Get Mystery Box with random crypto!

#በዘመናችን_የተፈጸመው_ድንቅ_የእመቤታችን_ተአምር ___ “ቆዩ እመቤታችን የተቆራረጠውን ሰውነቴ | ዝክረ ብሒለ አበው

#በዘመናችን_የተፈጸመው_ድንቅ_የእመቤታችን_ተአምር

___

“ቆዩ መቤታችን የተራረጠውን ሰውነቴን እንደገና እየቀጣጠለች ስለሆነ እንዳትከፍቱ”

___

ይህ ተአምር የተፈጸመው በ2006 ዓ.ም ነው። እጅግ የታወቀ የሳውዲ ዓረቢያ ባለጸጋ ሰው ነው። ልጅ ስላልነበረው ሶርያ ውስጥ በምትገኝ ጼዴንያ በምትባል ገዳም ስለት የምትሰማ የእመቤታችን ሥዕል መኖሯን ሰምቷል። ሰውዬው በገዳሙ ስለሚፈጸመው ተአምር ስለሰማ በአውሮፕላን ተሳፍሮ ደማስቆ ገባ። ደማስቆ ከደረሰ በኋላ አንድ የታክሲ ሹፌር አግኝቶ ''ጼዴንያ ከምትባል ገዳም ተአምር እንደሚፈጸም ሰምቼ ነው መጣሁት። ባለጸጋ ብሆንም ልጅ የለኝም። ከገዳሙ ሔጄ ልጅ እንዳገኝ ስለት ተስየ ልመጣ ነውና እባክህ ውሰደኝ። ስለቴን ከሰማችኝ ለገዳሟ 800 ሺሕ፣ ለአንተም ወደ ገዳሙ ስለወሰድከኝ 20ሺሕ ዶላር እሰጥሃለሁ'' ብሎት ወደ ገዳሙ ሔዶ ተሳልሞና ተስሎ ተመለሰ።

___

በዓመቱም ወንድ ልጅ ስለወለደ በጣም ደስ አለው። የተሳለውን ስለት ለድረስ ከመነሣ አስቀድሞ ወ ታክሲ ሹፌሩ ደውሎ ''ከዚህ በፊት ጼዴንያ ከሚባለው ገዳም እንደወሰድከኝና ልጅ እንድትሰጠኝ እንደተሳልኩ ታስታውሳለህ'' አለው። የታክሲ ሹፌሩም ''አዎን አስታውሳለሁ'' በማለት መለሰለት። ሰውዬውም ''ስለቴ ስለደረሰልኝ ለገዳሙ የተሳልኩትን፣ ለአንተም ቃል የገባሁትን ልሰጥ በዚህ ቀን ስለምመጣ አውሮፕላን ማረፊያ ጠብቀህ እንድትወስደኝ'' አለው።

___

የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራና የድንግል ማርያምን በረከት በጆሯቸው ቢሰሙም ለበረከት ተሳታፊ ለመሆን ያልታደሉ ሰዎች አሉ። ዙ ሰዎች እግአብሔር ስላደረገው ተአምር ያውቃሉ፤ ይሰማሉም፤ ግን ከበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን አይታደሉም። የታክሲ ሹፌሩም ከእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች የሚመደብ ነው። ባለጸጋው እንደደወለለት ጓደኞቹን ሰብስቦ ''ከሳውዲ ዓረቢያ እንዲህ ዓይነት ሰው ሊመጣ ነው። ይህን ያህል ገንዘብ ይዞ በመምጣት ጼዴንያ ለምትባለው ገዳም ይሰጣል። ገንዘቡን ለገዳሙ ከመስጠቱ በፊት ከአውሮፕላን ሲወርድ ተቀብለን ወደ ሰዋራ ቦታ ወስደን፣ ሰውዬውን ገድለን ለምን ገንዘቡን አንከፋፈልም'' ብለው መከሩ። ሰውዬው ሲመጣ አውሮፕላን ማረፊያ ጠብቀው በታክሲ ወደ ሰዋራ ቦታ ወሰዱት።

___

በመቀጠልም ሰውዬውን ከታክስ አስወርደው የያዘውን ገንዘብ ወሰዱ፤ ከዚያ በኋላ ከአንገቱ ጀምረው አጽቅ፣ አጽቁን ቆራረጡ። አስከሬኑን ከገደሉበት እዳይጥሉት ስለሩ በትልቅ ጆያ ከትተው በታክሲው ከኋላ በኩል ከዕቃ መጫኛው ውስጥ ከትተው ከሚያመቻችው ቦታ ለመጣል ይዘው መሔድ ጀመሩ። አገር አማን ብለው ሲጓዙ ፖሊስ መንገድ ዘግቶ ደንገተኛ ፍተሻ ሲያደርግ ደረሱ። ወደ ኋላ እንዳመለሱ መንገዱ አንድ መስመር ብቻ ያለው በመሆኑ አልቻሉም። አማራጭ ስላልነበራቸው ቆመው መጠበቅ ግድ ሆነባቸው። ፖሊስም መኪኖችን እየፈተሸ እነሱ ካሉበት ደረሰ። እቆሙበት የደረሰው ፖሊስ ታክሲውን ክፈቱ አላቸው። ታክሲው ሲከፈት በትልቅ ሻንጣ ውስጥ ብዙ ገንዘብ ይዘዋል። ፖሊሱም ''እናንተ የታክሲ ሹፌር ናችሁ። ይህን ያህል ገንዘብ ከየት አገኛችሁ'' ሲላቸው ምክንያት ፈጥረው ቢነግሩትም ስላላመናቸው እስቲ የመኪናውን የዕቃ መጫኛ ክፈቱ አላቸው። ሰዎቹ ስለደነገጡ ''አንተ ክፈት፣ አንተ ክፈት'' መባባል ጀመሩ። ድርጊታቸው ፖሊሱ ይበልጥ እንዲጠራጠራቸው አደረገ። ''መኪናው የአንተ አይደለም እንዴ ለምን አትከፍትም'' ብሎ ሹፌሩን ሲያስገድደው ወርዶ ሊከፍት ጎንበስ ሲል “ይህንን የዕቃ መጫኛ እንዳትከፍት” የሚል ድምፅ ከውስጥ ስለሰማ የሠሩትን ያውቃልና ደንግጦ ወደቀ። ፖሊስም በሁኔታቸው ተገርሞ ምን ሆናችሁ ሲላቸው ከተረጋጉ በኋላ ከመጀመሪያው አንሥቶ የፈጸሙትን በዝርዝር ነገሩት።

___

ወዲያው ጋዜጠኞች፣ የካሜራ ባለሞያዎች፣ ፖሊሶች እንዲመጡ ተደረገና የታክሲውን ዕቃ መጫኛ ሊከፍቱ ሲሞክሩ “ቆዩ እመቤታችን የተቆራረጠውን ሰውነቴን እንደገና እየቀጣጠለች ስለሆነ እንዳትፍቱ” የሚል ምፅ ሰሙ። እዲከፍቱ ሲፈቀድላቸው የዕቃ መጫኛውን ሲከፍቱ ሰውዬው ከጆንያ ወጥቶ ቁጭ ብሏል። በሰውነቱ ላይ ምልክት ከመኖሩ ውጭ ምንም የጉዳት ምልክት የለበትም። ከሕይወት ወደ ሞት ተሸጋግሮ የነበረው ሰው ከጆንያ ወጥቶ ሰዎቹ ምን እንዳደረጉት፣ ለምን ወደ ሶርያ እንደመጣ፣ ገንዘቡን ለምን እንደያዘው ፣ ወዴት ሊሔድ እንደነበር ተናገረ።

___

ይህም ተአምር በመጀመሪያ በሶርያ ቲሌቭዥን ቀጥሎም በልዩ ልዩ ቴሌቭዠን ጣቢያዎች ተላለፈ። ለገዳሙ የተሳለውን ገንዘብ አደረሰ። ለታክሲ ሹፌሩም ''አንድ ጊዜ ቃል ገብቻልሃለሁ'' ብሎ 20ሺሕ ዶላር ሰጠው። ይህ በእኛ አገር ተአምረ ማርያ የተጻፈ ሳይን እመቤታችን ዛሬም ተአምር እንደምታደርግ የዓለም ሕዝብ ይረዳ ዘንድ በብዙ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች የተላለፈ ነው።

_ _ _ _ ___

በዚህ በተጨነቅንበት ወቅትም እመቤታችን ከመከራ እንደምትሰውረን፣ ለችግር ብንጋለጥ እንኳ በተአምራት እንደምትታደገን፣ መከራ ላይ ብንወድቅም ለበረከት እንደሚሆንልን በማመን በንስሐ እንዘጋጅ። እምነታችንን እናጥብቅ፣ ራሳችንን ጠብቀን እንኑር።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ከአቅማችን በላይ የሆነውን አምላካችን እግዚአብሔር ከእኛ ያርቅልን። አሜን!!!