Get Mystery Box with random crypto!

# ጥቅምት_15_የ12ቱ_ቅዱሳን_ሐዋርያት_ የዕረፍታቸው_መታሰቢያ_ነው ። ለሐዋርያት ሞት/ሰማዕትነት | ዝክረ ብሒለ አበው

# ጥቅምት_15_የ12ቱ_ቅዱሳን_ሐዋርያት_
የዕረፍታቸው_መታሰቢያ_ነው ።
ለሐዋርያት ሞት/ሰማዕትነት ምክንያትና መንሻ
ነው የምንለው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ
በመመስከራቸው ነው። የ12ቱን የቅዱሳን
ሐዋርያት ምስክርነታቸውንና አሟሟታቸውን
በቅደም ተከተል እንመልከት፦
# 1_ሐዋርያው_ያዕቆብ => ከ ክርስቶስ ሞትና
ትንሣኤ በኋላ ከእስጢፋኖስ ቀጥሎ
የመጀመርያው ሰማዕት ነው። አሟሟቱን
በሐ.ሥራ 12፥2 በግልፅ ተፅፏል። ንጉሥ ሄሮድስ
በሐዋርያት ላይ መከራ ያፀናበት ጊዜ ነበር።
ያዕቆብም በሰይፍ አንገቱ ተቆርጦ ተገደለ።
ይህም የሆነው ከክርስቶስ እርገት በኃላ 44-45
አመት አከባብ እንደተሰዋ ይነገራል።
# 2_ሐዋርያው_ጴጥሮስ => ቅዱስ ጴጥሮስ
ከክርስቶስ ስቅለት በፊት ክርስቶስን
እንደማያውቀው ቢክድም ከክርስቶስ እርገት
በኋላ ግን ስለ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ
ለመጀመርያ ጊዜ የሰበከው ጴጥሮስ ነው!
ኢየሱስ በዮሐ.21፥8-19 እንደተናገረው
ሐ.ጴጥሮስ ዳግመኛ ለመካድ እንቢ በማለቱ
በሮም ከተማ በሮማውያን እጅ እንደ ክርስቶስ
ልሰቀል አይገባኝም ብሎ ቁልቁል ተስቅሎ
ሞቷል! ይህም ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ በ64
አመት ነበር።
# 3_ሐዋርያው_እንድሪያስ ፦ ወንድሙ ጴጥሮስ
ከተሰዋ ከ6 ዓመት በኋላ በ70ኛው ዓ.ም በ ×
ቅርፅ መስቀል በግሪክ ተሰቅሎ ተገድሏል። 7
ወታደሮች በብርቱ ከገረፉት በኃላ ሥቃዩን
ለማስረዘም በማሰብ በ × መስቀል ላይ ሆኖ
ይህን ይናገር ነበር "ይህችን አስደሳች ዕለት
በጉጉት ስጠብቅ ነበር ለእኔ በመስቀል መሞት
ክብሬ ነው፤ ምክንያቱም መስቀልን ክርስቶስ
በሥጋው ተሰቅሎበት ቀድሶታልና" እያለ 2 ቀን
ለወታደሮች ይሰብክ ይመሰክር ነበር።
# 4_ሐዋርያው_ቶማስ => የክርስቶስን ትንሣኤ
በሐዋርያት ሲነገር አላምንም ያለውና በኋላም
ኢየሱስ ተገልጦ ችንካሩንና የተወጋ ጎኑን
በመዳሰስ ያመነው ሐዋርያ ሲሆን ይህንንም
ለመመስከር ወደ ህንድ ሀገር በሄደ ጊዜ እንደ
ጦር በተዘጋጀ የዛፍ እንጨት ወጋግተው ደግሞም
በጋለ ብረት ካሰቃዩት በኋላ በሕይወት ሳለ
እንዲቃጠል ተደርጎ ተሰዋ። ይህም ከክርስቶስ
ትንሣኤ በኋላ በ70ኛው ዓመት አከባቢ ነበር።
# 5_ሐዋርያው_ፊልጶስ => ክርስቶስን "አብን
አሳየንና ይበቃናል" ያለው ነው። ዮሐ.14፥8።
የክርስቶስን ሞት በመካከለኛውና ምዕራባዊው
እስያ ከሰበከ በኋላ በአመፀኛ ዩሑዳዎች ተይዞ
ከባድ ድብደባና ግርፋት ከተቀበለ በኋላ
በስቅለት ከክርስቶስ ትንሣኤ በኃላ በ54 ዓመት
ተሰውቷል።
# 6_ሐዋርያው_ማቴዎስ => ቀድሞ ቀራጭ
የነበረ ሲሆን አይሁዳውያን ክርስቶስን እንዲቀበሉ
በብርቱ ይፈልግ ነበር ከመሞቱ ከ10 አመት
ቀደም ብሎ የማቴዎስ ወንጌልን ፅፏል። ማቴዎስ
በማቴ.ወ 28፥20 እንደፃፈው ኢየሱስ የሰጠውን
የወንጌል ተልዕኮ በመወጣት በሰይፍ
እስከተሰዋበት ዕለት ድረስ ይሰብክ ነበር። ይህም
የሆነው ከ ክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ከ60 እስከ 70
አመት ነበር።
# 7_ሐዋርያው_ናትናኤል /በርተሎሜዎስ=>
ናትናኤል ከበለስ በታች ሳለ ነበር ፊልጶስ
የጠራው፤ ኢየሱስም ስለናትናኤል ሲናገር
"ተንኮል የሌለበት የእስራኤል ሰው" እንደሆነ
ምስክሮ ነበር፤ ናትናኤልም ኢየሱስ
የእግዚአብሔር ልጅና የኢስራኤል ንጉሥ እንደሆነ
ተናግሮ እንደነበር ዮሐ.ወ 1፥45-50 ተገልጿል።
ናትናኤልም በኢስያ ምሽነር ) ባሁኗ ቱርክ
የክርስቶስን ትንሣኤ አብሥሯል። በኋላ ግን
በአርመኒያ እጅግ አስቃቂ በሆነ ሞት ቁም ስጋው
ተገፎ, አንገቱ ተቀልቶ, ከ ክርስቶስ ዕርገት በኃላ
በ70 አመት ተሰውቷል።
# 8_ሐዋርያው_ያዕቆብ /የኢየሱስ ወንድም
ያዕቆብ=> ከክርስቶስ ሞት በኋላ ለበርካታ
ዓመታት በኢየሩሳሌም መሪ ሆኖ አገልግሏል፤
በወቅቱ ክርስቶስን አሳልፎ የሰጡትና የገደሉት
ሰዎች ያዕቆብ የክርስቶስን ትንሣኤ እንዲክድ
ያስገድዱት ነበር። እነዚህም አይሁዳውያን
በማቴ.ወ 27፥25 ላይ የተጠቀሱት ናቸው።
በኋላም ያዕቆብ የክርስቶስን ትንሣኤ አልክድም
ብሎ በመወሰኑ ከቤተ መቅደስ ህንፃ አናት ጫፍ
ላይ ወደታች ወርውረውት ባለ መሞቱ
እየተገረሙ ጭንቅላቱን በቆልማማ ዱላ
ደብድበውት ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ በ60
ዓመት ተሰውቷል። ይህም በቤተ መቅደስ ጫፍ
ሰይጣን ኢየሱስን ወስዶት የፈተነበት ስፍራ ነው።
# 9_ሐዋርያው_ስምኦን => እስራኤላውያንን
ከሮማውያን እጅ ለማስለቀቅ ብዙ ይተጋ ነበር፤
የክርስቶስን ትንሣኤ በአይኑ ከተመለከተ በኋላ
የወንጌል አርበኛ በመሆን በግብፅ, በሰሜን
አፍሪካ, በቢታንያ, በሊቢያ, በፓርሻ መልካም ዜና
አብስሯል። ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ በ74 ዓመት
በስቅለት ተሰውቷል።
# 10_ሐዋርያው_ይሁዳ ጌታን የሸጠው ይሁዳ
ሳይሆን የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ=> የክርስቶስን
ትንሣኤ በሜሶፖታምያ በአሁኑ ኢራቅ ከሰበከ
በኃላ በማያምኑ ሰዎች በበትር ተመቶ ከ
ክርስቶስ ትንሣኤ በኃላ በ72ኛው ዓመት ሰማዕት
ሆኗል።
# 11_ሐዋርያው_ማትያስ => በአስቆሮቱ ይሁዳ
ቦታ የተተካው ሐዋርያ ነው። በሐ.ሥራ 1፥26 ላይ
እናገኘዋለን። ኢየሱስ 2 2 ሆነው ለምስክርነት
ለመሄድ ከተመረጡ ከ70ዎቹ መካከል 1 ነው
ብለው አባቶች ይናገራሉ፤ ይህም እውነት በሉቃስ
10፥1 ተፅፏል። ማትያስም ከክርስቶስ ትንሣኤ
በኋላ በ70ኛው ዓመት ተሰቅሎ ሳለ በድንጋይ
ተውግሮ ሞቷል።
# 12_ሐዋርያው_ዮሐንስ => ሐዋርያውን ከሀገር
አውጥተው ፍጥሞ በምትባል ደሴት ለእስር
ሰጡት፤ በዚህችም ደሴት ኢየሱስ መልአኩን ልኮ
የመጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻውን ክፍል/ራእይ
ዮሐንስን እንዲፅፍ ነገረው። ራእይን ከፃፈ በኋላ
ከእስር ተፈቶ በቱርክ ጳጳስ ሆኖ አገልግሏል።
ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በህይወተ
ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ
፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ
ነዉ፡፡ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹‹‹ዮሐንስ እኔ
እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ
ምን አግዶህ??›››ዮሐ 21፡20 ይህም እስከ
ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነዉ፡፡በማቴ
16፡18 ላይ ‹‹እዉነት….……ሞትን የማይቀምሱ
አንዳንድ አሉ›››››ያለዉ ቃል ለቅዱስ ዮሐንስና
መሰሎቹ የተነገረ ቃል ነዉ፡፡
"በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን
ጽኑ እኔ ዓለምን ድል ነሥቼዋለሁና።"
ዮሐ.15፥33
እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ሐዋርያት በረከታቸውን
ያድለን አሜን አሜን አሜን!!! ወስብሐት
ለእግዚአብሔር ወለ ወላድቱ ድንግል ወለ
መስቀሉ ክቡር አሜን አሜን አሜን!!!