Get Mystery Box with random crypto!

ዝክረ ብሒለ አበው

የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የቴሌግራም ቻናል አርማ behileabew — ዝክረ ብሒለ አበው
የሰርጥ አድራሻ: @behileabew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 345

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-10-08 16:25:01
44 viewsbisrat, 13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 16:24:56 መስከረም 29 ቅድስት አርሴማ ሰማዕት የሆነችበት ዕለት ነው።

እናታችን ቅድስት አርሴማ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን ከሆኑ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ብሉይን ሐዲስን ተምራ እያነበበች እንዲሁም በተግባር እየተረጎመች ዘወትርም በጸሎት ትተጋ እንደነበር ገድሏ ይተርካል፡፡ በዚህ ዘመን ድርጣድስ የሚባል በአርመን የነገሠ አረማዊ ንጉሥ ለጣዖት የሚሰግድ' ፀሐይንም የሚያመልክ' ክርስቲያኖችንም እኔ ለማመልከው አምላክ መስገድ አለባችሁ በማለት መከራ ያጸናባቸው ነበር፡፡ እናታችን ቅድስት አርሴማም ተጋድሎዋን የጀመረችው የዚህ ጨካኝ ንጉሥ አገልጋይ ወይም ሹም ፳፯ ክርስቲያኖችን እንደልማዱ እየደበደበ' እየገረፈና ልዩ ልዩ ስቃይ እያደረሰባቸው ሲወስዳቸው በማየቷ ነበር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‘‘ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን ስለኔ ወደገዢዎችና ወደ ነገሥታት ትወሰዳላችሁ፡፡’’ (ማቴ. ፲፡፲፮፡፲፱)፡፡ ያለውን በማሰብ ቅድስት አርሴማም ገና በሃያ ዓመቷ የዚህን ዓለም ንጉሥ እኩይ ግብሩን በመንቀፍ ስለ ክርስቶስ ከሚሰቃዩ ወገኖቿ ጋር ግንባር ቀደም በመሆን ትመሰክር ጀመር፡፡ የንጉሡም አገልጋይ በደም ግባቷና በንግግሯ ማማር ተደንቆ በዚች በፈቃዷ ልትሠዋ በወደደች ሴት ምንም ሊያደርግባት ስላልወደደ ወደ ንጉሡ ወደ ድርጣድስ ከሃያ ሰባቱ ክርስቲያኖች ጋር ወሰዳት፡፡ ንጉሡም ብዙ የተነገረላትን ወጣት ሲያይ በውበቷና በንግግሯ ተማርኮ ለዓለማዊ ደስታውና ፍላጎቱ ተመኛት፡፡ ለእርሱም ሙሽራ እንድትሆን ብዙ ወተወታት፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን ናቀችው ‘‘እኔ የሰማያዊው ንጉሥ የክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የዚህን ዓለም አላፊ ጠፊ የሆነውን ገንዘብና ደስታ የምሻ አይደለሁም፡፡’’ በማለትም መለሰችለት፡፡ ንጉሡም ይህንን ከእርሷ በመስማቱ እጅግ ተቆጣ፤ በመናቁም ተበሳጨ፤ አሽከሮቹንም ጠርቶ በቤተ መንግሥቱ የታሰሩትን አንበሶች እንዲለቀቅባቸው አዘዘ፡፡ አንበሶቹ ግን ይደሰቱ ነበር፡፡ በኋላም ፊታቸውን ወደ ንጉሡና አገልጋዮቹ በማዞር ሩጠው እስኪደበቁ ድረስ አሳደዷቸው፡፡ ንጉሡ ይበልጥ ነደደው ክርስቲያኖቹ በረሃብ እንዲያልቁ እንዲታሰሩ አዘዘ፡፡ እግዚአብሔርም በአምስተኛው ቀን በብርሃን ቤቱን ሞልቶት የሚበሉትን በመሶብ የሚጠጡትን በጽዋ ከሰማይ አወረደላቸው፡፡ ንጉሡም ይህንን በማየቱ ከዚያ አውጥቶ በእሳት ውስጥም አስገባቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅን የጠበቀ አምላክ እነርሱንም አዳናቸው፡፡ በሌላም በብዙ መንገድ ሊያጠፋቸው እንደሞከረ ገድሏ ይተርካል፡፡ በመጨረሻም ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ በሰይፍ እንዲያልቁ ይወስናሉ፡፡ እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ሲሰይፋቸው ቅድስት አርሴማ ለሚሰየፉት ሁሉ የድል አክሊል ከሰማይ ሲወርድላቸው ትመለከት ስለነበር የእርሷን ተራ በጉጉት ትጠብቀው ነበር፡፡ በመደሰቷም እየጸለየች አይዟችሁ ጽኑ ትላቸው ነበር፡፡ በመጨረሻም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጽናቷን ተመልክቶ ቃል ኪዳን ይገባላታል፡፡ ንጉሡም ሌሎቹን አሰይፎ ሲያበቃ ወደሷ ዞሮ በቁጣ እየጮኸ አንቺን እንደ ባልንጀሮችሽ በቀላሉ አልገልሽም ስቃይሽን አጸናብሻለሁ ብሎ ለአገልጋዮቹ ትእዛዝ በመስጠት አይኗን አስወጥቶ በእጇ ያሲዛታል፤ ጡቷን ያስቆርጣል፤ በኋላም አንገቷን ያሰይፋታል በዚሁ ሁኔታ እናታችን ሰማዕትነትን ተቀበለች፡፡ ይህንን ሁሉ መከራ ስለአምላኳ ስትል እራሷን አሳልፋ የሰጠች ድንቅ ሰማዕት ናት፡፡ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ ‘‘ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ’’ (መዝ.) እንዳለ ለእናታችን ቃል ኪዳን ገብቶላታል። የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በረከትና ረድኤት በእኛ ላይ ጸንቶ ይኑር!!! አሜን
60 viewsbisrat, 13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 19:43:46
60 viewsbisrat, 16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 19:43:36 #መስከረም_26_አስቸጋሪው_ወርሃ_ክረምት_አልቆ_አስደሳቹ_ወርሃ_ጽጌ_ይጀምራል።

ሕፃኑን እና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሸሽ፡፡” (ማቴ 2፣13)

ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ከመስከረም 26 - ኅዳር 6 ያለውን ወቅት ዘመነ ጽጌ ትለዋለች፡፡ /የአበባ ወራት ማለት ነው፡፡/ አበቦች በምድር ላይ የሚያብቡበት ወቅት ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በአርባው ቀናት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እቅፍ እና ጀርባ ሆኖ፣ በዮሴፍ መሪነት ከምድረ እስራኤል ወደ ግብጽ መሰደዳቸው ይታሰባል፡፡ በዛሬው ትምህርታችን የስደቱን ታሪክ እና በቤተ ክርስቲያን ለስደቱ መታሰቢያ የሰየመችውን ወቅት ከሥርዓቱ ጋር እንማራለን፡፡

1.#የስደቱ_ምክንያት፡- ጌታችን በተወለደ በሁለተኛው ዓመት ሰብአ ሰገል በኮከብ ተመርተው “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከብን በምሥራቅ Aይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡” (ማቴ 2÷2) በዚህም ንጉሡ እና ኢየሩሳሌም ታወኩ፡፡ በወቅቱ በኢየሩሳሌም የነበረው ንጉሥም ሄሮድስ ይባላል፡፡ የካህናት አለቆችን፤ ክርስቶስ ወዴት እንደሚወለድ ጠይቆ፤ ሰብአ ሰገልን ጠርቶ ሲመለሱ መንገዳቸውን በእርሱ በኩል አድርገው፤ ‹‹እርሱም እንድሰግድለት ንገሩኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ቤተልሔም ሄደው በበረት የተወለደውን ጌታችንን አግኝተውት ፣ ሰግደው ፣ ስጦታ አቅርበው ፣ ሲመለሱ ÷ በሕልም ሄሮድስ ሊገድለው እንደሚፈልገው በሕልማቸው ተገለጠላቸውና በሌላ መንገድ ሄዱ፡፡ ሄሮድስ የመግደል ሐሳቡ እንዳልተሳካለት ሲያውቅ ሁለት ዓመት የሞላቸውን ሕፃናት በሙሉ ሰብስቦ አስገደለ፡፡

2. #ስደት ፡- በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ ሕፃኑን እና እናቱን ይዞ ፤ ወደ ግብጽ እንዲሸሽ ነገረው ፡፡ እስክነግርህም በዚያ ተቀመጥ አለው ፡፡ ሄሮድስም እስኪሞት ሦስት ዓመት ከስድስት ወር በዚያ ተቀመጡ፡፡ የበረሐው ሙቀት÷የውኃ ጥም እና የሄሮድስ ወታደሮች ክትትል ለሰብአዊ አእምሮ ከባድ ፈታናዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሄሮድስ ከነጥፋቱ ሞተ፡፡

3. #የስደቱ መታሰቢያ በቤተ ክርስቲያን፡- በቤተ ክርስቲያን ይህ የስደት ወቅት በየዓመቱ ይታሰባል፡፡ የስደቱ መታሰቢያ ወቅት በቅዱስ ያሬድ ዘመነ ጽጌ ይባላል ፡፡ ይህ ወቅት ከመስከረም 26 - ኀዳር 6 ቀን ሲሆን በምድር ላይ የሚገለጡት አበቦችን ለማመልከት የተሰጠው ስያሜ እና በዚህም ዘመናትን ለሚመግብ ጌታ ለእግዚአብሔር ምሥጋና የሚቀርብበት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ማሕሌተ ጽጌ እና ሰቆቃወ ድንግል የተባሉ መጻሕፍት በዜማና በንባብ ይደረሳሉ፡፡

#ማሕሌት:- (ምስጋና ማለት ነው፡፡) መዘምራን በቤተ ክርስቲያን በቀን እና በሌሊት ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ምስጋና ነው ፡፡ በዘመነ ጽጌ የጌታችንን ስደት የሚያመለክቱ ዜማዎች ይቀርባሉ፡፡

#ማሕሌተ_ጽጌ:- በቁሙ የጽጌ ምስጋና ማለት ሲሆን የጌታችንን እና የእመቤታችንን ስደት አስመልክቶ በአባ ጽጌ ድንግል የተደረሰ በያሬድ ዜማ የሚቀርብ ምስጋና ነው፡፡

#ሰቆቃወ_ድንግል:- (የድንግል ሐዘን ማለት ነው፡፡) ይሄም በአባ ጽጌ ድንግል የተደረሰ ሲሆን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጅዋን ከሄሮድስ ወታደሮች እና ከበረሐ ወንበዴዎች ለማዳን በስደቱ ወቅት ያሳለፈችውን መከራ በግጥም የሚያስታውስ መጽሐፍ ነው፡፡ በዚህ ወቅት በዜማ እና በንባብ ይደረሳል፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ሌሊት ለእሑድ አጥቢያ በየቤተ ክርስቲያኑ ማሕሌተ ጽጌ እና ሰቆቃወ ድንግል ይደረሳሉ፡፡

#ይህንን_ወቅት_ለመዘከር:- ምዕመናንም የወርኃ ጽጌን እሑዶች በየነፍስ አባቶቻቸው ተከፋፍልው አገልጋዬችን የሚያስተናግዱበት እና ችግረኞችን የሚመግቡበት ትውፊት አለ፡፡

#የፈቃድ_ጾም፡- በዚህ ወቅት የታወጀ ጾም የለም፡፡ ነገር ግን በገዳም ያሉ መነኮሳት እና መናንያን እንዲሁም አንዳንድ ምዕመናን የጌታችንን እና የእመቤታችንን ስደት ለማሰብ በፈቃዳቸው ይጾማሉ፡፡


ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳሳቢ።

ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ካገር ወደ አገር ከእርሱ ጋር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ።

ድንግል ሆይ ከአይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደው ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ።

ድንግል ሆይ ረኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኃዘኑን ከእርሱ ጋር የደረሰብሽን ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ።

ድንግል ሆይ ጥፋትን አይደል ይቅርታን አሳስቢ።

መዓትን አይደለ ምህረትን አሳስቢ።

ለጻድቃን አይደለ ለኃጥአን አሳስቢ።

ለንጹሐን አይደለ ለተዳደፉ አሰስቢ። አሁንም
አብንና ወልድን መንፈ ቅዱስን እናመሰግንዋለን ለዘላለሙ አሜን።

መልካም የጽጌ ወር!!!
117 viewsbisrat, 16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 18:00:13
69 viewsbisrat, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 17:59:21 #መስከረም_25_ዕረፍቱ_ለነቢየ_እግዚአብሔር_ዮናስ።

ዮናስ ማለት የዋህ ርግብ ማለት ነው፡፡ ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ነው፡፡ የተወለደው በሰራፕታ ነው፡፡ በዘመኑ የነበረ ነቢይ ኤልያስ ነው፡፡ ይህም ነቢይ በዘመኑ ንጉሥ አክአብ ንግሥቲቱ ኤልዛቤል 850 ነቢያተ ሐሰት ካህናተ ጣዖት አቁመው ጣዖት ሲያመልኩ ተው ቢሏቸው አልመለስም ቢሉ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማይ ዝናም እንዳይዘንም አድርጓል፡፡ 1ነገ.18፥1-46፤ ያዕ. 5፥17

ከዚህ በኋላ ምግቡን ያመላልሱለት የነበሩ ቁራዎች ቀርተውበት ውኃውም ደርቆበት ወደ ጌታ ቢያመለክት ‹‹ወደ ሰራፕታ ሂድ በዚያም አንዲት መበለት ሴት ትመግብሃለች›› ብሎት ሰራፕታ የዮናስን እናት አግኝቷት ‹‹ውኃ አጠጪኝ ጥቂት ቁራሽም አምጪልኝ›› አላት፡፡ ‹‹ሕያው እግዚአብሔርን እፍኝ ዱቄት አለችኝ ጋግሬያት አንተም እኔም ልጄም (ዮናስ) በልተናት እንሞታለን›› አለችው፡፡ ኤልያስም የረሀቡ ዘመን እስኪያልፍ ይበርክት አላት፡፡ ብትገባ ዱቄቱ በማድጋው ዘይቱ በማሰሮው መልቶ አገኘች፡፡

ልጅዋ ዮናስም ታሞባት በሞተ ጊዜ ሄዳ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስን ሳይገባኝ ከቤቴ ገብተህ ኃጢአቴን ተመራምረህ ልጄን ትገድልብኝ አለችው፡፡ እጁን ከእጁ እግሩን ከእግሩ ገጥሞ እየወደቀ እየተነሣ ቢጸልይ በሰባተኛው ተነሥቷል፡፡ 1ነገ. 17፥1-24

ዮናስ አርባ ዓመት ሲሞላው ሀብተ ትንቢት ተሰጥቶት ማስተማር ጀመረ፡፡ አንድ ጊዜ ጌታ ነነዌ ወርደህ ‹‹ነነዌ እስከ ሦስት ቀን ትጠፋለች ንስሓ ግቡ›› ብለህ አስተምር አለው፡፡ ዮናስም ‹‹እርሱ እንደሆነ ለቸርነቱ መስፈርት የለውምና ቢምራቸው ሐሳዊ ነቢይ ልባል አይደለምን?›› ብሎ ከፊቱ ለመሰወር ወደ ተርሴስ ሊሄድ መርከብ ተሳፈረ፡፡ በባሕሩ ማዕከል ሲደርሱ ጽኑ ማዕበል ተነሥቶ መርከበኞቹን አስጨነቃቸው፡፡ እሱም ከወደ ውስጥ ተኝቶ ነበር፡፡ ቀስቅሰው ‹‹ስንጠፋ ዝም ትላለህን?›› አሉት፡፡ ከእግዚአብሔር እንደሆነ አውቆ ‹‹እኔን አውጥታችሁ ጣሉኝ›› አላቸው፡፡ እነሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ንጹሕ ደም ልንጠፋ አይደለምን›› ብለው ዕጣ ተጣጣሉ በርሱ ላይ ወጣ፡፡ አውጥተው ጣሉት ማዕበሉም ጸጥ አለ፡፡
እሱም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በከርሠ ዐንበሪ ቆይቶ በሦስተኛው ቀን ዐንበሪው በነነዌ የብስ ተፋው፡፡ ከተማም ገብቶ ‹‹ሀገራችሁ እስከ ሦስት ቀን ትጠፋለች ንስሓ ግቡ›› እያለ አስተማረ፡፡ ንጉሡም የጾም አዋጅ አስነግሮ ከዙፋኑ ወርዶ ሕዝቡም ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው አዘኑ አለቀሱ፡፡ ሕፃናት ከጡት ከብቶችም ከሣር ተከልክለዋል፡፡ ዮናስ ይህን አይቶ እንግዲህማ ሊምራቸው ነው እኔም ሐሳዊ ነቢይ ልባል ነው ብሎ እያዘነ ከከተማ ወጥቶ ዳስ ሠርቶ ተቀመጠ፡፡ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት ተኘቶ ቢነቃ ከራስጌው ቅል በቅላ ፀሐይ ስትከላከለው አየ፤ ደስ አለው፡፡ ሁለተኛ ተኝቶ ቢነሣ ጠውልጋ ደርቃ አገኘ አዘነ፡፡ ጌታ ‹‹አንተ ላልተከልካት ውኃ ላላጠጣሃት ቅል እንዲህ ስታዝን አኔስ በዝናም አብቅዬ በፀሐይ አብስዬ ለምመግባቸው ሕዝቤ አላዝንምን?›› አለው፡፡ ፈቃዱንም ለመፈጸም /ሐሳዊ ነቢይ እንዳይሉት/ በሦስተኛው ቀን እሳት ከሰማይ ወርዶ ከፍ ከፍ ያሉትን ዕፅዋት ጫፍ ጫፋቸውን በልቷል፡፡ (ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1-4) 

ነቢዩ ቅዱስ ዮናስ በምድር ያለውን አገልግሎቱን ፈጽሞ መስከረም 25 ቀን በክብር አርፏል።

" ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።" (የማቴዎስ ወንጌል 10:41)

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
66 viewsbisrat, edited  14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:24:42
41 viewsbisrat, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:22:43 # ነሐሴ_24_እረፍቱ_ለጻድቅ_ተክለሃይማኖት
በመጽሐፍ ቅዱስ “ጻድቅ” የሚለው ቃል ሕግን
መፈጸም፣ እንደ ሕግ መኖርና መመራት፣
ትክክለኛነትን እና እውነተኛነትን ያመለክታል፡፡
“ጻድቅ” የሚለውም ቃል በሕግ የጸና፣ እንደ ሕግ
የሚኖር እውነተኛ ሰውን የሚወክል ቃል ነው፡፡
ሰዎች አካሄዳቸውን በእግዚአብሔር ፊት
ሲያደርጉና እንደ እግዚአብሔር ሕግ ሲኖሩ ጻድቃን
ይባላሉ፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትም
በእግዚአብሔር ፊት እንደ እግዚአብሔር ሕግ
የኖሩ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ናቸው፡፡ ጻድቁ
ተክለሃይማኖት እግዚአብሔርን ከሚወዱ እና
ከሚያከብሩ ከአባታቸው ጸጋዘአብ እና ከእናታቸው
እግዚእ ሐረያ ታኅሣሥ 24 ቀን ተወለዱ፡፡
ጸጋዘአብ ማለት የአብ ጸጋ ማለት ሲሆን እግዚእ
ሐረያ ማለት ደግሞ በጌታ የተመረጠች ማለት
ነው፡፡ ጸጋ ዘአብ እና እግዚአ ሐረያ እግዚአብሔርን
በፍጹም ልባቸው የሚያምኑ፣ በተለያየ ሕመም
የሚሰቃዩ እና ችግረኞችን የሚረዱ ደጋግ ሰዎች
ነበሩ፡፡ በተለይ ለእግዚአብሔር መልአክ ለቅዱስ
ሚካኤል የተለየ ፍቅር ስለነበራቸው በየወሩ
በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት በመታመን
የመልአኩን በዓል ድሆችን በመንከባከብ ያከብሩ
ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ቅዱስ ሚካኤል
በሕልም ተገልጾ እግዚአብሔር የተባረከ ልጅ
እንደሚሰጣቸው ነገራቸው፡፡ እግዚአብሔር
የሰጣቸውን ወንድ ልጅ ፍሥሐጽዮን ብለው
ጠሩት፡፡ ፍሥሐጽዮን ማለት የጽዮን ደስታ ማለት
ነው፡፡ ሕፃኑ ፍሥሐጽዮን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ
በሶስተኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ
ቅዱስ አሐድ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ
አመሰገነ፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበር
ፍሥሐጽዮን በልጅነቱ ብዙ ተአምራትን አድርጓል፡፡
በአንድ ወቅት ረሃብ ነበር ቤተሰቦቹ በዚህ
ምክንያት የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር እንዳያቋርጡ
ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ዱቄትና ዘይት
በማብዛት ቤተሰቦቹ ዝክሩን ያለምንም ችጋር
እንዲዘክሩ አድርጓል፡፡
ዝክር ማለት በእግዚአብሔር፣ በቅዱሳን እና
በመላእክት ስም የሚደረግ መታሰቢያ ነው፡፡
ፍሥሐጽዮን እግዚአብሔርን እያገለገለ አደገ፡፡
በዐሥራ አምስት ዓመቱ ከአቡነ ቄርሎስ ሁለተኛ
ዲቁና ተቀበለ፡፡ ወደ ቤት ሲመለስ ቤተሰቦቹ
አንዲት ሴት እንዲያገባት እንዳጩለት ነገሩት፡፡
ነገር ግን ፍሥሐጽዮን ይህን ጥያቄ
አልተቀበለውም ነበር፡፡ አንድ ቀን ፍሥሐጽዮን
ከጓደኞቹ ጋር ለአደን እንደወጣ መልአኩ ቅዱስ
ሚካኤል ተገልጦ ከዚህ በኋላ ያለውን ቀሪ
ዘመኑን የሰዎችን ነፍስ በማዳን እግዚአብሔርን
እንዲያገለግል መመረጡን ነገረው፡፡ መልአኩ
የፍስሐጽዮንን ስም ተክለሃይማኖት (የሃይማኖት
ዛፍ (ተክል)) ብሎ ለወጠው፡፡ ከዚህ በኋላ
ተክለሃይማኖት ወደቤቱ ተመልሶ ገንዘቡን ለቤተ
ክርስቲያን እና ለድሆች ሰጥቶ ወደ ገዳም ሄደ፡፡
በገዳም እያገለገለ እና እየተማረ የቅድስና
ማዕርግን ተቀበለ፡፡ በትጋት ወንጌልን በመስበኩ
ብዙ ሰዎችን ወደ ክርስትና ተመለሱ፡፡ በደብረ
ዳሞ ገዳም ለብዙ ዓመታት በአገልግሎት ከቆየ
በኋላ አንድ ቀን በገመድ ሲወርድ ገመድ ተበጥሶ
ሲጸልይ ክንፍ ተሰጠው፡፡
ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ሃያ ዘጠኝ ዓመታትን
ያሳለፈው ደብረ አሰቦ በተባለ ቦታ ቆሞ
በመጸለይ ነበር፡፡ ለረጅም ሰዓታት በመቆም
ይጸልይ ስለነበረ እግሩ ሊቆረጥ ችሏል፡፡ አንድ
እገሩ ቢቆረጥም ጸሎቱን እና ትጋቱን አላቋረጠም
ነበር፡፡ በአንድ እግሩ ለሰባት አመታት ጸልዮአል፡፡
ጻድቁ ተክለሃይማኖት ዘመኑን ወንጌልን ለማያምኑ
ሰዎች በመስበክ ብዙ ኢ-አማንያንን ክርስትናን
እንዲቀበሉ አድርጓል፡፡ የቤተ ክርስቲያን
አገልግሎት እንዲሰፋ እና ገዳማዊ ሕይወት
እንዲጠነክር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ ሲሆን
በዘጠና ዘጠኝ ዓመቱ ነሐሴ ሃያ አራት ቀን
በክብር አርፏል፡፡ ጸሎቱ ቃል ኪዳኑ እና በረከቱ
ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
43 viewsbisrat, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 19:26:58
24 viewsbisrat, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 19:26:42 #ሐምሌ_19

...በፈላ የጋን ውኀ ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና ኢየሉጣን ሊጨምሯቸው ሲሉ ቅድስት ኢየሉጣ በፈራች ጊዜ ቅዱስ ቂርቆስ ‹‹እናቴ ሆይ አትፍሪ፤ አናንያ፣ ዓዛርያና ሚሳኤልን ከእሳት ነበልባል ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ የፈላ ውኀ ያድነናል›› እያለ ያረጋጋትና በተጋድሎዋ እንድትጸና ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላት ነበር፡፡

ቅድስት ኢየሉጣም እንደገና በሃይማኖቷ ጸናች። እግዚአብሔር አምላኳንም አመሰገነችው። ልጇን ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንም “ልጄ ሆይ ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት
አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ” አለችው።

የመኳንንቱ ጭፍሮችም እሳት ወደ አለበት ጋኖች ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን በጨመሯቸው ጊዜ የውሃው ፍላት ወደያውኑን ቀዘቀዘ። ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና።

‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል፤›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (መዝ. ፴፬፥፯)፡፡
የቅዱስ ገብርኤል፣ ቅድስት ኢየሉጣ እና ቅዱስ ቂርቆስ ጸሎታቸው፣ ምልጃቸው ይጠብቀን!!!
24 viewsbisrat, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ