Get Mystery Box with random crypto!

ዝክረ ብሒለ አበው

የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የሰርጥ አድራሻ: @behileabew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 345

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2022-04-17 14:12:30
159 viewsbisrat, 11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 14:11:34 ሰሙነ ሕማማት

በአምላካችን በጌታችንና በመድኃኒታችን
በኢየሱስ ክርስቶስ ደም በተመሠረተችው እና
ሐዋርያት ባጸንዋት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ
በተለያዩ ጊዜ የተነሡትና በተለያዩ ጊዜያት ጉባኤ
ዘርግተው ሃይማኖታዊ ውሳኔ የደነገጉት ሊቃውንተ
ቤተ ክርስቲያን በጸሎተ ሃይማኖት ላይ "ከዚህ
በኋላ በሥጋ ታመመ፣ ሞተ፣ ተቀበረ..." በማለት
ሕማሙንና ሞቶ መቀበሩን ከጻፉልንና ካስተማሩን
በመነሣት አባቶቻችን ከሆሣዕና ማግስት ጀምሮ
እስከ ትንሣኤ ዋዜማ ያሉትን ቀናት"ሰሙነ
ሕማማት" ብለው ሰይመውታል። በመሆኑም
እኛም አባቶቻችን በእነዚህ ስድስት ቀናት
የጌታችንን ሕማሙን በማሰብ በታላቅ ጸሎት፣
ስግደትና ጾም እንድናሳልፍ መጽሐፍ ጽፈው፣
ጸሎት አዘጋጅተውና ሥርዓት ሠርተው
ሰጥተውናል። እያንዳንዱ የዓቢይ ጾም ሳምንት
የእራሱ መጠሪያ እንዳለው እነዚህም ስድስት
ቀናት የየእራሳቸው የሕማሙና የሞቱ መታሰቢያ
ስላላቸው እንደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት
ክንዋኔአቸውን በአጭሩ እናቀርባለን፦
ሰኞ፦ በዚህ የመጀመርያው ዕለት
+ ኢየሱስ ክርስቶስ ከቢታንያ ወደ ቤተ መቅደስ
ማምራቱ፤
+ ፍሬ አልባ የሆነችውን በለስ መርገሙ (ማቴ.
፳፩ ማር ፲፩)፤
+ ቤተ መቅደሱን ከገንዘብ ለዋጮች ማንጻቱ፤
+ በቤተ መቅደስ ማስተማሩና ተአምራት ማድረጉ
እንዲሁም በቢታንያ ማደሩ ይነገራል።
ማክሰኞ፦ በዚህ በሁለተኛው ዕለት
+ ኢየሱስ ክርስቶስ ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም
መሄዱና የረገማት ቅጠል ከነሥሯ ደርቃ
እንዳያት፤
+ ለሕግ ጠባቂዎችና መምህራን ፈሪሳውያንና
የአይሁድን ትምህርት ለተማሩ የጥቂት
ሰዱቃውያንን ጥያቄ መመለሱ፤
+ ስለ ዳግም ምጽአቱና ስለ ቤተ መቅደሱ
መፍረስ ማስተማሩ፤
+ ስለ ወይኑ ቦታና ስለ ሠራተኞቹ፣ (ማቴ. ፳፩)
ስለ ንጉሡ ልጅ ሠርግ(ማቴ. ፳፪) ስለ
ልባሞቹና ስለ ሰነፎቹ ደናግል በምሳሌ
ማስተማሩ፤
+ በድጋሚ ወደ ቢታንያ ስለ መመለሱ ይነገራል።
(ማቴ. ፳፮)
ረቡዕ፦ በዚህ በሦስተኛው ዕለት
+ ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሙሉ
ቀን በቢታንያ ስለማሳለፉ፤
+ ኃጢአተኛዋ ሴት መዓዛው የጣፈጠ ሽቱ
በጌታችን ላይ ስለማፍሰስዋ
(ማቴ. ፳፮) (ይኽቺም ሴት በጌታችን እግር
ላይ ዘይት እያፈሰሰች በፀጉሯ ያበሰችው
የአልዐዛር እኅት ማርያም አይደለችም) እና
+ የአስቆሮቱ ይሁዳ በሠላሣ ዲናር ጌታን አሳልፎ
ለመስጠት ከአይሁድ ጋር መስማማቱ፤
+ ካህናተ አይሁድ ሊይዙት መምከራቸው
ይነገራል።
ሐሙስ፦ በዚህ በአራተኛው ዕለት
+ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ለፋሲካ
የሚሆነውን እራት እንዲያዘጋጁ ነግሯቸው
ስለማዘጋጀታቸውና የደቀ መዛሙርቱን እግር
አጥቦ የምሥጢረ ቁርባንን ሥርዓት
መሥራቱ፦ እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ
ቆርሶም ሰጣቸውና። ስለ እናንተ የሚሰጠው
ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ
አድርጉት አለ። እንዲሁም ከእራት በኋላ
ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ። ይህ ጽዋ
ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን
አዲስ ኪዳን ነው።(ሉቃ. ፳፪፡፲፱-፳)
+ የኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ጸሎት
ማድረግ፦ አባት ሆይ፥ ብትፈቅድ ይህችን
ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ
አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር።
(ሉቃ. ፳፪፡፵፪) መባሉ ይነገራል።
አርብ፦ በዚህ በአምስተኛው ዕለት
+ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳም በበደለ ጊዜ ከሳሽ
ዲያብሎስን በአንተና በሴቲቱ መካከል፥
በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን
አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥
አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ። (ዘፍ.
፫፡፲፭) በማለት የገባለት ቃል መፈጸሙ፤
+ ስለ ጌታ መያዝ፣ መገረፍ፣ መሰቃየትና
መሰቀል ይነገራል። በቤተ ክርስቲያንም
ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከሚደረገው ስግደት
በበለጠ ነገረ መስቀሉን በማሰብ በጸሎትና
በስግደት ዕለቱ ይከበራል።
ቅዳሜ፦ በዚህ በስድስተኛው ዕለት
+ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሙታን እንደሰበከላቸው
በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥
በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት
ሰበከላቸው፤ (፩ጴጥ. ፫፡፲፰) እንዲል።
ከዚህ በተጨማሪም በኖኅ ዘመን ስለ ውኃው
መጉደል ርግብ የለመለመ ቅጠል ይዛ
እንደመጣች የቅዳሜ ስዑር ዕለትም ካህናት
"ክርስቶስ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ።" በማለት
ለሕዝቡ የለመለመ ቄጠማ ያድላሉ። ምክንያቱም
በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትም የኃጢአት ባሕር
እንዲሁ ተወግዷልና። ይኽ ዕለት ቅዳም ስዑር
ይባላል። ትርጓሜውም "የተሻረ" ማለት ነው።
ይኸውም ቅዳሜና እሑድ ጾም የማይገባ ሆኖ
ሳለ ጌታ በከርሠ መቃብር ስላደረ በአክፍሎት
ስለሚጾም ቅዳም ስዑር ይባላል።
እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሐ
ወበሰላም።
183 viewsbisrat, 11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 08:21:10
221 viewsbisrat, 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 08:20:49 ቢያዎች
አቋቁመው በየዓመቱ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ
ችግኞች በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሰበካና
ለሕዝባውያን ድርጅቶች እንዲከፋፈሉ
በማድረጋቸው የተራቆቱ መሬቶች በዛፎች
እንዲዋቡ ጥረዋል፡፡
መ/ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
በማስፈቀድ በማኅደረ ማርያም የሐዲሳት፣
የድጓና የቅዳሴ ት/ቤት አሠርተው ለመምህራኑ
ከ50 እስከ 200 ብር ደመወዝ እንዲከፈላቸው፣
ለደቀ መዛሙርቱ ድጎማ እንዲሰጣቸው
አድርገዋል፡፡
ሠ/ ጥንታዊውንና ታሪካዊውን የጣና ቂርቆስ
ገዳም በብር 8ሺሕ835 እንዲታደስ አድርገዋል፡፡
በጣና ለሬማ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ብር
4ሺሕ ረድተዋል፡፡ የደረሞ ቅዱስ ሚካኤልን ቤተ
ክርስቲያን ብር 21ሺሕ 114 በማውጣት
አሳድሰዋል፡፡ እንዲሁም ጥንታዊውን የግርቢ
ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በብር 8ሺሕ860 ብር
እንዲታደስ አድርገዋል፡፡ በአዘዞ በሰሚ ቅዱስ
ሚካኤል ወደ ካህናቱ ማሠልጠኛ የሚወስደው
መንገድ በምግብ ለሥራ መርሐ ግብር እንዲሠራ
አድርገዋል፡፡
በጎንደር መንበረ መንግሥት ጥበበ እድና የአዳሪ
ቤቱ ዙሪያ ርዳታ በመጠየቅ ከ9ሺሕ በላይ
በማወጣት እንዲሠራ አድርገዋል፡፡ በጎንደር
ጉባኤ ቤትና የዶክተር አየለ ዓለሙ የመቃብር
ቤት የአራቱ ጉባኤያት ሥዕል እንዲሠራበት
አድርገዋል፡፡ በሊቦ አውራጃ በቆላ እብናት
ለአምራቾች የኅብረት ሥራ ማኅበር ብር 15 ሺሕ
ረድተዋል፡፡ በጎንደር ከተማ በአዘዞ አባ ሳሙኤል
በመጠለያ ለሚረዱ ከልማትና ክርስቲያናዊ
ተራድኦ መምሪያ ጋራ በመተባበር የኤልክትሪክ
ምጣድ ርዳታ አድርገዋል፡፡ በዳባት ወረዳ
የሚገኘውን የደፍቂ ቅዱስ ሚካኤልን በብር
5ሺሕ፣ ቆማ ፋሲለደስን በብር 5ሺሕ
አሳድሰዋል፡፡ ለአምስትያ ገዳም ብር 4ሺሕ፣
ለጣርክ ማርያም ብር 7ሺሕ ረድተዋል፡፡
ዐደባባይ ኢየሱስም በብር 40ሺሕ እንዲታደስ
አድርገዋል፤ የድምፅ ማጉያም አስገብተውለታል፡፡
በጎንደር ዙሪያ አውራጃ ለቸንከር ተክለ ሃይማኖት
ርዳታ በመጠየቅ ብር 764ሺሕ አበርክተዋል፡፡
በዚያው በጎንደር ዙሪያ ከማክሰኝት እስከ አርባያ
ለመንገድ ሥራ ብር 30ሺሕ ርዳታ እንዲገኝ
አድርገዋል፡፡ ከእብናት እስከ ጎሐላ ለመንገድ
ሥራ የብር 6ሺሕ ርዳታ እንዲገኝ አድርገዋል፡፡
በስሜን አውራጃ ለሚገኙ ጥንታውያን ገዳማት፤
ለቤተ ሚናስ ዋልድባ ከብር 10ሺሕ በላይ፤
ለጣዕመ ክርስቶስ ብር 10ሺሕ፣ ለሰቋር ዋልድባ
ብር 4ሺሕ ግምት ያላቸው የቁሳቁስ(የዓይነት)
ርዳታ አድርገዋል፡፡
በጎርጎራ ገዳም በደሴተ ጣና ለሚገኙ ገዳማት፤
ለማን እንዳባ ገዳም ብር 1ሺሕ880፤ ለብርጊዳ
ማርያም ገዳም ብር 1ሺሕ ለበሬ መግዣ
እንዲሰጥ አድርገዋል፡፡
ከልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ መምሪያ ርዳታ
ሰጪ ድርጀቶች በመጠየቅ አቅም በፈቀደ መጠን
በተወሰኑ አብያተ ክርስቲያናት የቆዳ፣ የሽመና፣
የሹራብ ሥራ፣ የልብስ ስፌት፣ የወፍጮ ቤትና
የዳቦ ቤት እንዲቋቋምና አገልግሎት እንዲሰጡ
አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም ለስብከተ ወንጌል፣
ለሰንበት ት/ቤትና ለሕዝብም መሰብሰቢያ
የሚያገለግሉ አዳራሾች በየአብያተ ክርስቲያናቱ
አካባቢ አሠርተዋል፡፡ ሕዝቡ ንጹሕ ውኃ ማግኘት
እንዲችል የውኃ ጉድጓድ በማስቆፈር ለዚሁ
የሚያገለግል ሞተርና ቧምቧ እንዲያገኙ
የበኩላቸውን ጥረዋል፡፡
ለሀገረ ስብከቱ ያስገኟቸው ሽልማቶች ፤
የሰበካ ጉባኤ ቃለ ዐዋዲ ደንብ በትክክል
እንዲፈጸም በማድረጋቸውና ሰበካ ጉባኤን
በሚገባ በማደራጀታቸው፣ በየዓመቱ በሚደረገው
የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ
ዓመታዊ ስብሰባ የሥራ ግምገማ በተደረሰበት
ውጤት የጎንደር ሀገረ ስብከት ቅድሚያ ቦታ
እንዲይዝ አድርገዋል፡፡
በዚህም መሠረት፡- ከ16ቱ አህጉረ ስብከት፣
ከ1975 እስከ 1977 ዓ.ም. በተከታታይ እንዲሁም
በ1979 ዓ.ም. አንደኛ፤ በ1978 ዓ.ም. ኹለተኛ
በመኾን በውጤታማነት እንዲሸለም አድርገዋል፡፡
ብፁዕነታቸው፣ ከዚህ በላይ ጠቅለል ባለ መልክ
በተዘረዘረው ዓይነት ተልእኳቸውን በትክክል
የተወጡ አባት ከመኾናቸውም በላይ በ1979
ዓ.ም. በተደረገው የብሔራዊ ሸንጎ አባላት
ምርጫ በጎንደር ዙሪያ አውራጃ ምርጫ ጣቢያ
ደንቢያ ከመረጠው 26ሺሕ127 ሕዝብ መካከል
17ሺሕ249 ድምፅ በማግኘት ተመርጠው
ሕዝብን አገልግለዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ፣ የበላዮቻቸውን መካሪ፣
የበታቾቻቸውን አክባሪ፣ በሥራ ታታሪ፣ መንፈሳዊ
አባትነታቸውና ትሑት ሰብእናቸው አርኣያነት
ያለው ቁጥብ አባት ናቸው፡፡
ለፕትርክና በከፍተኛ ድምፅ የተመረጡበት ኹኔታ ፤
ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ለ11 ዓመታት ያህል
በመጀመሪያ በኦጋዴን አውራጃ ኤጲስ ቆጶስ
ቀጥሎም በጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
በመኾንና በቅዱስ ሲኖዶስ አባልነት
አገልግለዋል፡፡ ለፕትርክና ምርጫው በተዘጋጀው
ደንብ አንቀጽ 2 መሠረት፡- የትምህርት
ዝግጅታቸው፣ ገዳማዊ ሕይወታቸው፣ የአስተዳደር
ችሎታቸው፣ የመንፈሳዊና ማኅበራዊ
አገልግሎታቸው፣ ሥነ ምግባራቸው ተመዝኖ
ብቃትና አርኣያነት ያላቸው አባት ኾነው
በመገኘታቸው በዕጩነት ተመርጠዋል፡፡
የመራጭ አባላት ቁጥር፤
በምርጫው ደንብ መሠረት፣ 32 የቅዱስ ሲኖዶስ
አባላት፣ 7 የአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት፣ 48 የአህጉረ
ስብከት ሰበካ ጉባኤያት ሥራ አስፈጻሚ
ኮሚቴዎች ተወካዮች፣ 22 የቀደምት የአንድነት
ገዳማትና ታላላቅ አድባራት ተወካዮች በድምሩ
109 መራጮች ነሐሴ 22 ቀን 1980 ዓ.ም.
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ተገኝተው
ድምፅ ሰጥተዋል፡፡
በዕጩነት ከቀረቡት ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል፣
ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ፣ 66 ከፍተኛ ድምፅ
በማግኘት፣ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ኾነው ለመመረጥ
በቅተዋል፡፡ ሢመተ ፕትርክናቸው ነሐሴ 29 ቀን
1980 ዓ.ም. የተፈጸመ ሲኾን፣ 4ኛ ፓትርያርክ
በመኾን ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡ በፖሊቲካዊ
ግፊትና ጫና መንበራቸውን እስከለቀቁበት፣
ነሐሴ 28 ቀን 1983 ዓ.ም. ድረስም፣ ለሦስት
ዓመታት ለቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ አባታዊ
አመራር ሰጥተዋል፡፡
196 viewsbisrat, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ