Get Mystery Box with random crypto!

ዝክረ ብሒለ አበው

የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የሰርጥ አድራሻ: @behileabew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 345

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-06 20:26:56 #ምን_ዓይነት_ጸሎት_በየትኛው_ሰዓት_እንጸልይ?

ልበ አምላክ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ዳዊት”ስብዓ ለእለትየ እሴብሐከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ ፣ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለው”/መዝ 118-164/ብሎ እንደተናገረ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሰባት ጊዜ በየእለቱ እንዲጸልይ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ሰባቱ የጸሎት ጊዜያትም የሚከተሉት ናቸው:-
 
#1_ጸሎተ_ነግህ
ቅዱስ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ” መዝ 62÷11 እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ፣ከመኝታችን ስንነሳ ምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ጸሎተ ነግህ ይባላል፡፡በዚህ ጊዜ የሚከተሉትን ምስጢራት እያሰብን መጸለይ ይገባናል፡፡
#ሀ-ሌሊቱን አሳልፎ ቀኑን ስለተካልን እያመሰገንን ወጥተን እስክንገባ በሰላም ጠብቆ ውሎአችንን የተባረከ እንዲያደርግልን እንጸልያለን።
#ለ-የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑ ያንን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ የሰውን ልጅ በመዓልትና በሌሊት የሚጠብቁ መላእክት ለተልዕኮ ሲፋጠኑ የሚገናኙበት ሰዓት ነው፡፡
#ሐ-የሌሊቱ መልአክ ሲሄድ የቀኑ መልአክ ሲቀርብና ሲተካ የሚገናኙበት በመሆኑ በዚህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡
#መ-ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ አደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑ እንጸልያለን።

#2_ጸሎተ_ሠለስት (3 ሰዓት)
ከነግህ በመቀጠል የምንጸልየው ጸሎት ጸሎተ ሠለስት (የሦስት ሰዓት) ጸሎት ይባላል፡፡ይህ የጸሎት ጊዜ:-
#ሀ-ሔዋን የተፈጠረችበት 
#ለ-እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማችበት
#ሐ-ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት
#መ-ነቢዩ ዳንኤል ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ መልሶ የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት
#ሠ-ለአባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት /በኢየሩሳሌም ጸንተው በመቆየታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህንን ታላቅ ጸጋ የተቀበሉበት /ሰዓት ነው፡፡

#3_ቀትር (6 ሰዓት)
በእለቱ እኩሌታ ላይ የምናገኘው ይህ ሰዓትም እንደዚሁ የጸሎት ጊዜ ነው፡፡ይህም ጊዜ:-
#ሀ-ሰይጣን አዳምን ያሳተበት
#ለ-በዕፀ በለስ ምክንያት ለስሕተት የተዳረገውን አዳምን ለማዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ የዋለበት
#ሐ-የቀን እኩሌታ በመሆኑ የፀሐይ ሙቀት የሚያይልበት የሰው ልጅ ለድካም የሚዳረግበት በዚህም ምክንያት አጋንንት የሚበረታቱበት ጊዜ ነው። .ስለዚህ የአዳምን ስሕተት፣ የዳግማዊ አዳም የኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልና መሞት፣እያሰብን የቀን እኩሌታ በመሆኑ መዳከማችንን ተገን አድርጎ አጋንንት እንዳይሰለጥንብን እየለመንን እንጸልያለን፡፡

#4_ተሰዓተ_ሰዓት (9 ሰዓት)
ዘጠኝ ሰዓት ላይ አራተኛውን ጸሎት እናደርሳለን።በዚህ ጊዜ:-
#ሀ-ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነጻ ለማውጣት በፈቃዱ ቅዱስ ሥጋውን ከቅድስት ነፍሱ የለየበት ሰዓት ነው።
#ለ-ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን በጎም ሆነ ክፉ ተግባር ወደ ፈጣሪ የሚያሳርጉበት ነው
#ሐ-ቆርኖሌዎስ የተባለ መቶ አለቃ በጸሎት ጸንቶ ደጅ ሲጠና ከሰነበተ በኋላ ከፈጣሪው ምላሽ ያገኘበት ሰዓት ነው (ሐዋ 10÷ 9) በዚህ ጊዜ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ሞት አያሰብን ቅዱሳት መላእክት ከፈጣሪያቸው እንዲያስታርቁን እየለመንን የቆርኖሌዎስ እድል እንዲገጥመን እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡

#5_ጸሎተ_ሰርክ (11 ሰዓት)
አምስተኛው የጸሎት ጊዜ የሠርክ ጸሎት ነው፡፡ ስለዚህ የጸሎት ሰዓት ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፡፡”ጸሎቴን እንደ ዕጣን በፊትህ ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን” (መዝ 140 ÷2) በዚህ ጊዜ:-
#ሀ-ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ወደ መቃብር የወረደበት ሰዓት ነው፡፡ (ማቴ. 27÷ 57)

#6_ጸሎተ_ንዋም (የመኝታ ጊዜ ጸሎት)
ይህ ጊዜ ዕለቱን በሰላም አሳልፈን ለሌሊቱ ዕረፍት የምንዘጋጅበት ነው፡፡በሰላም ላዋለን ፈጣሪ በሰላም አሳድረን ብለን ራሳችንን በእምነት የምናስረክብበት ነው፡፡እኛ ተኝተን የሚሆነውን አናውቅም እርሱ ግን የማያንቀላፋ እረኛ ስለሆነ ይጠብቀናል።ስለዚህ ከመተኛታችን በፊት ሊሌሊቱን እንዲባርክልን እንጸልያለን። በዚህ ጊዜ፡-
#ሀ-ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ ዛሙርቱን በጌቴሴማኒ ጸሎት አስተምሯቸዋል፡፡ ቀኑ አልፎ በሌሊቱ ይተካል ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጸሎት ማስተማሩን እያሰብን እንጸልያለን፡፡
#ለ-ሰላም አሳድረንም ብለን ለፈጣሪ ራሳችንን በእምነት አደራ እናስረክባለን፡፡

#7_መንፈቀ_ሌሊት (እኩለ ሌሊት)
እኩለ ሌሊትም እንደ ቀናቱ የጸሎት ሰዓታት የተለያዩ ትርጉሞች አሉት ። ቅዱሰ ዳዊት ‘’መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ”“ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ዘንድ እነሳለሁ”/መዝ 118-62/በማለት ይህ ሰዓት ከእግዚአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት እንደሆነ ገልጿል፡፡ በዚህ ጊዜ:-
#ሀ-ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት ሰዓት ነው።
#ለ-ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ ኃይልም የተነሳው በሌሊት ነው።
#ሐ-ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ለፍርድ ሚመጣበትም ሰዓት ነው። ከዚህ የተነሳ ለእኛ ሲል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን በማሰብ ሞትን ድል እንደነሳልንም አስበን በማመስገን ዳግመኛ ለፍርድ ሲመጣ በቀኙ ከሚያቆማቸው ወገን እንዲያደርገን እየለመንን በዚህ ሰዓት እንጸልያለን፡፡

#ሰባቱን_የጸሎት_ጊዜያት_ጠብቀን_መጸለይ_ካልተቻለንስ?
በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት የታቻለንን ያህል እንድንጸልይ ታዘናል፡፡እነዚህን የጸሎት ሰዓታት በገዳም ያሉ መነኮሳት በየበረሃው የሚዞሩ ባሕታውያን ይጠብቋቸዋል፡፡ይጸልዩባቸዋልም፡፡ በከተማ በሥራ ምክንያት ሩጫ በዝቶበት በሁሉም ሰዓት መጸለይ የማይችል ክርስቲያን ግን ቢያንስ በማለዳ ከእንቅልፉ ሲነሳ እና ማታ ወደ መኝታው ሲያመራ መጸለይ ይገባዋል።ጠዋት እና ማታ በመጸለይ ከፈጣሪ ጋራ ያለው የአባትና ልጅ ግንኙነት እንዳይቋረጥ ማድረግ ይገባዋል፡፡

#ምን_እንጸልይ?

በመደበኛነት ልንጸልያቸው የሚገቡ ጸሎታት / በቤተክርስቲያናችን አባቶች በገዳማቱ በአድባራቱ የሚዘወተሩ እለታዊ ጸሎታት/ እነኚህ ናቸው:-

#1_መዝሙረ_ዳዊት
መዝሙረ ዳዊት በገዳማት ከሚኖሩ አበው መነኮሳት ባህታውያን ጀምሮ በካህናት፣ምእመናን በሁሉም ዘንድ በየእለቱ የሚጸለይ ጸሎት ነው።አባቶች ከፊደል ቆጠራው ቀጥሎ ዳዊቱን ያጠኑና ከዚህ ጊዜ ጀምረው እየደገሙት፣እየጸለዩበት ይኖራሉ።ዳዊት ሳይደግሙ ወደ ዕለታዊ ተግባራቸው አይሰማሩም።መዝሙረ ዳዊት እንደሌሎች ጸሎታት ሁሉ በየዕለቱ ተለይቶ የሚጸለይ አለው።

ቀጥለን እንመልከት ሰኞ ከ 1 – 30፣ማክሰኞ ከ 31 – 60፣ረቡዕ ከ 61 – 80፣ሐሙስ ከ 81 – 110፣አርብ ከ 111 – 130፣ቅዳሜ ከ 131 – 150 እሁድ- ጸሎተ ነቢያት እና መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ይጸለያል፡፡ አንድ ንጉሥ መዝሙረ ዳዊትን ስንጸልይ ለዕለቱ የታዘዘውን ሃያ እና ሰላሳ መዝሙር ማድረስ ባንችል እንኳን አንድ ንጉሥ ማድረስ ይገባናል። አንድ ንጉሥ የሚባለው፡-አስር መዝሙር ነው፡፡ለምሳሌ ሰኞ አንድ ንጉስ ለማድረስ ከፈቀዱ ከ 1 – 10 ያለውን ያደርሳሉ፡፡ከማክሰኞ ከሆነ ደግሞ ከ 30
124 viewsbisrat, 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 19:17:32
43 viewsbisrat, 16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 19:15:24 #ጥር_29_የ2015_ዓ_ም_ጾመ_ነነዌ_የሚጀምርበት_ዕለት።

እግዚአብሔር ለሕዝቡ መልእክት ለማስተላለፍ ወደ ሕዝቡ ከላካቸው ነቢያት መከካል አንዱ ነቢዩ ዮናስ ነው፡፡
ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው።
ታዲያ አንድ ቀን ፣ ወደ አንዲት ታላቅ ከተማ ሔዶ እንዲሰብክ የእግዚአብሔር ቃል ለነቢዩ ዮናስ መጣለት፡፡ ይህች ታላቅ ከተማ ነነዌ ትባላለች፡፡ በዚህች በነነዌ ከተማ የሚኖሩ ሰዎች ኀጢአታቸው እጅግ በዝቶ ነበር፡፡ ርኅሩኁ አምላካችን እግዚአብሔር የሰውን መዳን እንጂ ጥፋቱን ስለማይፈልግ ንስሐ ግቡ ብሎ እንዲያስተምራቸው ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ላከው፡፡ ነቢዩ ዮናስ ግን የፈጣሪውን ትእዛዝ ላለመፈጸም ሊኮበልል አሰበ፡፡ ከዚያም ተርሴስ ወደምትባል አገር የምታልፍ መርከብ አግኝቶ በእርሷ ተሳፈረ፡፡ ከእግዚአብሔር ፊት መኮብለል ወይም መሸሽ አይቻልም።

ነቢዩ ዮናስ በመርከብ ተሳፍሮ ሲሔድም እግዚአብሔር ታላቅ ነፋስን አምጥቶ በባሕሩ ላይ ታላቅ ማዕበልን አስነሣ፡፡ በዚህ ጊዜ መርከቢቱ ልትሰበር ደረሰች፡፡ ይህ ሁሉ የደረሰው ነቢዩ ዮናስ ከእግዚአብሔር ፊት ለመሸሽ በማሰቡ ነው፡፡ መርከቢቷ ውስጥ ያሉ ሰዎችም እጅግ ፈሩ፡፡ መርከቧ ክብደት ስለበዛባት ነው ብለው አስበው በውስጧ የነበረውን ዕቃ ዅሉ ወደ ባሕር ቢጥሉትም መርከቢቱ ግን ልትረጋጋ አልቻለችም ነበር፡፡ ማዕበሉም አልቆም አለ፡፡

ይህ ዅሉ ሲኾን ግን ነቢዩ ዮናስ ተኝቶ ነበር፡፡ ከዚያም የመርከቡ አለቃ ወደ እርሱ ቀረበና ‹‹ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን እንደኾነ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ›› አለው፡፡ በመርከቡ ውስጥ ያሉት ሰዎችም ‹‹ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እናውቅ ዘንድ ኑ ዕጣ እንጣጣል›› ተባብለው ዕጣ ሲጣጣሉ ዕጣው በነቢዩ ዮናስ ላይ ወጣ፡፡ ሰዎቹም ነቢዩ ዮናስን ‹‹ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እባክህ ንገረን?›› አሉት፡፡ ነቢዩ ዮናስም ከእግዚአብሔር ፊት መኮብለሉን በነገራቸው ጊዜ ሰዎቹ በፍርኀት ኾነው ‹‹ይህ ያደረግኸው ምንድን ነው?›› አሉት፡፡ ባሕሩንም ሞገዱ እጅግ ያናውጠው ነበርና ‹‹ባሕሩ ጸጥ እንዲል ምን እናድርግብህ?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹‹ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁ፡፡ አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፡፡ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል፤›› አላቸው (ትንቢተ ዮናስ ፩፥፩-፲፫)፡፡ ሰዎቹም ነቢዩ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ በዚህ ጊዜ ባሕሩ ከመናወጥ ጸጥ አለ፡፡

ባሕሩ ሲናወጥ የነበረው ዮናስ እግዚአብሔር ያዘዘውን ትቶ ለመሸሽ በመርከቡ በመሳፈሩ ነው! እግዚአብሔርን ሳንታዘዝ ያሰብንበት ቦታ መድረስ አንችልም፡፡ ምክንያቱም ዓለሙን ዅሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነውና በባሕርም ኾነ በየብስ (በደረቅ መሬት) ብንጓዝ ከእርሱ መሰወር ፈጽሞ አይቻለንም፡፡ እግዚአብሔር የሌለበት ቦታና ከእርሱ እይታ የተሰወረ ምንም ነገር የለምና፡፡

እናም ሰዎቹ ነቢዩ ዮናስን ወደ ባሕር ሲጥሉት እግዚአብሔር ያዘጋጀው ታላቅ ዓሣ ዋጠው፡፡ ነቢዩ ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ቆየ፡፡ ነቢዩ ዮናስም እግዚአብሔር እንዲያወጣው በዓሣው ሆድ ውስጥ ኾኖ አብዝቶ ጸለየ፡፡ እግዚአብሔርም የነቢዩ ዮናስን ጸሎት ሰምቶ ዓሣውን እንዲተፋው አዘዘው፡፡ ዓሣውም ነቢዩ ዮናስን በየብስ (በደረቅ መሬት) ላይ ተፋው፡፡ ነቢዩ ዮናስም ‹‹ይህቺ አገር ማን ትባላለች?›› ብሎ የአካባቢው ነዋሪዎችን ሲጠይቅ አገሪቱ ነነዌ እንደ ኾነች ነገሩት፡፡ ከዚህ በኋላ ነቢዩ ዮናስ የእግዚአብሔርን ቃል እሺ ብሎ ተቀብሎ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ገብቶ ‹‹በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለባበጣለች (ትጠፋለች)›› ብሎ አስተማረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ቃሉን ሰምተው ከኀጢአታቸው ተመልሰው፣ ማቅ ለብሰው ንስሐ ገቡ፡፡ ከከንጉሡ ጀምሮ ሕፃናትም ጭምር፣ እንስሳትም ሳይቀሩ ምንም ምግብ ሳይቀምሱ፣ ውኀም ሳይጠጡ ለሦስት ቀን ጾሙ፡፡ እንዲምራቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው መመለሳቸውንና ንስሐ መግባታቸውን አይቶ ይቅር አላቸው፤ ነነዌንም ከጥፋት አዳናት፡፡ ነቢዩ ዮናስ እግዚአብሔርን አልታዘዝም ያለው እኔ ነነዌ ትገለባበጣለች (ትጠፋለች) ብዬ ባስተምር ሕዝቡ ተጸጽቶ ይቅርታ ቢጠይቁ እግዚአብሔር ይቅር ሲላቸው እኔ ውሸታም ነቢይ እባላለሁ ብሎ ፈርቶ ነበር፡፡ ነገር ግን የነነዌ ሰዎች ነቢዩ ዮናስንም ውሸታም ነው አላሉትም፡፡ ትምህርቱን ተቀብለው ከጥፋት በመዳናቸው እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡ እግዚአብሔር ምን ያህል ሩኅሩኅና ቸር እንደኾነ በዚህ ታሪክ እንረዳለን።
ምንም እንኳን እኛ ብንበድለውም፣ ብናሳዝነውም ተጸጽተን ንስሐ ከገባን የቀደመውን በደላችንን ደምስሶ ኀጢአታቻንን ይቅር ይለናል፡፡

ነነዌ ከመቶ ሃያ ሺሕ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሳት የሚኖሩባት ታላቅ ከተማ ነበረች፡፡ እነኚህ ዅሉ ሰዎች ንስሐ ባይገቡ ኖሮ ነነዌን እሳት ይበላት ነበር፡፡ የነነዌ ሰዎች ከበደላቸው ተጸጽተው፣ ንስሐ ገብተው በመጾማቸውና በመጸለያቸው እግዚአብሔር ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡
እኛም ዛሬ እግዚአብሔርን በድለነዋል እርሱ የማይወደውንም ክፋት ፈጽመናል። ስለዚህ እንደ ነነዌ ሰዎች ተጽጽተን ንስሐ ከገባን አምላካችን ቸር፣ ታጋሽ እና ይቅር ባይ አምላክ ስለኾነ ኀጢአታችንን ይቅር ብሎ ከጥፋት ያድነናል፡፡ እኛ ክርስቲያኖች በየዓመቱ ጾመ ነነዌን የምንጾመውም እግዚአብሔር ኀጢአታቻንን ይቅር እንዲለን ነው፡፡ ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይኹን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
52 viewsbisrat, 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 17:14:31 የሰአትና የቦታ ለውጥ የመንበረ ቅዱሳን ወሳኝ መርሃግብርን እንድንታደም እኛ 7:00 በቅድስት ማርያም (አምስት ኪሎ) እንገናኝ። አለ መቅረት ማትረፍ ነው አሁን ወቅቱ 24 ሰዓት ከቤተክርስቲያን አይናችንን አንንቀል።
24 viewsእሱበ ዐይናለም, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 22:05:10 እሁድ ፍፁም መቅረት አይቻልም ብንችል ጓደኞቻችንን ሰብሰብ አርገን እንገናኝ ።
የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ አይነት ምክንያታችሁ ለወቅቱ አይመጥንም።
8:30 አራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ እንገናኝ
20 viewsእሱበ ዐይናለም, 19:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 22:04:40 ያባቶቻችንን ድምፅ እንስማ የነነዌን ፆም ጥቁር በመልበስ እንፁም እንፀልይ
21 viewsእሱበ ዐይናለም, 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 20:20:27
43 viewsbisrat, 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 20:19:29 #ቤተክርስቲያን_እና_የሐዋርያቱ_ታንኳ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌው ሕሙማነ ሥጋን በተአምራት ሕሙማነ ነፍስን በትምህርት ይፈውስ ነበር። ከዕለታት በአንደኛው ቀን ይህንኑ የዕለት ተዕለት ተግባሩን ሊፈጽም ደቀ መዛሙርቱን ብቻ አስከትሎ ባሕሩን ተሻግሮ ወደ ጌርጌሴኖን ከተማ ሊሄድ ወደ አንዲት ታንኳ ገባ። የዚህን ጊዜ ታንኳ የመቅዘፍ፤ የመዋኘት፤ ዓሳ የማስገር ልምድ ያላቸው እነ ቅዱስ ጴጥሮስ ከፊት ሆነው ታንኳዋን ይቀዝፉ ጀመር። በባሕሩም እንብርት ሲደርሱ ታንኳዋ ከባድ ችግር አጋጠማት ጽኑዕ የሆነ አውሎ ነፋስ ተነሳ ታንኳይቱም በውሃ እስክትሞላ ለመሰባበርም እስክትደርስ በታላቅ ማዕበል ተመታች።

ደቀ መዛሙርቱም የነፍስ አድን ጩኸታቸውን አሰሙ። ጌታችን ግን በስተኋላ ባለው የታንኳይቱ ክፍል ትራስ በመንተራስ ተኝቶ ነበር። ጌታችን በባህርይው መተኛት ኖሮበት ሳይሆን የሚደክም የሚተኛ ሥጋን መልበሱን ሲያጠይቅ ነው። እርሱ በባህሪው ለቅጽበት ተኝቶ አያውቅም።
መጽሐፍ እንዲህ ይላል " እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም።" (መዝሙረ ዳዊት 120:4)

ደቀመዛሙርቱም የችግራቸው መፍቻ ቁልፍ በጌታችን መሆኑን ተረድተው ቀሰቀሱት እንዲህም አሉት ''ጌታ ሆይ አድነን እንጂ የእኛ መጥፋት አይስጨንቅኽም ወይ'' ጌታችንም ''እናንተ ሃይማኖት የሌላችሁ ምን ያስፈራችኋል፤ ከእርሱ ጋር ሳለን ጥፋት አያገኘንም በእርሱ ስም አምነን እንድናለን አትሉም'' ብሎ ገሰጻቸው ነፋሱንም ገሰጸው ባህሩን ደግሞ ''ዝም በል ጸጥ በል'' ወዲያውኑም ነፋሱ አምላኩን ታዞ ቀጥ አለ በአካባቢውም ታላቅ ሰላም ሰፈነ  ይህን ተአምር ሲመለከቱ የነበሩ ሁሉ በአድናቆትና በፍርሐት ስሜት "እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? ተባባሉ። " (የማርቆስ ወንጌል 4:35-41)

በዚህ የወንጌል ክፍል
ታንኳይቱ - የቤተክርስቲያን
ደቀመዛሙርቱ - የካህናትና የምዕመናን ባሕሩ - የዓለም
ነፋሱና ማዕበሉ - የፈተና እና የመከራ
ምሳሌ ናቸው።

ስለዚህ ጌታችን ባለበት ቅድስት ቤተክርስቲያን የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ያለ የሌለ ኃይላቸውን በመጠቀምና በመተባበር ሊያፈርሷት ሊንዷትና ሊያጠፏት ከምንግዜውም በላይ ቆርጠው ተነስተዋል።

እኛም ልጆቿ የችግራችን መክፈቻ ቁልፍ  በእርሱ ዘንድ ነውና አምላካችንን ''ጌታ ሆይ አድነን በደምህ የዋጅሃት ቅድስት ቤተክርስቲያን ስትጠፋ አይገድህምን'' እንበለው።

''ሰውን ብትታገልና ብትዋጋ ታሸንፈዋለህ ወይም ያሸንፍሃል፤ ቤተክርስቲያንን ግን ማሸነፍ አይቻልም፤ ቤተክርስቲያን ሁልጊዜ ትዋጋለች ተሸንፋም አታውቅም፤  ዲያብሎስ ዝናሩን አራገፈ ቀስቱን ጨረሰ ቤተክርስቲያንን ግን አልጎዳትም'' (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!!
44 viewsbisrat, 17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 19:09:01
25 viewsbisrat, 16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 19:06:49 #ጥር_24_ቀን_አቡነ_ተክለሃይማኖት_ከተጋድሎ_ብዛት_የተነሣ_አንድ_እግራቸው_ተቆርጦ_የወደቀበት_ዕለት_ነው።

አቡነ ተክለ ሃይማኖት የመጀመሪያ ስማቸው ፍስሓ ጽዮን ይባላል ፤ እናታቸው እግዚእ ኀረያ አባታቸው ደግሞ ጸጋ ዘአብ ይባላል፡፡ የተወለደት በሸዋ ምድር ጽላልሽ (ዝራሬ) በተባለው ቦታ ነው ፤ በተወለደ ዓመት ከሦስት ወር ሲሆናቸው በሀገራቸው ረሀብ ሆነ፡፡ እናታቸው እግዚእ ኀረያም ‹‹የቅዱስ ሚካኤል በዓል ሉታጎልብን ነው?›› በማለት ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ በዚህ ሰአት ሕፃኑ ፍስሓ ጽዮን በልጅ እጆቹን የእናቱን እንባ ለመጥረግ ሲሞክር ፤ እግዚእ ኀረያ ጡት የፈለገ መስሎት ጡት ብትሰጠው ፤ ጡቱን ትቶ ወደ ቤት እንድታስገባው እናቱን ያለከትታ ጀመረ፡፡እርሷም ሕፃኑን ወደ ቤት ይዚው ገባች ፤ ሕፃኑም እፍኝ ደቄት ያለበት የደቄት ማስቀመጫ ውስጥ ሕፃኑ እጆቹን ቢጭንበት ፤ ደቄት ፈሞልቶ ፈሰሰ፡፡ እርሷም በተአምሩ ተደንቃ እግዚአብሔርን እያመሰገነች የደቄት እቃዎቿን ሁሉ አቀረበች ፤ ሕፃኑም እያንዳንደ ላይ ጠብ ጠብ ቢያደርግበት ሁሉም ሞልቶ ተገኝቷል ፤ ሌሎች የቅዱስ ሚካኤል ዝክር ለመዘከር የሚያስፈልጉ ነገሮችን ሁሉ በሕፃኑ እጅ ተዳሶ ሞልቶላታል፡፡ ባልና ሚስት ይህንንም ድንቅ ሥራ እያደነቁ ፤ ዝክሩን ለመጋቢት 12 አዘጋጅተው ለብዙዎች አብልተው አጠጥተው ፤ እነርሱም የረሀቡ ዘመን እስኪያልፍ ድረስ እየተመገቡ ኖረዋል፡፡ ፍስሓ ጽዮን ሰባት ዓመት ሲሞላቸው አባታቸው ወደ አብነት ትምህርት ቤት ወስደው ሕይወት ብነ በጽዮን ለተባለ መምህር ሰጥተዋቸው ሄደ ፤ ፍስሓ ጽዮን እግዚአብሔር በሰጣቸው ብሩህ አዕምሮ ብዙ መጻሕፍትን ተምረው ከአቡነ ጌርልስ ዲቁናን ተቀበለ፡፡ ፍስሓ ጽዮን ለአቅመ አዳም በደረሰ ጊዜ ሚስት ፈልገው ቢያመጡለት ፤ ፈቃደኛ አለመሆኑን በመግለጥ ሸሽቶ ሄደ፡፡ እናቱና አባቱም ብዙ ሳይቆዩ በአምስት ዓመት ልዩነት ሁለቱም አረፉ ፤ ፍስሓ ጽዮንም በነገሩ በጣም አዘነ፡፡

ከእለታት አንድ ቀን በልጅነቱ በተማረው የአደን ልምድ ፤ ወደ ጫካ ገብቶ ሉያድን ባለበት ሰአት ፤ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት የሚድንበትን ጦር እንደያዘ ከአንድ ዛፍ ሥር ቁጭ አለ፡፡ በዚህ ሰአት እግዚአብሔር በራእይ ተገልጾለት እንዲህ አለው ‹‹ሐዲስ ሐዋርያ እንድትሆን መረጥሁህ ከእንግዲህም ነፍሳትን እንጂ እንስሳትን አራዊትን አታድንም ፤ ስምህም ተክለ ሃይማኖት ይባላል›› አለው፡፡ (ተክለ ሃይማኖት ማለት ተክለ አብ ፤ ተክለ ወልድ ፤ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡) አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ከእንቅልፍ በነቁ ጊዜ የያዘት ጦር መስቀል ሆና አገኟት ፤ ተነሥተውም ልዋል ልደር ሳይለ መንፈሳዊ ሥራን ጀመሩ፡፡ በሸዋ ውስጥም እየተመላለሱ በስሕተት መንገድ የሚሄደትን የእግዚአብሔር ልጆች በንስሓ መመለስ ጀመሩ ፤ እንዲህ ባለ አገልግሎት ለብዙ ጊዜያት አገለገለ፡፡

በአንድ ወቅት ከተታ ወደተባለ አውራጃ ደርሰው በወንጌል እመኑ ክርስትናን ተወበለ ብለው ቢያስተምሩ ፤ የአውራጃው ሕዜብ ‹‹አምላካችንን ትተን አይሆንም›› አላቸው ፤ ጻድቁም ‹‹ማንን ታመልካላችሁ?›› አሏቸው፡፡

ሕዜቡም ‹‹ብንቸገር የሚረዳን ብንታመም የሚያድነን ዛፍ አለ›› አላቸው፡፡ ጻድቁም ‹‹እንግዲያውስ እኔም እንድሰግድለት ካለበት አድርሱኝ›› ብለው አብረዋቸው ሄደ ፤ በቦታው ሉደርሱ ጥቂት ሲቀራቸው በዚያ ዛፍ ያደረ ሰይጣን ‹‹ይሄን ሰው መልሱልኝ›› እያለ መጮኽ ጀመረ ፤ ሕዜቡም ‹‹እንግዲያውስ አምላካችን አልወደደህም በዚህ ቆዩ›› አላቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም እኔ መ ቅረቤን ካልወደደ ራሱ ይምጣ ብለው በእግዚአብሔር ስም እንዲመጣ አዘዘት ፤ በዚህ ጊዜ ከእነ ዛፉ ተነቅል ፤ ዛፉ አካባቢ የሚሰግደትን ሰዎች ገድል ከፊታቸው ቆመ ፤ ጻድቁም ሰይጣኑን ከዛፉ ላይ አርቀው ፤ የሞቱትን ሰዎች አስነሥተው ፤ በአካባቢው ያለውን ሕዜብ አስተምረው ስምንት ሺህ የሚሆኑ ነፍሳትን አጥምቀዋል፡፡በአንድ ወቅትም እንዲሁ ንጉሥ ሞተለሚ በነገሠበት በምድረ ዳሞት ሄደው ሲያስተምሩ ፤ ንጉሡ አስይዝአቸው ‹‹ከወዳት መጣህ ምን ልታደርግስ መጣህ?›› ባላቸው ጊዜ ፤

‹‹አማልክትህን እንዳጠፋ ከእግዚአብሔር ተልኬ መጥቻለሁ›› አለት ፤ እርሱም ተናድድ በቀፎ አስሮ ጦመ ግራርያ የሚባል ገደል በጭፍሮቹ አስጣላቸው ፤ ሉቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በክንፎቹ ጠብቆ ከተላኩት ጭፍሮች አስቀድሞ ንጉሡ ፊት አደረሳቸው፡፡ ሁለተኛ ጊዜ ቢያስጥላቸው እንደቀድመው ከፊቱ ቆሙ ፤ በዚህ ተበሳጭቶ ጦሩን አንሥቶ ቢወረውረው ጦሩ ከእጁ ተጠቀለለበት ፤ ለሁለተኛ ጊዜም ቢወረውር ጦሩ በእጁ ተጠቅልል ቀረ ጽኑ ሕመምም አመመው ፤ በቤተ መንግሥቱ ያለ የጣዖት ካህናት መጥተው ሕመሙን ሉያርቁለት ጦሩን ሉያላቁለት ቢሞክሩም አልቻለም ፤ ኋላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸልየው ከሕመሙ አድነውታል ፤ እርሱም ጣዖት አምልኮ ሐሰት እንደሆነ አይቶ ካህናተ ጣዖቱን በሰይፍ አስፈጅቷቸዋል ፤ በወንጌል አምኖም ተጠምቋል፡፡ ጻድቁ በዚህ አካባቢ እንዲህ ባለ አገልግሎት ለ12 ዓመታት ቆዩ፡፡

ከዚህም በኋላ በአማራ ክልል ሄደው በአባ በጸልተ ሚካኤል ገዳም እህል እየፈጩ ውሃ እየቀደ እንጨት እየሰበሩ ይልቁንም ሕሙም እየፈወሱ ለ10 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በመቀጠልም ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም በመሔድ ምንኩስናን ተቀብለው በጸልት በጾም ተወስነው ለ10 ዓመት ኖረዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ጻድቁ አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞ ገዳም በመሔድ አባ ዮሐኒ ከተባለት አባት ከፍ ያለውን የምንኩስና ክብር ተቀበለ

፤ ለ10 ዓመት በዚያ አገልግለው ከደብረ ዳሞ ለመውጣት በደብረ ዳሞ ተራራ መወጣጫ ገመድ ላይ ሆነው ሲወርደ ፤ ለክፉ ሥራ የማይተኛ ሰይጣን ገመደን በጠሰባቸው ፤ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ስድስት የጸጋ ክንፍ ሰጣቸው፡፡ በተሰጣቸውም የጸጋ ክንፍ ኢየሩሳሌም ሦስት ጊዜ በመመላለስ ተሳልመዋል፡፡ በኋላም በደብረ ሊባኖስበዓት ሠርተው አጋንንትን በመዋጋት ሃይማኖትን እያስተማሩ ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሰዋል፡፡ ጻድቁ በበዓታቸው ገብተው ስምንት ጦሮችን ከፊት ከኋላ ከግራ ከቀኝ ተክለው ለብዙ ጊዜ ሱባኤ ይዘዋል፡፡ ብዙ ከመቆምና ከመጋደል ብዛት የተነሣም ጥር 24 ቀን አንድ እግራቸው ተቆርጦ ወድቋል፡፡ ከዚህም በኋላ በአንድ እግራቸው ቆመው ለሰባት ዓመታት ስለ ሀገራቸው ኢትዮጵያና ስለ ሕዜቦቿ ጸልየዋል፡፡ በመጨረሻም የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ ጌታችን እመቤታችንን መላእክትን ነቢያትን ሐዋርያትን ሰማዕታትን ጻድቃንን አስከትል መጥቶ

‹‹ወዳጄ ተክለ ሃይማኖት ሆይ ልመናህ ሰምቼ ከድካምህ ላሳርፍህ መንፈሳዊ ደስታ ካለበት ላስገባህ መጣሁ ፤ ሁለተኛ ሞት አያገኝህም በተስፋህ ያመነውን በቃልኪዳንህ የተማጸነውን ሥጋህን የቆረስክበትን ደምህን ያፈሰስክበትንም ቦታ እጅ የነሳውን ሁሉ ገሃነም ከመውረድ አድንልሃለሁ ፤ በዚህም ቦታ በተስፋህ ጸንተው በኪዳንህ ተማጽነው የሚኖሩ ልጆችህን እንደ ሰማይ ኮከብ እንደ ምድር አሸዋ አበዛልሃለሁ፡፡›› በማለት ተስፋና ብዙ ቃል ኪዳንን ሰጣቸው፡፡ ለጻድቁም በጽኑ ሕመምና ደዌ እንደሚሞቱ ነግሯቸው ተሰወረ፡፡

ጻድቁም በተነገራቸው መሠረት በሕመም ተይዘው በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን አረፉ፡፡ በረከታቸው በሁላችን ላይ ትደርብን!!!
26 viewsbisrat, 16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ