውሎ ወደ ናኦስ የተመለሱትን አህዛብ ገንዘቡ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ኃይልነት እንዲያምኑ አድርጓል፡፡

ናኦስ በአልሸነፍ ባይነትና በአጋንንት ረዳትነት ራሱን ወደ ላይ እንዲንሣፈፍ አድርጎ በአየር ላይ ቢወጣ ቅዱስ እስጢፋኖስ የእግዚአብሔርን ተአምር በማሳየት በትዕግስት ጠብቆ በአጋንንት ረዳትነት ወደ ላይ የተነሳውን ናኦስ በትምዕርተ- መስቀል ቢያማትብበት ይዘውት የነበሩት አጋንንት ሁሉ ለቀውት ሲበተኑ ናኦስም ምድር ደርሶ ተንኮታኩቶ በመውደቁ በጣኦት አምላኪነት የነበሩ ሁሉ ዳግም ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተመልሰዋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
48 viewsbisrat, 12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 15:24:48
38 viewsbisrat, 12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 22:04:35
50 viewsbisrat, 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 22:04:05 # ጥቅምት_15_የ12ቱ_ቅዱሳን_ሐዋርያት_
የዕረፍታቸው_መታሰቢያ_ነው ።
ለሐዋርያት ሞት/ሰማዕትነት ምክንያትና መንሻ
ነው የምንለው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ
በመመስከራቸው ነው። የ12ቱን የቅዱሳን
ሐዋርያት ምስክርነታቸውንና አሟሟታቸውን
በቅደም ተከተል እንመልከት፦
# 1_ሐዋርያው_ያዕቆብ => ከ ክርስቶስ ሞትና
ትንሣኤ በኋላ ከእስጢፋኖስ ቀጥሎ
የመጀመርያው ሰማዕት ነው። አሟሟቱን
በሐ.ሥራ 12፥2 በግልፅ ተፅፏል። ንጉሥ ሄሮድስ
በሐዋርያት ላይ መከራ ያፀናበት ጊዜ ነበር።
ያዕቆብም በሰይፍ አንገቱ ተቆርጦ ተገደለ።
ይህም የሆነው ከክርስቶስ እርገት በኃላ 44-45
አመት አከባብ እንደተሰዋ ይነገራል።
# 2_ሐዋርያው_ጴጥሮስ => ቅዱስ ጴጥሮስ
ከክርስቶስ ስቅለት በፊት ክርስቶስን
እንደማያውቀው ቢክድም ከክርስቶስ እርገት
በኋላ ግን ስለ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ
ለመጀመርያ ጊዜ የሰበከው ጴጥሮስ ነው!
ኢየሱስ በዮሐ.21፥8-19 እንደተናገረው
ሐ.ጴጥሮስ ዳግመኛ ለመካድ እንቢ በማለቱ
በሮም ከተማ በሮማውያን እጅ እንደ ክርስቶስ
ልሰቀል አይገባኝም ብሎ ቁልቁል ተስቅሎ
ሞቷል! ይህም ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ በ64
አመት ነበር።
# 3_ሐዋርያው_እንድሪያስ ፦ ወንድሙ ጴጥሮስ
ከተሰዋ ከ6 ዓመት በኋላ በ70ኛው ዓ.ም በ ×
ቅርፅ መስቀል በግሪክ ተሰቅሎ ተገድሏል። 7
ወታደሮች በብርቱ ከገረፉት በኃላ ሥቃዩን
ለማስረዘም በማሰብ በ × መስቀል ላይ ሆኖ
ይህን ይናገር ነበር "ይህችን አስደሳች ዕለት
በጉጉት ስጠብቅ ነበር ለእኔ በመስቀል መሞት
ክብሬ ነው፤ ምክንያቱም መስቀልን ክርስቶስ
በሥጋው ተሰቅሎበት ቀድሶታልና" እያለ 2 ቀን
ለወታደሮች ይሰብክ ይመሰክር ነበር።
# 4_ሐዋርያው_ቶማስ => የክርስቶስን ትንሣኤ
በሐዋርያት ሲነገር አላምንም ያለውና በኋላም
ኢየሱስ ተገልጦ ችንካሩንና የተወጋ ጎኑን
በመዳሰስ ያመነው ሐዋርያ ሲሆን ይህንንም
ለመመስከር ወደ ህንድ ሀገር በሄደ ጊዜ እንደ
ጦር በተዘጋጀ የዛፍ እንጨት ወጋግተው ደግሞም
በጋለ ብረት ካሰቃዩት በኋላ በሕይወት ሳለ
እንዲቃጠል ተደርጎ ተሰዋ። ይህም ከክርስቶስ
ትንሣኤ በኋላ በ70ኛው ዓመት አከባቢ ነበር።
# 5_ሐዋርያው_ፊልጶስ => ክርስቶስን "አብን
አሳየንና ይበቃናል" ያለው ነው። ዮሐ.14፥8።
የክርስቶስን ሞት በመካከለኛውና ምዕራባዊው
እስያ ከሰበከ በኋላ በአመፀኛ ዩሑዳዎች ተይዞ
ከባድ ድብደባና ግርፋት ከተቀበለ በኋላ
በስቅለት ከክርስቶስ ትንሣኤ በኃላ በ54 ዓመት
ተሰውቷል።
# 6_ሐዋርያው_ማቴዎስ => ቀድሞ ቀራጭ
የነበረ ሲሆን አይሁዳውያን ክርስቶስን እንዲቀበሉ
በብርቱ ይፈልግ ነበር ከመሞቱ ከ10 አመት
ቀደም ብሎ የማቴዎስ ወንጌልን ፅፏል። ማቴዎስ
በማቴ.ወ 28፥20 እንደፃፈው ኢየሱስ የሰጠውን
የወንጌል ተልዕኮ በመወጣት በሰይፍ
እስከተሰዋበት ዕለት ድረስ ይሰብክ ነበር። ይህም
የሆነው ከ ክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ከ60 እስከ 70
አመት ነበር።
# 7_ሐዋርያው_ናትናኤል /በርተሎሜዎስ=>
ናትናኤል ከበለስ በታች ሳለ ነበር ፊልጶስ
የጠራው፤ ኢየሱስም ስለናትናኤል ሲናገር
"ተንኮል የሌለበት የእስራኤል ሰው" እንደሆነ
ምስክሮ ነበር፤ ናትናኤልም ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ልጅና የኢስራኤል ንጉሥ እንደሆነ
ተናግሮ እንደነበር ዮሐ.ወ 1፥45-50 ተገልጿል።
ናትናኤልም በኢስያ ምሽነር ) ባሁኗ ቱርክ
የክርስቶስን ትንሣኤ አብሥሯል። በኋላ ግን
በአርመኒያ እጅግ አስቃቂ በሆነ ሞት ቁም ስጋው
ተገፎ, አንገቱ ተቀልቶ, ከ ክርስቶስ ዕርገት በኃላ
በ70 አመት ተሰውቷል።
# 8_ሐዋርያው_ያዕቆብ /የኢየሱስ ወንድም
ያዕቆብ=> ከክርስቶስ ሞት በኋላ ለበርካታ
ዓመታት በኢየሩሳሌም መሪ ሆኖ አገልግሏል፤
በወቅቱ ክርስቶስን አሳልፎ የሰጡትና የገደሉት
ሰዎች ያዕቆብ የክርስቶስን ትንሣኤ እንዲክድ
ያስገድዱት ነበር። እነዚህም አይሁዳውያን
በማቴ.ወ 27፥25 ላይ የተጠቀሱት ናቸው።
በኋላም ያዕቆብ የክርስቶስን ትንሣኤ አልክድም
ብሎ በመወሰኑ ከቤተ መቅደስ ህንፃ አናት ጫፍ
ላይ ወደታች ወርውረውት ባለ መሞቱ
እየተገረሙ ጭንቅላቱን በቆልማማ ዱላ
ደብድበውት ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ በ60
ዓመት ተሰውቷል። ይህም በቤተ መቅደስ ጫፍ
ሰይጣን ኢየሱስን ወስዶት የፈተነበት ስፍራ ነው።
# 9_ሐዋርያው_ስምኦን => እስራኤላውያንን
ከሮማውያን እጅ ለማስለቀቅ ብዙ ይተጋ ነበር፤
የክርስቶስን ትንሣኤ በአይኑ ከተመለከተ በኋላ
የወንጌል አርበኛ በመሆን በግብፅ, በሰሜን
አፍሪካ, በቢታንያ, በሊቢያ, በፓርሻ መልካም ዜና
አብስሯል። ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ በ74 ዓመት
በስቅለት ተሰውቷል።
# 10_ሐዋርያው_ይሁዳ ጌታን የሸጠው ይሁዳ
ሳይሆን የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ=> የክርስቶስን
ትንሣኤ በሜሶፖታምያ በአሁኑ ኢራቅ ከሰበከ
በኃላ በማያምኑ ሰዎች በበትር ተመቶ ከ
ክርስቶስ ትንሣኤ በኃላ በ72ኛው ዓመት ሰማዕት
ሆኗል።
# 11_ሐዋርያው_ማትያስ => በአስቆሮቱ ይሁዳ
ቦታ የተተካው ሐዋርያ ነው። በሐ.ሥራ 1፥26 ላይ
እናገኘዋለን። ኢየሱስ 2 2 ሆነው ለምስክርነት
ለመሄድ ከተመረጡ ከ70ዎቹ መካከል 1 ነው
ብለው አባቶች ይናገራሉ፤ ይህም እውነት በሉቃስ
10፥1 ተፅፏል። ማትያስም ከክርስቶስ ትንሣኤ
በኋላ በ70ኛው ዓመት ተሰቅሎ ሳለ በድንጋይ
ተውግሮ ሞቷል።
# 12_ሐዋርያው_ዮሐንስ => ሐዋርያውን ከሀገር
አውጥተው ፍጥሞ በምትባል ደሴት ለእስር
ሰጡት፤ በዚህችም ደሴት ኢየሱስ መልአኩን ልኮ
የመጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻውን ክፍል/ራእይ
ዮሐንስን እንዲፅፍ ነገረው። ራእይን ከፃፈ በኋላ
ከእስር ተፈቶ በቱርክ ጳጳስ ሆኖ አገልግሏል።
ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በህይወተ
ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ
፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ
ነዉ፡፡ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹‹‹ዮሐንስ እኔ
እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ
ምን አግዶህ??›››ዮሐ 21፡20 ይህም እስከ
ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነዉ፡፡በማቴ
16፡18 ላይ ‹‹እዉነት….……ሞትን የማይቀምሱ
አንዳንድ አሉ›››››ያለዉ ቃል ለቅዱስ ዮሐንስና
መሰሎቹ የተነገረ ቃል ነዉ፡፡
"በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን
ጽኑ እኔ ዓለምን ድል ነሥቼዋለሁና።"
ዮሐ.15፥33
እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ሐዋርያት በረከታቸውን
ያድለን አሜን አሜን አሜን!!! ወስብሐት
ለእግዚአብሔር ወለ ወላድቱ ድንግል ወለ
መስቀሉ ክቡር አሜን አሜን አሜን!!!
50 viewsbisrat, 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 18:59:35
60 viewsbisrat, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ