Get Mystery Box with random crypto!

#ጥቅምት_17_ቅዱስ_እስጢፋኖስ_ሊቀ_የዲያቆናት_ሁኖ_በሐዋርያት_እጅ_የተሾመበት_ዕለት_ነው። ልዩ | ዝክረ ብሒለ አበው

#ጥቅምት_17_ቅዱስ_እስጢፋኖስ_ሊቀ_የዲያቆናት_ሁኖ_በሐዋርያት_እጅ_የተሾመበት_ዕለት_ነው።

ልዩ ስሟ ሐኖስ በተባለ ቦት በእግዚአብሔር ፈቃድ ቅዱስ በሆነው ጋብቻ የሚኖሩ ስምኦንና  ሃና የሚባሉ ባልና ሚስት ነበሩ፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይሳጠቸው ዘንድ በጾምና ጸሎት በሱባኤ ጸንተው ከኖሩ በኋላ የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ አምላክ ጥር 1 ቀን የተባረከ ልጅ ሰጣቸው።
ስሙንም እስጢፋኖስ ብለው ሰየሙት #እስጢፋኖስ፦የስሙ ትርጉም - አክሊል ማለት ነው፡፡

ከመጥምቁ ዮሐንስ እግር ሥር በመሆን ተምሯል፡፡ በሐዋርያት ዘመን ሁሉም ያላቸውን እያመጡ አንድ ላይ ይኖሩና ይመገቡ ስለነበር ሕዝቡን መመገብ እንዲሁም ቃሉን ማገልገል ለሐዋርያት እጅግ እየከበደ መጣ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ይህን በማስተዋል ሕዝቡን ሰብስበው ከመካከላቸው በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች እንዲመርጡ እና ሕዝቡን እንዲያገለግሉ አደረጓቸው፡፡ ሕዝቡም በሐዋርያት ቃል እጅግ ተደስተው ሰባት ሰዎችን መርጠው በሐዋርያት ፊት አቆሙአቸው ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱና ዋነኛው ቅዱስ እስጢፋኖስ ነበር፡፡ ሐዋርያትም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጭነው ጥቅምት 17 ቀን ሊቀ-ዲያቆናት አድርገው በሰባቱ ዲያቆናት ላይ ሾሙት፡፡

 ከዚያን ዕለት ጀምሮ ዲያቆናት የሐዋርያትን ቤተ ክርስቲያን ማገልግል ጀመሩ፡፡ ዲያቆን ማለት አገልጋይ ማለት ሲሆን በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ለድሆች በትክክል እርዳታ ለማድረስ፣ በማዕድም ለማገልገል ተመርጠው ነበር፡፡ በኋላም እየቆየ ዲቁና በቤተ ክርስቲያን እንደ አንድ ማዕርግ ሆነ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ዲያቆናት ጠባይና አገልግሎት በመልእክቱ ጽፏል፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስ በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ምልክትና ተዓምራትን ያደርግ ነበር፡፡ ብዙ አይሁድም ሲከራከሩት የሚናገርበትን መንፈስ መቋቋም ግን አልቻሉም ነበር፡፡

#ቅዱስ_እስጢፋኖስ_በአህዛብ_ፊት_ያደረገው_ተአምራት:-
ሊቀዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ በአህዛብ መካከል ቆሞ ሲያስተምር ከቆየ በኋላ አንድ አንደበቱ ዲዳ የሆነ ሰው አጠገቡ ቢመጣ በጆሮው የህይወት እስትንፋስ እፍ ቢልበት መስማት የማይችለው መስማት ቻለ፡፡ በዚህም ጣኦት አምላኪውን ናኦስ እና ተከታዮቹ ሁሉ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተመለሱ፡፡

ጣኦት አምላኪው ናኦስ በድርጊቱ በጣም በመናደዱ የተነሣ በአጠገቡ የቆመውን በሬ ልክ ናኦስ በጆሮው ቢተነፍስበት በሬው በምትሃት ለሁለት ተሰንጥቆ በመሞቱ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተመለሱት በናኦስ ምትሃታዊ ድርጊት በመሣባቸው እንደገና ወደ ናኦስ ተመለሱ፡፡ የአህዛብ ልቡና ወላዋይ እንዳይሆንና እንዳይጠፉም በማሰብ ናኦስ ለሁለት ሰንጥቆ የገደለውን በሬ በእግዚአብሔር ኃይልና ድንቅ ሥራ ደግሞ ህይወት ዘርቶ ማስነሳት እንደማይችሉ በማስተማር ልቦናቸው ወላውሎ ወደ ናኦስ የተመለሱትን አህዛብ ገንዘቡ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ኃይልነት እንዲያምኑ አድርጓል፡፡

ናኦስ በአልሸነፍ ባይነትና በአጋንንት ረዳትነት ራሱን ወደ ላይ እንዲንሣፈፍ አድርጎ በአየር ላይ ቢወጣ ቅዱስ እስጢፋኖስ የእግዚአብሔርን ተአምር በማሳየት በትዕግስት ጠብቆ በአጋንንት ረዳትነት ወደ ላይ የተነሳውን ናኦስ በትምዕርተ- መስቀል ቢያማትብበት ይዘውት የነበሩት አጋንንት ሁሉ ለቀውት ሲበተኑ ናኦስም ምድር ደርሶ ተንኮታኩቶ በመውደቁ በጣኦት አምላኪነት የነበሩ ሁሉ ዳግም ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተመልሰዋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!